Ethio Construction Engineering
32.4K subscribers
6.23K photos
359 videos
1.99K files
3.21K links
🔨 World Construction Engineering
Latest updates, tips, and tutorials on building, civil engineering, and construction in World.
Learn, build, and grow with us!

📨 @Philemona7 Or @ETCONpBOT

For Ad:- https://telega.io/c/etconp
Download Telegram
Ethio Construction Engineering
Photo
👉በሃይድራውሊክ ምህንድስና የምንጠቀማቸው የኮምፒውተር ሶፍትዌሮች
.
ዘመኑ የቴክኖሎጂ እንደመሆኑ በፊት በእጅ የሚሰሩ ረጃጅም እና አድካሚ ቀመሮች (calculation ) ፣ መረጃ መሰብሰቢያ እና ማደራጃዎች እንዲሁም የተለያዩ ንድፎች (Design and modeling ) በሶፍትዌር በቀላሉ እየተሰሩ ይገኛሉ ... ስራን ከማቅለል በተጨማሪ ትክክለኛ መረጃ ካስገባንላቸው ከግድፈት (error) ነፃ እና ፈጣን የሆነ ስራን ይሰሩልናል።
በሃይድሮሊክ ምህንድስና የምንጠቀማቸው የተለያዩ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮች አሉ።

እነዚን ሶፍትዌሮች አጠቃቀም በፅሁፍ ማቅረብ አድካሚ እና ሶፍትዌሮቹን በትክክል ለመጠቀም የሚያስችል ብቃትን ለማዳበር የማይመች በመሆኑ ደግሞም የቅርበት ክትትል እና ልምምድን ስለሚፈልጉ በዚህ ፔጅ መለጠፍ አልቻልንም ። ነገር ግን አንድ ሃይደራውሊክ ኢንጂንየር የሶፍትዌር ስልጠና መውሰድ አለበት የምንላቸውን የሶፍትዌር አይነቶች ከታች በዝርዝር እናያለን ~
.
🚧Spreadsheet app - የተለያዩ የምህንድስና ካልኩሌሽኖችን ለመፍታት (solve) ይጠቅማል
.
🚧Flow Master - የውሃ ቧንቧዎችን ፣ የጎርፍ መሄጃ ቦዮችን እና የተለያዩ ክፍት የውሃ ማሳለጫዎችን (open channel ) ለመንደፍ (design) ይጠቅማል
.
🚧Storm CAD - የጎርፍ እና የተለያዩ ተፋሰስ ቱቦዎችን ለመንደፍ ያገለግላል
.
🚧Culvert Master - የውሃ መቀልበሻ (culvert) መዋቅሮችን ለመንደፍ ይጠቅማል
.
🚧Water CAD - የተለያዩ የውሃ ማሰራጫ ስርዓቶችን ለመንደፍ ይጠቅማል
.
🚧Epanet - ይህ ሶፍትዌር እንደ water CAD የተለያዩ የውሃ ማሰራጫ ስርአቶችን ለመንደፍ ይጠቅማል ።

📌ማስታወሻ ፦ የወተርካድ እውቀቱ ካሎት ይህን ሶፍት ዌር መማር ጥቅም የለውም ።
.
🌟HEC-HMS በዝናብ የሚከሰት ጎርፍን ለመገመት እና ሞዴል ለመስራት ያገለግላል።
.
🌟CropWAT - በመስኖ ንድፍ ወቅት የምንጠቀማቸውን የመረጃ ግብአቶች ተንትኖ ይሰጠናል ለምሳሌ፦ Crop water requirement , crop irrigation requirement, reference evapotranspiration , Scheme water supply , evaluate rain fed production and drought effects , ወዘተ...
.
🌟ETo - calculator - ኢቫፖትራንስፓይሬሽንን ካልኩሌት ለማረግ ይጠቅማል!።
.
🌟ArcHydro ,GeoRAS, AutoCAD, HydroDEM እና የመሳሰሉትን እንደ ግዴታ ባይሆንም ማወቁ ግን ተገቢ ነው።

#Hydraulics

@etconp
👍21💔2👏1
👉በ ውስጥ መስመር ለተጠየቅነው ምላሽ

📩ጥያቄ ፦ "ዝናብ (rainfall) ለምን በ cm/ mm ይለካል ?"

📤መልስ፦ የሚለካው የዝናብ መጠን በእርግጥ (actual) የዝናብ መጠን አይደለም። ዝናብ ሲለካ በcm/mm የሚለካው፤ ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት የሚዘንበው ዝናብ በጎርፍ መልክ ከመፍሰስ፣ ወደ አፈር ውስጥ ከመስረግ እና በሌላ መልክ ከመባከን አግደነው
የዘነበው ዝናብ ቢጠራቀም የሚፈጥረው ጥልቀት (depth) ነው።

🏷ይህ ማለት 100cm ዝናብ ተመዘገበ ቢባል የዘነበው ዝናብ ከስርገት እና በጎርፍ መልክ የሚፈሰው ቢታቀብ (ወይም በታንክ ብናጠራቅመው) የ100cm ጥልቀት አለው ማለት ነው።

📌The depth of the resulting rain is the thickness of the total rainwater layer.

🪧Depth and thickness are
distances are they not? That is why centimeters are their unit.

#Hydraulics

@etconp
👍2🙏1
👉ትንሽ ስለ ጊቤ 3 ሃይድሮኤሌትሪክ ግድብ ፕሮጀክት

▶️የፕሮጀክቱ ስም፦ ጊቤ 3 ሃይድሮኤሌትሪክ ግድብ
▶️የብሮጀክቱ ባለቤት (Client) ፦ የኢትዮጵያ ማብራት ሃይል
▶️የፈጀው ወጪ በ ዩሮ€ 1,470 million

➡MAIN TECHNICAL DATA

⏺የግድቡ ቁመት (Dam Height) ፦ 250m
⏺የግድቡ የቁንዲ ርዝመት (Crest length)፦ 630m
⏺ግድቡ በሚያርፍበት ቦታ ላይ የተደረገ ቁፋሮ መጠን (Excavation)፦ 4,000,000m^3
⏺የተሞላው የኮንክሪት መጠን (Roller compacted concrete) ፦ 6,114,000m^3
⏺የ Power house መጠን፦ 234×37×43
⏺የተርባይን አይነቶች እና ብዛት ፦10ፍራንሲስ ተርባይን እያንዳንዳቸው 187MW የማመንጨት አቅም ያላቸው
.
➡POWER & ENERGY
.
⏺የማመንጨት አቅም (Installed capacity) ፦ 1870 MW
⏺በአንድ አመት የሚያመነጨው የሃይል መጠን ፦ 6500GWH/yr

⏺የውሃ ማቆርያው(Reservoir)
ስፋት (Surface area)፦ 200 km²
⏺ውሃ የማቆር አቅም (Storage capacity)፦ 14,000 x 160 m³
.
➡የወንዝ ቅልበሳ ክንውን (River diversion)

⏹ሁለት ኮፈር ግድቦችን ተጠቅሟል (እነዚህ ግድቦች አፈርን ከድንጋይ ጋር በመጠቅጠቅ የተሰሩ ናቸው Embankment dam የሚባለው)

⏺የነዚህ ግድቦች የላይኛው አካል ቁመት (Upstream height ) ፦ 55 m 
የታችኛው አካል ቁመት (Down stream height) ፦ 19m

📍ሶስት ወሃ ቀልባሽ ዋሻዎች ተቆፍረዋል ባጠቃላይ 3218 m ይረዝማሉ

#Hydraulics

@etconp
👍19❤5
👉እስኪ አሁን ደግሞ አለማችን ትልቁ የንፁህ መጠጥ ውሃ ማጠራቀሚያ ስለሆነው የሳውዲ አረቢያው ብሪማን የውሃ አቅርቦት ፋሲሊቲ እናውራ

⭕▶ይህ የውሃ ማጠራቀሚያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2014 በአለም የድንቃድንቅ መዝገብ (World gunnies  book of records) ላይ የአለማችን ትልቁ Water supply Reservoir (የውሃ ጋን) በመባል ተመዝግቧል
.
⭕▶የ ብሪማን የውሃ አቅርቦት ፋሲሊቲ 11 ትላልቅ  ሪዘርቮየሮች ሲኖሩት አንዱ ሪዞርቮየር 120m ዲያሜትር እና 18m ቁመት አለው እንዲሁም 187,500m^3 በላይ መጠን ያለው ውሃን ማቆር ይችላል
.
⭕▶ፕሮጀክቱ 200M ዶላር የፈጀ ሲሆን ከአስራአንዱም የውሃ ታንከሮች 2,062,500m^3 ውሃ የማቅረብ ብቃት አለው
.
⭕▶ እነዚህ የውሃ ጋኖች ከተለመደው የውሃ ጋን አሰራር ወጣ ያለ አሰራርን የተጠቀሙ ሲሆን ከግዝፈታቸው አንፃር በድልልድዮች የምናያቸውን post-tensiond ኮንክሪት ግድግዳዎችን በመጠቀም ታንፀዋል የውሃ አቅርቦቱንም ለማቀላጠፍ እርስ በእርሳቸው በሃይድራውሊክ የተያያዙ ናቸው። (ስለ ፖስት ቴንዥንድ ከታች ያለውን ፁፍ ይመልከቱ)
.
⭕▶ከአስራ አንድ ጋኖች የምናገኘው የውሃ መጠን 800 ኦሎንፒክ ስታንዳርድ የመዋኛ ገንዳዎችን ይሞላልናል ለአንዱ ስናሰላው ደግሞ 73 ያህል ገንዳዎችን ይሞላልናል
.
⭕▶ ለአንድ አመት እንኳ ውሃ ከናካቴው ቢጠፋ እነዚህ ሪዘርቨየሮች የጅዳ ከተማን የውሃ አቅርቦት የማሟላት አቅም አላቸው።

