የኛ ግጥም
45 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 8


.
.
.
እጄን ይዛኝ ፡ ወደ ቤት እየወሰደችኝ "እንዴት በዚህ ሰዓት መጣህ ...? ፡ ትምህርት የለም ወይንስ #03:00 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ናፈኩህ ...?" አለችኝ እንደ መሽኮርመም ነገር ሆና ። ስለ ጊቢው ሁኔታ ጓደኛዬ የነገረኝን እንዳለ ነገርኳት ። እሷም እንደኔው በረብሻው ደስተኛ ባትሆንም ትምህርት እስከ ቀጣይ እሮብ ባለመኖሩ በውስጧ እልል እያለች እንደሆነ ያስታውቅባታል ። ለምን እንዲህ አናደርግም "ዛሬ አርብም አይደል ፡ እስከ እሮብ ድረስ #5 ቀን አለን ። እና ይሄን ሁሉ ቀን #1 ቤት ውስጥ ከምንጎለት ፡ ለምን ከዚህ ርቀን የሆነ ቦታ ሄደን ፈታ ብለን አንመለስም ...?" አለችኝ ። አሰብኩበት ፡ ጉዳቱ አልታየኝም ፤ ተስማማሁላት ። በውሳኔው ሁለታችንም ደስተኞች ነን ። "ከበቂ በላይ ገንዘብና መኪና አለን ፡ ግን የት ነው የምንሄደው ...?" የሚል ሀሳብ አነሳች ።
"ብቻ አንቺ ኑሪልኝ ኑሪልኝ
ኑሪልኝ እንጂ ፣
የትም ይመቸኛል የትም
የትም ይመቸኛል የትም" ።
አይነት መልስ ሰጠዋት ። "ለመዝናናት ደብረ ዘይት እና ሀዋሳ አሪፍ እንደሆኑ በቲቪ አይቻለሁና ከሁለቱ አንዱ ቢሆን ደስ ይለኛል" አለችኝ ። እኔም 'ሀዋሳ ሄጄ አላውቅም ፤ ቡሾፍቱ ግን #3 ጊዜ ስለሄድኩኝ እዛ ሳይሻል አይቀርም' ስላት በደስታ ተስማማች ። ነገ በጠዋት ጉዞ ወደ ውቢቷ ደብረ ዘይት ከተማ ። ከባንክ ቤት ለጉዞው ብለን #10 ሺህ ብር አወጣች ። ATM ስላላት ተጨማሪም ካስፈለገን ፡ ባስፈለገን ሰዓት እናወጣለን ብላኛለች ። ምናልባት መንገድ ላይ ረሀብ ከለቀቀብን ብለን ለነገ ምግብ ተባብረን አዘጋጅተናል ። ነጋና ጉዞ በጠዋት ጀመርን ። ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ መካከል የ #512km ርቀት እንዳለ ታፔላ ላይ ተለጥፎ አምብቤያለሁ ፤ ሰዎች ስያወሩም ሰምቻለሁ ። Google ላይ search ሳደርግ ግን #452 km ነው የሚለው ። በዚህም በዚያም በመኪና (ኢትዮ ፣ ዘመን ፣ ገዳ ፣ ሰላም ፣ ወዘተ bus'ኦች) ከድሬ ሸገር ለመድረስ ከ #8 ሰዓት እስከ #9 ሰዓት ይፈጃል ። በባቡር እራሱ ሄደን ነበርና ከሸገር ጠዋት #02:00 ሰዓት ተነስቶ ቀን #10:00 ሰዓት ነው ድሬ የሚደርሰው ። እሱም መብራት ካልጠፋ ነው ፤ ከጠፋ ማታ #03:00 ሰዓትም ሊገባ ይችላል ። ከድሬ ደግሞ ቀን #07:00 ሰዓት ይነሳና ምሽት #03:00 ሰዓት ለቡ ፡ አዲስ አበባ ይገባል ። በፕሌን ደግሞ የ #45 ደቂቃ መንገድ ነው ። እኛ #01:00 ሰዓት ነበር በ Rava #4 መኪና ከድሬ የተነሳው ። ፈጣሪ ካለ እስከ #10:00 ሰዓት ፊንፊኔ እንገባለን ። anyways የከንቲባው ልጅ መኪናዋን አየር ላይ እያከነፈችው ነው ። ቢቻለኝና ስልጣኑ ቢኖረኝ የአምስት ዓመት ስራ ልምድ እፅፍላት ነበር ። በአነዳዷ ስገረም አየችኝ መሠለኝ "አይዞህ እሺ ፡ ከቢሾፍቱ ስንመለስ አለማምድሀለው" አለችኝ ። የድሬ ሸገር asphalt ብዙም ውጣ ውረድ የለውም ። በግራም በቀኝም አልፎ አልፎ ከሚታይ ትናንሽ ሰፈር ውጪ በረሀ ነው ማለት ይቻላል ። አብዛኛው መሬት ሰውም ፣ እንስሳም ፣ እፅዋትም የለውም ። አፈር ብቻ ። ከብዙ ደቂቃ ዝምታ በዋላ ፡ "እስቲ ሶስቴ ደብረ ዘይት የሄድክባቸውን ጊዜያት አስታውሰኝ ...?" አለችኝ ።

