የኛ ግጥም
45 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 23


.
.
.
ሁሉም ተማሪዎች calculator ይዘው ነው የመጡት ። እኔ ግን በህልሜ የመረቀንኩት አለቀቀኝም መሰለኝ ብዕር እንኳን አልያዝኩም ። ብዕሩን እንደምንም ከመምህር አግኝቻለሁ ። calculator ቀድሞውኑ ለድምር አያስፈልገኝም ፤ አየር ላይ አጫውተዋለሁ ። ብዙ ጊዜ ተማሪ ፈተና ሲደርስ ሲጨናነቁ አያለሁ ። እኔጋር ግን እሱ የለም ። የምችለው ከሆነ እሰየው ፤ ካልሆነ ግን ሲፈልግ ገደል ይግባ ። (ፈተናው ሳይሆን አንተ ነህ ገደል የምትገባው...🙆) ። ፈተናው ተሰጠንና አየሁት ። #5 ጥያቄ ነው ። ከነሱ ውስጥ ግን እኔ ከአንደኛው ጥያቄ ውጪ አንድም info የለኝም ። እያንዳንዳቸው #4 ፣ #4 ነጥብ አላቸው ። ስለዚህ ከ #20% ውስጥ #4% ነው የማገኘው ማለት ነው ። የማውቃትን #1 ጥያቄ ሰርቼ የቀሩትን ደግሞ ከልጆች copy paste ላደርግ ብዬ ቀና ስል #2 አስተማሪዎች አንዱ ከፊት ሌላኛው ደግሞ ከዋላ ሆነው ድምበር እየጠበቁ ነው ። ጥሎብኝ ፈተና ሲከብደኝ መጨናነቅ አልፈልግም ። የቀሩትን #4 ጥያቄዎች በመሰለኝና ደሳለኝ ሞልቼ ወጣሁ ። ከሳምንታት በፊት "ምነው አንተ ልጅ እያሽቆለቆልክ እኮ ነው ፣ በጣም ከስተሃል" ባሉኝ አንደበታቸው ዛሬ ግን class ውስጥና መንገድ ላይ ያገኙኝ ልጆች እንዳለ "ምን ተገኘ ደግሞ ፡ በጣም ተስማምቶሃል" እያሉኝ ያልፉኝ ጀመር ። እንደውም የተመልካች አይን ሲበዛብኝ ሰግቼ ትፉልኝ ማለት ጀመርኩኝ ። እነሱ ግን ትፉልኝ እና ትፉብኝ መለየት ስለከበዳቸው በዋላ ላይ ማስታጠብያ ገዛሁና እሱ ውስጥ እንዲተፉልኝ አደረኩ ። ሁሉም የውፍረቴን ምክንያት ቢጠይቁኝም ፡ እኔ ግን ትንፍሽ አላልኩም ። ምክንያቱም ከዚህ በፊት ስከሳ አንድም ሰው የክሳቴን ምስጢር አልጠየቀኝምና ። ዶርም መሄድ ስላስጠላኝ ወደ Library አቀናሁ ። የተባረከው ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ንሰሐ ይገባል ፤ እንደኔ አይነቱ ደግሞ ቤተ መፅሐፍት ገብቶ ላይገባው ግራ ይጋባል ። Final ፈተና እየደረሰ በመሆኑ ሶስቱም የጊቢው Library እንደ አባይ ሞልተው ተማሪዎች ወደ ግብፅ እየፈሰሱ ይገኛሉ ። አሁን ያለሁት ከሶስቱ አንዱ በሆነውና ዘንድሮ ተመርቆ ስራ በጀመረው Central Science and technology Library ውስጥ ነው ። ይሄ ቤተ መፅሐፍት ግን በጣም ዕድለኛ ነው ። ስንቱ ተምሮና ተመርቆ ስራ ባጣበት ዘመን ላይ ነው ሳይማር ተመርቆ ስራ የጀመረው ። anyways እኔ እንኳን የገባሁት እንደ ሌሎቹ የትምህርት መፃፍ ላነብ አይደለም ። ላይብረሪው ከትምህርት መፅሐፍ ውጪ ፡ ጋዜጣ ፣ መፅሔት ፣ FB ፣ Telegram ፣ ወዘተ መጠቀምያ ቦታ አለው ። ያውም እንደ ሳሎን በሶፋ የተሽቆጠቆጠ ቦታ ። እና ብዙ ጊዜ እዚህ እየመጣሁ Telegram ስለምጠቀም ላይብረሪስቶቹ ጭምር ሸምድደውኝ እንደ ድንገት እንኳን አርፍጄ ቦታው ላይ ሰው ሊቀመጥ ሲመጣ "ሰው አለው" ማለት ጀምረዋል አሉ ። እዚህ የሚገኙ ጋዜጦች ግን አይመቹኝም ። ከነሱ ይልቅ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ሽንት ቤቶች ግድግዳ ላይ በተለያዩ የጊቢው Activist ተማሪዎች የሚፃፉት ሺህ እጥፍ ይማርካሉ ። ብዙ ጊዜ እንደውም የETV ዜና ሲናፍቀኝ ወደ ሽንት ቤት ጎራ እልና አነባለሁ ። ወደ ውስጥ ሳትዘልቅ ገና ከበሩ መግቢያ ላይ ይጀምራል ። "እንኳን ወደ ተመስገን በየነ የምግብ ማስወገጃ አዳራሽ በደህና መጣችሁ ። እናንተ ብቻ ጠንክራችሁ ብሉ እንጂ እኛ የናንተን የከበሩ ማዕድናት ለመቀበል #24 ሰዓት ዝግጁ ነን ። ለደንበኞች ቦታ ይያዛል ፣ በተጨማሪም በራሳችን ጉልበት ውሃ ወደ ሽንት ቤቱ እንደፋለታለን" ። ወደ ውስጥ ገብታችሁ ሱሪ አውልቃችሁ ቁጭ ስትሉ ደግሞ በአምስቱም አቅጣጫ (ከፊት በር ላይ ፣ ከዋላ ፣ በቀኝ ፣በግራ እና ኮርኒስ ላይ) ከሽንት ቤቱ ውጡ የማያስብሉ ምርጥ ምርጥ ቀልዶችን ያገኛሉ ። ከሁሉም ግን እኔን የምትመቸኝ "ለዚሁ ነበር እንደዛ የበላሁት ...?🙆" የምትለዋ ነች ።

ምሽት ላይ እራት ከጓደኞቼ ጋር በልተን ቶኒ ላይ ሻይ ጠጥተን #01:30 ወደ ዶርም ስንመለስ ህይወት ደውላልኝ telegram እንድገባ ነገረችኝ ። ቀኑን ሙሉ ያልደወለችልኝ አባቷ እቤት ስለዋሉ እንደሆነና በቅርቡ ደግሞ ከሀገር እንደሚወጡ ነገረችኝ ። አብዛኛው ወሬዋ ግን ናፍቆት ነክ ነበር ። እንደውም በ voice ጭምር እየዘፈነች ልካልኛለች ። Studio ሳትገባ ዝምብላ እንደ ቀልድ የምትልክልኝና እቤቷ እያለሁም የምታዜምልኝ ሙዚቃዎች ህይወት አላቸው ። እሱ ብቻ አይደለም ፤ የምትፅፍልኝ መልዕክቶች ጭምር ልቤን ያቆሙታል ። "ቀኑን ሙሉ ስላንተ ሳስብና ስፅፍልህ ነበር የዋልኩት" ብላኝ ይሄን መልዕክት ላከችልኝ ። "ከዋክብትንና የምድር አሸዋን መቁጠር ከሚሳንህ በላይ ላንተ ያለኝን ስሜት በቁጥር ማወቅ ያዳግትሀል ። በዚች ምድር ላይ ለመኖር #1ሺህ ምክንያቶች ላያስፈልጉኝ ይችላሉ ። ባይሆን ያንተ መኖር ብቻ በራሱ በቂዬ ነው ። አንተ የቀኔ ፀሀይ ነህ ፤ ብሩህ ታደርግልኛለህ ። የምሽቴም ጨረቃ ነህ ፤ ጨለማዬን ትገፍልኛለህ ። ልቤ ፣ ደምስሬ ፣ አይምሮዬ ፣ ንግግሬ ፣ ልብ ምቴ ፣ ህይወቴ ፣ ሁሉ ነገሬ ውስጥ ገብተሃል ። ሌላው ይቅር ፡ አይኔን እንኳን ስጨፍን የምትታየኝ አንተ ነህ ። ብዙ ጊዜ ስትጎጂ እና ስታለቅሺ ማየት አልፈልግም ብለኸኛል ። የኔ ጌታ እየተጎዳሁና እያለቀስኩ ነው የዋልኩት ። አውቃለሁ አጠገቤ መሆን ስላልቻልክ እንጂ እኔን ለመጉዳት እንዳልራከኝ ። ቢሆንም ግን በጣም እየፈራሁ ነው ። ህይወት ላንተ ናት ፡ ሞት ግን ለኔ ፣ ደስታ ላንተ ነው ፡ ሀዘን ግን ለኔ ፣ አብሮ መሆን ላንተ ፡ ብቸኝነት ግን ለኔ ፣ ሁሉ ነገር ላንተ ፡ አንተ ግን ለኔ ነህ ። አንተን መናፈቅ ያስደስታል ፤ ለዛም ነው ቀኑን ሙሉ የማስብህ ። ምሽት ላይ ሆኜ አንተኑ ሳስብህ ከዋክብት አዝነውልኝ ሊያፅናኑኝ ከሰማይ ላይ ይረግፋሉ ። ምናልባት ሰማይ ባዶ ሆና ካገኘሀት ብዙም አትደነቅ ። ምክንያቱም በደምብ እንዳስብህ አድርገህኛልና ። ቀኑን ሙሉ ድምፅህን ሳልሰማ ፣ አይኖችህን ሳላይ ፣ በናፍቆት አሳለፍኩኝ ። ረስተኸኝ ይሁን እያልኩ እጨነቃለሁ ። የኔን ስሜት ሳልነግርህ ከማንም በላይ ታውቀዋለህ ብዬ አስባለሁ ። አብጄ አማኑኤል ብገባ እራሱ አንተን መርሳት የሚቻለኝ አይመስለኝም ። ደግሞ ህይወት መልሳ እንደምታገናኘን እና ወደፊት አንድ ቀን አብረን እንደ ምንህን ተስፋ አደርጋለሁ ። በህይወት መንገድ ላይ መመለስ የለም ፤ ጉዞው ወደፊት ብቻ ነው ። በመንገዴ ውስጥ ብዙ ሰው ላይኖር ይችላል ። ለኔ ግን እሱ አያሳስበኝም ። ነገር ግን የኔ ጌታ ፡ ያንተ አለመኖር ያማል ። ከአለም ጋር ከተለያየን ቆየን ፤ ምክንያቱም የኔ አለም አንተ ነህ ። ፀሀይ ፊቷን አዙራብኝ ብርሃን ካጣሁ ቆይቻለው ፤ ምክንያቱም የኔ ፀሀይ አንተ ነህ ። ጨለማ ውስጥ ነኝ ፣ ምንም አይታየኝም ። ጭር ያለ ቦታ ነኘ ፤ ምንም አይሰማኝም ። እልም ያለ በረሃ ውስጥ ነኝ ፤ በውሃ ጥም ልሞት ነው ። ቀኑንና ለሊቱን መለየት ከብዶኛል ። በቶሎ ላገኝህ ብዬ ተኝቼ አሁንስ ነጋልኝ ስል ተመልሶ ይጨልማል ። እኔ አንተን ሳጣህ እንኳን ቀኑን እራሴንም እረሳለሁ ። ግን የኔ ጌታ እስካሁን ድረስ ያልረሳሁት #

1 ነገር አለ ። እሱም አንተ ነህ ። ምክንያቱም አንተን እረሳሁ ማለት በህይወት የለሁም ማለት ነው" ። ይሄን ሁሉ ብላኝ ፣ በድምጿም እየዘፈነች ልቤን ብታቆመውም የኔ መልስ ግን ዝምታ ነው ። ዝም ....ይቀጥላል