የኛ ግጥም
44 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
🌺የከንቲባው ልጅ🌺
🔥ክፍል 36

.
ስልክ ቁጥሩ ከጠቀመኝ ብዬ ቤታቸው ላይ የተለጠፈውን ማስታወቂያ በስልኬ ፎቶ አነሳሁትና ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተመለስኩኝ ። #10 ሰዓት ላይ class ነበረኝና በፍጥነት ቁና ቁና እየተነፈስኩ ክፍላችን ደረስኩኝ ። #20 ደቂቃ አርፍጃለው ። ሆኖም ግን አስተማሪው ተንበርከክ ሳይለኝ አስገባኝ ። የ machine element መምህራችን ህንዳዊ ዜጋ ነው ። ያው የሱ ትምህርት ትርጉም በስለሺ እስኪመጣልን ድረስ ምንም እየገባን አይደለም ። ድንጋዩ ማነው እንዳትሉኝ እንጂ ድንጋይ ላይ ውሃ እያፈሰሰ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም ። ሰውዬው ከሚያወራቸው ነገሮች አንዲት እንኳን አትሰማም ። ከሱ እንግሊዝኛ ይልቅ የ shah rhuk khan ህንደኛ በስንት ጣዕሙ ። ደግሞ መቸክቸክ አይደክመውም ። አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አምስት ጊዜ black board እያጠፋ እየፃፈ ፡ እኛንም ያለ ሞያችን ደራሲ አርጎናል ። እኔ ለሰባቱም ትምህርቶች ትበቃለች ብዬ የገዛዋትን አንዷን ባለ #50 ወረቀት ደብተር እሱ በአንደኛው ቀኑ ነበር ብቻውን መሃል ላይ ያደረሳት ። anyways ግን ከህንድ የሚመጡት አስተማሪዎች ይሄን ሁሉ km አቋርጠው የሚመጡበት ምክንያት አይገባኝም ። ሀገር ውስጥ አስተማሪ ጠፍቶ ነው እንዳንል ስንቱ ተመርቆ ስራ ጠፍቶ እቤት ውስጥ ተጎልቷል ። የማስተማር ብቃት ፈልገውም ከሆነ የኛዎቹን የሚበልጡበት አንድም የተለየ ብቃታቸው አይታየኝም ። እንግሊዝኛቸው ግራ የሆነ ። ከኛ ጋር መማር ማስተማሩ ላይ በቋንቋ ካልተግባባን ምኑን ተማርን ። በቋንቋም ብንግባባ ደግሞ የትምህርት አሰጣታቸው የህፃን ጨዋታ ነው ። ሰሌዳው ላይ የሀገር Note ይፅፉና እሱኑ መልሰው ያነቡልናል ። አለቀ ፡ ደቀቀ ። እኛ ማንበብ ከብዶን ነው እንዴ የመጣነው ...? እንዳልኩትም ራጅ ኩማር ሰሌዳው ላይ የቸከቸከውን አንብቦልን መጨረሻ ላይ quiz ፈተነን ። ከፈለጋችሁ ከደብተር ላይ ስሩ ሲለን እኔ ደግሞ የትልቅ ሰው ምክር አይናቅም ብዬ እሱ እንዳለን ከደብተር ላይ copy paste አደረኩት ። ድፍን ምስር ሳልበላ የደፈንኩት የመጀመሪያው ፈተና ሆኖም በ UNESCO ላይ ተመዝግቦልኛል ። በጣም ደክሞኝ ስለነበር ከ class መልስ ወደ ዶርም ገባሁ ። እንዲህ ደክሞኝ እያለም ግን የያዘኝ ሱስ ሊያስተኛኝ አልቻለም ። high school እያለሁ በጣም ሱሰኛ ነበርኩኝ ። ቤተሰብ እንኳን እስኪማረርብኝ ድረስ የጦፈ ሱስ ውስጥ ገብቼ ነበር ። የተያዝኩት #9ነኛ ክፍል እያለሁ ነው ። ያለሱ አይሆንልኝምና ቤተሰቦቼ በጣም ስለሚያዝኑብኝ ከነሱ ተደብቄ እጠቀም ነበር ። ለሱሴ የሚሆን ገንዘብ አላጣም ። ያለኝን ብር በሙሉ እሱላይ ነበር የማጠፋው ። እንደምንም እየቆጠብኩም ቢሆን ከወር ወር ያደርሰኛል ። campus ስገባ ደግሞ እሱኛውን ሱስ ትቼ ሌላ ሱስ ውስጥ ወደኩኝ ። ይሄ ደግሞ ጭራሽ ከድሮው ሱሴ የባሰ ሆነብኝ ። ስራዬ ሁሉ እሱ ብቻ ነው ። ማጥናት ፣ መማር ፣ ምናምን የለም ። ሙሉ ሰዓቴን እሱ ላይ ነው የማሳልፈው ። ዛሬ ግን ለመተው አስቤአለሁ ። ከቻልኩ እስከነጭራሹ ላለመጠቀም ፤ ካልሆነም በየቀኑ ላለመጠቀም ወስኛለሁ ። ብዙ መጎዳትን እንጂ ጥቅምን አላገኘሁበትም ። ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ገንዘቤን ለ tele መገበር ብቻ ነው ። #9ነኛ ክፍል እያለሁ የጀመረኝ የ facebook ሱሴ ካምፓስ ስገባ ወደ telegram ተቀይሮ ይሄው አይኔ እስኪጠፋ ድረስ ስበላ ፣ ስጠጣ ፣ ስማር ፣ ስሄድ ፣ ስቀመጥ ፣ ስተኛ ፣ ብቻ ምን አለፋችሁ #24 ሰዓት ከስልኬ ጋር እንደተቃቀፍኩ ነው የምውለው ።የሰው ልጅ ብዙ አስደናቂ ነገሮችን ፈጥሯል ። ለኔ ግን እስካሁን ድረስ ወደር ያልተገኘለት ፣ የትኛውም ፈጠራ የማይተካከለው ነገር ቢኖር #መተኛት ነው ። እዚጋ አንድ ጊዜ ተረጋጉና ሌላ አለም ውስጥ ሳትገቡ በፊት ነገሩን ላስረዳችሁ ። "መተኛት" የሚለው ቃል ተኛ ፣ ደቀሰ ፣ ወገቡን ፈተሸ ፣ አንሶላ ውስጥ ገባ ፣ አሸለበ እና ከመሳሰሉት የግሪክ ግሶች የወጣ ሲሆን ትርጓሜውም ያው ግሪኮች ከላይ ያሉት ነው ። መተኛት በሶስት ይከፈላል ። አንደኛው ፦ የህዝብና ቤት ቁጠራን ለማባዛት የሚተኛው መተኛት ነው ። ምሳሌ ፦ ባልና ሚስት ። ሁለተኛው ፦ ፈጣሪ የማይወደው ፡ እኛ ሰዎች ግን ደስ ብሎን የምንተኛው መተኛት ነው ። ምሳሌ ፦ ከጋብቻ በፊት ወንድና ሴት የሚተኙት ። ሶስተኛው እና ወሳኙ መተኛት ደግሞ ብቻህን በር ዘግተህ ለጥ የምትለው መተኛት ነው ። ምሳሌ ፦ ተስፋዬ የሚተኛው ። እና ዛሬ ቀኑን ሙሉ ስተኛ ነው የዋልኩት ። እናንተ ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ አልጋ ሂዱ ፤ እሱም ያሳርፋችዋል የተባለ ይመስል ለምሳና ለእራት ብቻ ነበር ከአልጋዬ ላይ የወረድኩት ። አልጋም ላይ ብውልም ግን ምንም አልተኛሁም ። ማሰብ ፣ ማሰብ ፣ እንደገና ማሰብ ። ብዙ ካሰብኩኝ በዋላ የሆነ ነገር ትዝ ብሎኝ በራሴ አፈርኩኝ ። ፍቅር እውር ያደርጋል የሚሉት ተረት በኔ ላይ ሲደርስ አየሁኝ ። ቆይ ከነ ህይወት ጋር ለመሄድ ሳስብ እንዴት ቤተሰቦቼን ዘነጋዋቸው ...? ዝም ብዬ እንደ በግ ለማንም ምኑንም ሳልተነፍስ እብስ ብዬ ልጥፋ ነበር እንዴ ...! አባቷ እንኳን ይሁን የኔን ስም process ውስጥ ለማስገባት ብለው ነው አስቀድመው ከመሄዳቸው በፊት የኔን ውሳኔ ለመስማት የፈለጉት ። እኔስ ምን አስቤ ነው ...? anyways አሁን ግን መሄድ እንኳን ብፈልግ መሄድ የማልችልበት ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት ። ይሄን ደግሞ ለህይወት እንዳልነግራት ስልኳንና በሯን ዘግታብኛለች ። የማገኝህ አብረኸኝ እንደምትሄድ ከወሰንክ ብቻ ነው ብላኛለች ። ለዚህ ብዬ ከቀጠሮው ቦታ ከቀረሁ ለዘለዓለም ከህይወት ጋር መቆራረጤ ነው ። በቦታው ላይ ተገኝቼ አልሄድም ካልኳት ደግሞ ቅስሟን መስበር ይሆንብኛል ። ልክ በቀጠሮው ቦታ እንደተገኘሁ ስታየኝ በቃ አብሮን ሊሄድ ወስኖ ነው የመጣው ብላ በደስታ ታብዳለች ። እኔ ደግሞ በተቃራኒው እንደቀረሁ ስነግራት ከመቅረቴ ይልቅ በቦታው ላይ መገኘቴ ይበልጡኑ ያሳብዳታል ። እንደማልሄድ ነግሬያት ለምን እንደቀረሁ ቁጭ ብላ ምክንያቴን የምትሰማኝ አይመስለኝም ። ብትሰማኝም ግን ለመቅረት ምክንያት የምደረድር ነው የሚመስላት ። ሁሌም ህይወት በኔ ላይ እንዲህ ነች ። መምረጥ የማልችላቸውን ሁለት ነገሮች ፈትፍታ ታቀርብልኛለች ። እኔ ደግሞ የትኛውን መጉረስ እንዳለብኝ አላውቅም ። ለአንድ በሽታ ሁለት መዳኒቶች ቀርበውልኝ የትኛውን እንደ ምውጥ ግራ ገብቶኛል ። ሁለቱም እኔን የማዳን ትልቅ ሀይል አላቸው ። ነገር ግን ሁለቱም በአንድ ላይ አይወሰዱም ። የግድ አንዱን መምረጥ ይኖርብኛል ። የቀጠሮው ቀን ደረሰ ። ህይወት #08 ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ራስ ሆቴል እጠብቅሃለሁ ባለችኝ መሠረት ዛሬ በቦታው ላይ በተስፋ እንደምትጠብቀኝ አውቃለሁ ። አሁን የቀረው የኔ ወስኖ መሄድ ወይም የኔ ጨክኖ መቅረት ብቻ ነው ።
"ያም ቆንጆ ይሄም ቆንጆ ፡
ያም ቆንጆ ይሄም ቆንጆ ፣
ልቤ አላርፍ አለኝ ከአንድ ጎጆ ፡
ከቶ አላርፍ አለኝ ከአንድ ጎጆ ።
ስቋጥር ስፈታ ፡ ሳሰላስል ፡ አንዱን ይዤ ፡ አንዱን ስጥል ፣
ዞሬ ዞሬ ከሁለት ሰው ፡ መምረጥ አንዱን ተቸግሬአለሁ