የኛ ግጥም
45 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
💐የከንቲባው ልጅ💐

🔥ክፍል 15


.
.
.
"ከአራት ዓመት በፊት #9ኛ ክፍል እንደጀመርኩ ነበር ። የከዚራ ልጅ ብሆንም Elementery እያለን በጣም የምወደውና የምቀርበው ብቸኛው ልጅ አቤል የሳቢያን ሰፈር ልጅ ስለነበር አንድላይ ለመሆን ሳብያን high school ተመዘገብኩኝ ። ከእለታት በአንዱ ቀን በትምህርት ቤታችን ጊቢ ውስጥ crazy day የሚባለውን የፈረንጆች የዕብደት ቀን ለማክበርና ለየት ብሎ የሚመጣ ሰውም እንደ ሚሸለም ጭምር ከተማሪዎች ጋር ወስነን የሚከበርበት ቀን ደረሰ ። አብዛኛው ተማሪ የተቀዳደደ ልብስ ለብሰው እንደ ሚመጡ ግልፅ ነውና እኛ ግን ከነሱ ለየት ብለን ለመቅረብ የግድ አዲስ ፈጠራ መጠቀም ነበረብን ። በደምብ አስበንበትና ተዘጋጅተንበት ሁለታችንም የዕብደቱን ቀን ለማክበር ተያይዘን ወደ ሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አቀናን ። እንዳሰብነውም አብዛኞቹ የተቀዳደደና የቆሸሸ ልብስ ለብሰው ፣ ፊታቸውን ደግሞ ከሰል ተቀብተው ነበር የመጡት ። ትኩረት መሳብ የቻልነው ግን እኛ ነበርን ። ያን ዕለት እኔን አይቶ ይቺማ ሴት ናት የሚል ፤ ልክ እንደኔው አቤልንም አይተው ወንድ መሆኑን የሚያውቅ ከሁለታችን በስተቀር አንድም አልነበረም ። ከፆታችን ውጪ ሁሉንም ነገር ተቀያይረናል ። እሱ የኔን ቀሚስ ፣ ጡት ማስያዣ ፣ ሹራብ ፣ ሂል/ታኮ ጫማ ፣ human hair ጭምር ገዝተን አድርጎ ፣ ሁሌም ከኔላይ የማጠፋዋን pink ሻርፕ በአንገቱ ዙሪያ ጠምጥሞ ፣ ቦርሳዬንም በጀርባው ተሸክሞ ፣ ከንፈሩንም Lip stick ተቀብቶ ምን የመሰለች ቆንጆ ኮረዳ መስሏል ። እኔ ደግሞ የሱን ሰፊ ጂንስ ሱሪ ፣ ሸሚዝ ፣ Adidas ጫማ ፣ ፀጉሬ እንዳይታይ ደግሞ ከላይ በሱ ኮፊያ ሸፍኜ ፣ እሱ ፂም ባይኖረውም ጉንጮቼ ላይ ፀጉር ለጣጥፌ ምን የመሠለ ሸበላ ወንድ ሆኛለሁ ። ለኛ ዕብደት ልብስ መቅደድ ፣ የቆሸሸ መልበስ ፣ ፊትን በቀለም ማጥቆር ሳይሆን ፈጣሪ ወንድ አድርጎ ፈጥሮት እንደ ሴት የሚሆን ፤ ሄዋን አድርጎ ፈጥሯት እንደ ወንድ የሚያረጋት ፣ ባጠቃላይ ወንድና ሴት ቦታቸውን ተቀያይረው ተፈጥሮን ሲቃወሙ ማየት ነው ዕብደት ። ይህ ነገር ደግሞ ከነጮቹ ከነ ሰልባጃቸው ወደ ሀገራችን እየገባና እየተስፋፋ ያለው ጉዳይ ነው ። ወንዱ ሴት ይመስል ከንፈሩን ደም የጠጣች ድመት አስመስሎ ፣ ፀጉሩን አሳድጎ እንደ ጭላዳ ዝንጀሮ ነስንሶ ፣ ከሰውነቱ ጋር የተጣበቀ ሱሪ ለብሶ ፣ ጆሮውን ተበስቶ ፤ ሴቷም ፀጉሯን ተቆርጣ ፣ ሱሪ ለብሳ ፣ ጡንቻ እያሳየች የወንድ አካሄድ እየሄደች ማየት ቀስ በቀስ በሀገራችን እየተለመደ መቷል ። አላማችንም ይህን ነገር መፀየፍና መከላከል ስለነበር ይህ አይነቱ ድርጊት ዕብደት መሆኑን ማሳወቅ እንጂ ፆታ ተቀያየሩ የሚል አልነበረም ። በዚህም ሁሉም ተስማምተውበት ሽልማቱን ወስደን ዝግጅቱም አለቀ ። ከት/ቤት ጊቢ ወተን አቤል ሊሸኘኝ ወደኛ ሰፈር አቀናን ። በሰዓቱ በጣም ጠምቶኝ ስለነበር እዚው ጠብቀኝ መጣው ብዬው በቀኝ በኩል ወደሚታየው ሱቅ ሄድኩኝ ። ባለሱቁን #2 ጁስ ስጠኝ ብዬው መቶ ብር ሰጠውት ። ወንድ መስዬው ስለነበር ድምፄን ሲሰማ ደንግጦ ነበር ። መልሱን እስኪፈልግ ድረሰ ዞር ብዬ አቤልን እያየሁት ፤ እሱም ወደኔ ዞሮ በአይኑ እየቃየኝ ነበር ። እውነት ለመናገር ከራስ ፀጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ድረስ እንዳለ የኔን ልብሶች ስለተጠቀመ ላየው ሰው እሱ አቤል ሳይሆን ህይወት ናት ። ባለሱቁ 'ይኸው የኔ ወንድም ይቅርታ እህት ለማለት ነው' ብሎኝ መልሱን ሲሰጠኝ ከዋላዬ የተኩስ ድምፅ ሰማሁ" ።
"ስዞር ፡ አቤል እዚው ጠብቀኝ ባልኩበት ቦታ ላይ ተዘርሮ ወድቆ አየሁት ። መኪና ውስጥ ሆነው ነበር የተኮሱትና መኪናዋ ሳትቆም በዛው ሄዳ ተሰወረች ። በቃ በዛች ሰዓት የማስታውሰው ነገር ቢኖር ለአባቴ ደውዬ ያለንበትን ቦታ ነግሬው ፤ እስኪመጣ ድረስ ሰው ተሰብቦ እንዳይበዛ ባለሱቁን ለምኜው አቤልን ተሸክመን ወደ ቤቱ ውስጥ እንዳስገባን ነው ። አቤል በጣም ተዳክሞ ነበር ፤ ብዙ ደምም ከተተኮሰበት የዋላው ጭንቅላት ፈሶታል ። ሆስፒታል መውሰዱ አማራጭ አልነበረም ፤ መጀመሪያውኑ ወደሱ ሮጬ ስደርስ ህይወቱ አልፏል ። አባዬም በፍጥነት መጥቶ ሁለታችንንም ወሰደን ። ቦታው በከዚራ እና በሳቢያን መካከል ስለነበር ባለሱቁ ሁለታችንንም አያውቀንም ነበር ። ሳስበው አባቴ መጥቶ እስኪወስደን ድረስ ተጠምጥሜበት እያለቀስኩ ስለነበር ከአለባበሱ አንፃር አቤል ሴት እንደሆነ ነው የሚያምነው ። ከዛን አባቴ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ ...? ገዳዮቹ ማንም ይሁኑ ማንም እኔን እንደገደሉ አድርገው ስለሚያምኑ በአቤል መቃብር ላይ የኔን ስም አፃፈበት ። ከኔና ከአባቴ ውጪ ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቅ ሶስተኛ ሰው አንተ ብቻ ነህ ። አቤል ዘመድና ቤተሰብ አልነበረውም ። በቃ ብቻውን በራሱ ለራሱ ሰርቶ የሚማር ልጅ ነበር ። እኔ እሱን እሱም እኔን ብቻ ነው የሚቀርበው ። የዋህ ፣ ለሰው አሳቢ ፣ መልከ መልካም እና ጠንካራ ልጅ ነበር ። ልባቸውን አቆሽሸው ልብሳቸውን ከሚያሳምሩት ወገን አልነበረም ። ባለው አቅም ያለውን ፅድት ያለች ዩኒፎርም ከንፁህ ልቡ ጋር ያዋሀደ ምርጥ ልጅ እንጂ ። ለዛም ነበር እሱ የሚማርበት ት/ቤት የተመዘገብኩት ። አባቴ የኔን ምርጫ ስለሚያከብር ብቻ ሳያቅማማ ነበር እዛ ያስመዘገበኝ ። ምን ዋጋ አለው ፡ አሁን ላይ ስሙ እንጂ እሱ የለ ። ለኔ የታሰበውን አፈር እሱ ቀመሰልኝ ። እሱንና እናቴን ለይቼ እላያቸውም ። እናቴ ህይወት ልትሰጠኝ ህይወቷን አጣች ። አቤል ደግሞ ህይወቴን ሊያስቀጥል ህይወቱ ተቋረጠ ። ሁለቱም አስበውበትና አቅደውበት ባያድኑኝም ለዛሬው ህይወቴ ምክንያቶች ናቸው ። ከአቤል ቀብር በዋላ አባቴ እንኖርበት ከነበረው ከዚራ ከሚገኘው ቤት ሌላ አዲስ ቤት ገዛና በድብቅ እዛ አስቀመጠኝ ። ቤቱ ላይም ከላይ 'የሚከራይ' ብሎ ለጠፈበት ። ሰዎች ሊከራዩ ሲደውሉ ብዙ ብር ስለሚጠራባቸው ማንም አይከራየውም ። ከኔና ከአባቴ ውጪ እዛ ቤት ውስጥ እኔ እንዳለሁ የሚያውቅም አልነበረም ። በዛ ቤት ውስጥ ለ #4 ተከታታይ ዓመታት አብዛኛውን ጊዜ ብቻዬን ፤ ጥቂቱን ደግሞ ከአባቴ ጋር አሳለፍኩኝ ። አንተን እስካወኩበት እለት ድረስ ከቤት መውጣት ፣ መልበስ ፣ መብላት ፣ መጫወት ፣ ምንም ነገር አያምረኝም ነበር ። የሁሉም ቀናት ውሎዬ ተመሳሳይ ናቸው ። መተኛት ፣ ማንበብ ፣ ፊልም ማየት ፣ ትንሽ መብላት ፣ በጊታሬ መዝፈን ፣ ቅዳሜና እሁድ ደግሞ ከአባቴ ጋር መሆን ነው ። ይሄንንም ለማድረግ አንድ ዓመት ፈጅቶብኛል ። ከአቤል ሞት በዋላ ለአንድ ዓመት በአንድ መኝታ ቤት ውስጥ የሱ ደም የለበሰ አካል በህሊናዬ ውስጥ እየተመላለሰ እየወቀሰኝ ደንዝዤ አሳለፍኩኝ ። ከዛን በዋላ ነው ቀስ በቀስ ወደ ቀልቤ የተመለስኩት ። ከነዚህ ሁሉ ጊዜያት በዋላ አንተን ሳገኝ ለምን በአንዴ እንደ ተለወጥኩ ታውቃለህ ...?" አለችኝና ከቦርሳዋ ውስጥ የሆነ ፎቶ አውጥታ ሰጠችኝ ። ፎቶው ላይ ያለውን ልጅ ሳይ ለማመን ነበር የከበደኝ ።

@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል..........