የኛ ግጥም
45 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
😘የከንቲባው ልጅ😘

🔥ክፍል 17


.
.
.
"ሰዎች መሞት አይፈልጉም ነገር ግን ፣
መንግሥተ ሰማይ መግባት ይፈልጋሉ ።
ንሰሐ አይገቡም ግን ሁሉንም የሰፈር ዕድር ገብተዋል"።

ሲመስለኝ አሁን ሞት ለ #3ተኛ ጊዜ ነገር እየፈለገኝ ነው ። የከንቲባው ልጅ ከመፍራቷ የተነሳ ጥቅልል ብላ ደረቴ ውስጥ ሽጉጥ ብላለች ። ("ሞት ርስት ነው ፤ መፈራቱስ ለምንድነው ...?") ። የጠረጠርነው ሰውዬ ይመጣ ይሆን እያልን በጉጉት (ይቅርታ በፍርሃት...😬) እየጠበቅን ነው ። እስካሁን ግን ምንም ነገር ሳናይና ሳንሰማ ቀኑ ወደ ምሽት ተለወጠ ። ሁሉም ነገር ፀጥ ረጭ ብሏል ። እኛም ድምፃችንን ብቻ ሳይሆን ትንፋሻችንን ጭምር አጥፍተን ኩርምት ብለን ተቀምጠናል ። በድንገት ሳናስበው በራችን ሲንኳኳ ሁለታችንም ከአልጋው ላይ ተስፈንጥረን ተነሳን ። ቀስ ብዬ ወደ በሩ አመራሁና 'ማ ማ ማነው...?' አልኩኝ በተንቀጠቀጠ ድምፅ ። "እኔ ነኝ" አለ ድምፁ አዲስ ያልሆነብኝ ሰው ። 'አንተ ማነህ ፡ ስም የለህም' አልኩት ፈራ ተባ እያልኩ ። "እኔ ነኝ የናንተን የዕንግድነት ቆይታና መስተንግዶ የምከታተል" አለን በትህትና ። ሁለታችንም በሀይል ኡፍፍፍ አለንና በሩን ከፈትኩለት ። "ዛሬ ምነው ድምፃቹ ጠፋ ፡ ምሳ ላይም አልነበራቹም ፡ እራቱንም ልትዘልቁበት አስባቿል እንዴ ...?" አለን በተለመደው ትህትናና ፈገግታ ። የእጅ ሰዓቴን ሳይ #01:33 ይላል ። እራት እዚው እንዲያ መጣልን ነግሬው እጅ ነስቶ ተመለሰ ። ብዙም ሳይቆይ ምግብ ከወይን ጋር ይዞ መጣ ። የምግብ ፍላጎት ባይኖረንም ነገ መንገደኛ በመሆናችን እንደ ነገሩ አድርገን ከላይ ትንሽ ወይን ከለስንበት ። በስተ መጨረሻም የእስካሁኑን ሙሉ ወጪ አስደምረን ከፍለንና አመስግነን ከአስተናጋጁ ጋር ተለያየን ። ለነገ ጠዋት #12:00 ሰዓት Alarm ሞልተን አንሶላ ውስጥ ገባን ። "ሞት ወደ ትጉህ ነፍስ ፣ እርጅናም ደግሞ ወደ አፍቃሪ ልብ አትመጣም" በሚለው ቃል እራሳችንን አሳምነን ተኛን ። ጠዋት ነግቶ Alarm እኛን ሳይሆን እኛ አላርሙን ቀስቅሰነው ከውቢቷ ደብረ ዘይት ከተማ ወደ በረሃዋ ንግስት ድሬዳዋ ጉዞ ጀመርን ። አዲስ አበባ ፣ አዳማ ፣ አዋሽ ፣ መታሃራ እያለን ሂርና ደረስን ። ወርደን ምሳችንን ዕሮብ በመሆኑ ቆንጆ በየ አይነት በልተን ጉዞ ቀጠልን ። ከዋላችን ከተለመዱት የጭነትና የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችና ሚኒባሶች ውጪ የተለየ አይነት መኪና ስላላየን ውስጣችን ለጊዜው ሰላም ተሰምቶታል ። ሙቀቱንና የመንገዱን አሰልቺነት ተቋቁመን ፣ የደንገጎን አስፈሪ ተራራማ zigzag ቁልቁለት መንገድ ወርደን #11:00 ሰዓት አካባቢ ድሬዳዋ ገባን ። ለጥንቃቄ ብለን ቀስ ስላለች እንጂ የሸገር ድሬ መንገድ ለትክክለኛው ሾፌር ከ #9 ሰዓት አያልፍም ። Tata የሚባሉት አውቶብሶች ግን በጣም ደካማ ስለሆኑ ጠዋት #12:00 ሰዓት ከሸገር ተነስተው ምሽት #03:00 ሰዓት ድሬ የሚገቡበት ሰዓት ይበዛል ። ለጊዜው ድሬዳዋ ራስ ሆቴል አርፈን እራት እዛው በልተን ትንሽ አምሽተን ወደ ከንቲባው ልጅ ቤት በከዚራ በኩል አድርገን አቀናን ። የቀድሞ ቤቷና የአባቷ መኖርያ ቤት አካባቢ ስንደርስ መኪናውን አቆመችና ለትንሽ ደቂቃ ትኩር ብላ በቁጭት አየችው ። እምባዋ ጉንጮቿ ላይ ሳይራመዱ ታፋዋ ላይ ዱብ ዱብ ማለት ሲጀምሩ ፤ አይኗን ከቤቱ ላይ ነቀለችና እምባዋን ዋጥ አድርጋ መኪናውን አስነስታ ወደ ራሷ ፣ ከአባቷ ውጪ አንድም ሰው ወደ ማያውቀውና ዝር ወደማይልበት ቤት አመራን...
ከምሽቱ #02:00 ሰዓት አልፏል ። የከንቲባው ልጅ ቤት ደርሰን የውጪኛውን በር ከፍተን ገብተን ፣ መኪናዋንም ጊቢ ውስጥ አቁማ ወደ ውስጥ ገባን ። የሳሎንና መኝታ ክፍሏ መብራቶች በርተው ነበር የጠበቁን ። ትዝ ይለኛል ስንወጣ አጥፍተን ነበር ። ህይወት ዞር ብላ በፍርሃት ታየኝ ጀመር ። "አጥፍተን ነበር አ የሄድነው ...?" አለችኝ ። እራሴን በአዎንታ ወደላይ ወደታች ነቀነኩኝና 'አባትሽ የዚህን ቤት ቁልፍ አላቸው እንዴ ...?' አልኳት ባለፈው ሲመጡ በር ላይ ነኝ ብለው ስለደወሉላት ። "አዋ አለው ፣ ባለፈው ሲመጣ ረስቼ ነው ብሎኛል" አለችኝ ። ከእሷና ከአባቷ ውጪ ቁልፉን ማንም ከሌለው ፣ በዛላይ አባቷ እንዳሉትም ሀገር ውስጥ ከሌሉ ፣ በተጨማሪም ቢሾፍቱ እያለን ካየነው ሰውዬ ጋር ሲደማመር የሆነ ችግር እንዳለ በግልጽ ተሰማኝ ። "ይሄኔ ነው መሸሽ" አለ ያገሬ ሰው ፤ አሁን ገና ፍርሀት የሚባለው ስሜት አካሌን ወረረው ። "ሞት ላይቀር ፍርሀት ፤ አመል ላይቀር ቅጣት" ። "ፈሪ ውሃ ውስጥ ሆኖ ያልበዋል" ፤ እኛ ግን የጦርነት ቀጠና ውስጥ ሆነን ደርቀናል ። "ፈሪ ከአልጋ ላይ ወድቆ ይሞታል" ፤ እኛ ግን