'ለመጀመሪያ ጊዜ ደብረ ዘይት ከተማ የሄድኩት #6ኛ ክፍል እያለሁ ነበር ። በወቅቱ scout የሚባል የወጣቶች ህብረት ነበር ። scout ማለት ወጣቶች ከትምህርት ሰዓታቸው ውጪ መጥፎ ቦታዎች እንዳይውሉ ፣ የሀገር ፍቅር እንዲኖራቸው ፣ ወላጆቻቸውን እንዲያከብሩ ፣ በትምህርታቸውም እንዲጠነክሩ የሚያደርግ ምርጥ ማህበር ነው ። ወጣቶች ላይ ትኩረት ያድርግ እንጂ ህፃናትና ጎልማሶችም የማህበሩ አባል መሆን ይችላሉ ። እና ያኔ ነበር ቢሾፍቱን ከጓደኞቼ ጋር ሀ ብዬ የረገጥኩኝ (ሀ እንኳን ያልኩ አይመስለኝም ...) ። እዛ የሚገኙትን አየር ሀይል ተቋምና ባቦጋያ ሀይቅን ጎብኝተን ገባን ። በዓመቱም ድጋሜ በ scout ሄደንና ሆራ አርሰዴንና የወጣቶች ማዕከልን አይተን ፡ ደስ የሚል ጊዜ አሳልፈን ተመለስን ። ለመጀመሪያ ጊዜ በጀልባ ሀይቅ ላይም የተንሳፈፍኩትም ያኔ ነበር ። እንዴት ደስ እንደሚል አጠይቂኝ ። በዛን ጊዜ ሙገር scout በእግረኛ ሰልፍ እንደ ኢትዮጵያ ታዋቂ ነበር ። ብዙ ፕሮግራም ላይ ተሳትፈናል ፣ ብዙ ቦታዎችን ሄደናል ። እንደውም ከአባሎቻችን መካከል አንዱ እድል አግኝቶ አሁን USA ነው ያለው ። አሁን ላይ ግን አባላቱ በትምህርት ምከንያት በየ ዩኒቨርስቲው ስለተበታተኑ ማህበሩ ፈርሷል' አልኳት ትንሽ እንደማዘን ሆኜ ። "እሺ ለሶስተኛ ጊዜስ እንዴት ሄድክ ...?" አለችኝ ። 'ለ #3ኛ ጊዜ እንኳን ደብረ ዘይት የሄድኩበት ምክንያት ለየት ይላል ። ታሪኩም ረዘም ስለሚል እንዳላሰለችሽ ሌላ ጊዜ ልንገርሽ' አልኳትና በረዥሙ ተንፍሼ አየር ወሰድኩኝ ። "የምለቅህ እንዳይመስልህ ፡ ምሳ ከበላን በዋላ ትተነፍሽያታለሽ" አለችኝ እየሳቀች ። "ስማኝማ ፡ ፊትለፊታችን ምንድነው ይሄ ሁሉ መኪናና ሰው...?" አለችኝ ትንሽ እንደ መደንገጥ ነገር ሆና ። 'አይዞሽ አትፍሪ ፡ አሁን አዋሽ ደርሰናል ። በዚህ መንገድ የሚያልፍ ማንኛውም መኪናና እቃ ሳይፈተሽ ንቅንቅ አይልም ። እንደ ኢትዮጵያ ብዙ የኮንትሮባንድ እቃዎች የሚያዙት እዚህ ነው ። ምክንያቱ ደግሞ ህገ ወጥ መሣሪያዎች ፣ ጫማ ፣ ልብስ ፣ electronics ፣ ወዘተ ቁሳቁሶች በውጫሌ በኩል ወደ ድሬዳዋ ስለሚገቡ ነው' አልኳትና መኪናችንን check አርገው ምንም የተለየ ነገር ስላልያዝን ሳያቆዩን ለቀቁን ። አዋሽ የሚሰሩ ፈታሾች ግን የሚሰሩት እንደ ሙዳቸው ነው ። ደስ ሲላቸው ያለሽን controband እቃ እንዳለ ፣ ሲያሻቸው ግማሹን ይወስዱብሻል ። መፈተሽ ሲሰለቻቸው ደግሞ ምንም ነገር ሳያዩ ያሳልፋሉ ። ይሄን ደግሞ ብዙ ጊዜ በዚህ ስናልፍ ታዚቤያለሁ ። የድሬ ሸገር መንገድ ርዝመት ከሙቀቱ ጋር ተዳምሮ በጣም አሰልቺና አድካሚ ነው ። ብዙ ሰዓት ሄደናል ። መተሃራ ለምሳ ወርደን ማታ የሰራነውን take away በልተን ፣ ትንሽ አረፍ ብለን ጉዞ ቀጠልን ። ከመኪናው ቴፕ ላይ የምትከፍታቸው ሙዚቃዎች ያበዱ ናቸው ። ለነገሩ ልጅቷም እብድ ነገር ናት ። እንደኔው የአስቱካ ወዳጅ ናት ። "ጨጨሆ ፡ ጨጨሆ" እያለች ከአስቴር አወቀ በላይ እየጮኸች ሳያት እብደቷ ተጋብቶብኝ እኔም ሙድ ውስጥ ገባሁ ።እንዲህማ ከቀጠልን መኪናዋ አክሮባት መስራቷ ነው ። አሁን ተገለበጠች ፡ አሁን ተፈጠፈጠች እያልኩ ከምሰጋ ብዬ ለትንሽ ደቂቃ መኪናውን አቁመን እብደታችንን እንድንጨርስ ነገርኳት ። አቆመችና "ስማኝማ ፡ ሽንቴ መጣኮ" አለችኝ....


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................