አልጋ ላይ የመውጣት አቅምም የለንም ። "ፈሪ የሚያባርረው ሳይኖር ይሸሻል" ፤ እኛ ግን የሚያባረን እያለ ካለንበት መንቀሳቀስ ከብዶናል ። ሞት በየሁሉም ሰው በራፍ ላይ የሚቆም ጥቁር መላክ ነው ። እኛም ቤቱን ፈትሸነው ባዶ መሆኑን ስናረጋግጥ ይህ በራፋችን ላይ የቆመው የሞት መላክ እንዳይወስደን በሩን ሁለት ጊዜ ቆለፍነው ። ተስፋና ፍርሀት ሁሌም አይነጣጠሉም ። ፍርሃት ያለ ተስፋ ፣ ተስፋም ያለ ፍርሃት አይኖርም ። ፍርሃትን የሰጠ አምላክ ፡ ተስፋንም አይነፍግም ። "ተስፋ ያልቆረጠ መነኩሴ ምናኔ ሲሄድ ሴቲቱን ይሰናበታል" አሉ አበው ። እኛም ምንም እንኳን ወደሞት እየሄደን ቢመስለን በምድር ተስፋ አልቆረጥንም ። አባቷ መጥቶ ከሆነ ብለን በሀገር ውስጥ ስልኩ ላይ ስትደውልለት "የደወሉላቸውን ደምበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም..." አለች የቴሌ ሰራተኛ ። በጣም ተጨንቀናል ። ጭንቀታችን በከንቱ ይሁን አይሁን ግን አናውቅም ። ከመተኛታችን በፊት ከጊቢ የዶርም ጓደኛዬ ደውሎልኝ ነገ ትምህርት እንደሚጀምር እና class ባልገቡት ተማሪዎች ላይ እርምጃ እንደ ሚወሰድ ነገረኝ ። ስልኩ speaker ላይ ስለነበር ያለኝን ነገር የከንቲባው ልጅም ሰምታለች ። አንድ ሶፋ ላይ ሆነን የመረቀነ የድሬ ልጅ መስለን አይናችንን አፍጥጠን እየተያየን የዕሮቡ ለሊት ለሀሙሱ ጀምበር እጁን ሰጠ ። ስንት ሰዓት እንደ ተኛን አላውቅም ። እራሳችንን እዛው ሶፋ ላይ ተቃቅፈን አገኘን ። አዲስ ነገር ካለ ብለን ቤቱንና ጊቢውን ፊትሽነው ። ሁሉንም ነገር ግን ትተነው እንደ ተኛን አገኘን ። ትንሽም ቢሆን ተረጋግተን "በቃ አንተ ወደ ጊቢ ተመለስ ፡ በኔ ምክንያት ትምህርትህን እንድታጣ አልፈልግም ። እስካሁን ድረስ ለኔ ያደረከው እራሱ ከበቂም በላይ ነው" አለችኝና ልትሸኘኝ ወደ ጊቢው ወጣን ። እኔም እቅፍ አረኳትና 'አይዞሽ እሺ ምንም አይፈጠርም ። ደግሞ ብዙም አልቆይም ፡ ፍቃድ ብቻ ጠይቄ ነው የምመልሰው እሺ' አልኳትና ስታለቅስ ላለማየት ብዬ በፍጥነት ወደ ውጪኛው በር አመራሁ ። ልክ በሩን ስከፍት "ትተኸኝ በዛው እንዳትቀርብኝ እሺ የኔ ጌታ ፣ ብቻዬን እፈራለሁ ፣ ደግሞም ማንም እንደሌለኝ ታውቃለህ አይደል...?" አለችኝ ልክ የመጀመሪያው ቀን ስንገናኝ "ትተኸኝ አትሂድ ፡ ማንም ሰው የለኝም" ባለችኝ ዜማ ። ዞር ብዬ ሳያት ፊቷ በዕምቧ እየታጠበ ነው።