#Hydraulics

@etconp
👍11❤1
Ethio Construction Engineering
👉ትንሽ ስለ ጊቤ 3 ሃይድሮኤሌትሪክ ግድብ ፕሮጀክት ▶️የፕሮጀክቱ ስም፦ ጊቤ 3 ሃይድሮኤሌትሪክ ግድብ ▶️የብሮጀክቱ ባለቤት (Client) ፦ የኢትዮጵያ ማብራት ሃይል ▶️የፈጀው ወጪ በ ዩሮ€ 1,470 million ➡MAIN TECHNICAL DATA ⏺የግድቡ ቁመት (Dam Height) ፦ 250m ⏺የግድቡ የቁንዲ ርዝመት (Crest length)፦ 630m ⏺ግድቡ በሚያርፍበት ቦታ ላይ የተደረገ ቁፋሮ…
👉የውሃ ተርባይን አይነቶች

▶️የውሃ ተርባይን ተሽከርካሪ (በራሱ ዛቢያ የሚዞር ወይም Rotary ) ማሽን ሲሆን ውሃ በፍጥነቱ አማካኝነት የሚፈጥረውን ሃይል (Kinetic Energy ) እና በሚወረወርበት ርዝመት አማካኝነት የሚፈጥረውን ሃይል (potential Energy) ወደ ሚካኒካል ስራ (መዞር መሽከርከር) የሚቀርልን ማሽን ነው።

▶️የውሃ ተርባይኖች የተፈጠሩት በ19ኛው ክፍለዘመን ሲሆን ይህም ማለት የኢንደስትሪው አብዮትበፈነዳበት ወቅት ነው። ስራቸው በወቅቱ ለነበሩ ኢንደስትሪዎች ሜካኒካል ሃይልን ማመንጨት ነው።

▶️በዚህ ዘመን ግን ትልቁ ስራቸው ከውሃ የሚመጣን ሃይል (kinetic and potential energy) ወደ ሚካኒካል ኢነርጂ መቀየር ነው።

▶️ውሃን ዘውረን ለምናገኘው ሃይል (hydro power ) የምንጠቀመው የተርባይን አይነት የሚወሰነው ውሃው (ሃይል የሚያመነጭልን ውሃ) ተርባይኑን ተንደርድሮ የሚመታበት ርዝመት (ከፍታ ) በእንግሊዘኛው Head በምንለው እና የውሃው መጠን (Volume) ወይም የፍሰት አቅም (Discharge) ላይ በመመስረት ነው።

⏺ከዚህ አንፃር የውሃ ተርባይኖች በአጠቃላይ ለ ሁለት ይከፈላሉ፦

▶️1- Reaction Turbine
▶️2- Impulse Turbine

⭕1-Reaction turbine፦ ይህ የተርባይን አይነት የአሰራር መርሁ በኒውተን 3ተኛ ህግ (law of action and reaction ) ላይ የተመሰረተ ነው።
መካከለኛ (30-300m) እና አነስተኛ (< 30m)  የውሃ የመስፈንጠሪያ ርዝመት (Head) ላላቸው ሃይል ማመንጫዎች ተመራጭ ነው።

⏺የሪአክሽን ተርባይን አይነቶች፦
✅Francis turbine
✅Kaplan turbine
✅Tyson turbine
✅Gorlov helical turbine ....ወዘተ
.
⭕2-Impulse turbine፦ በዚህ የተርባይን አይነት በተሽከርካሪው የተርባይን አካል ምላጮች ላይ የሚያርፈው የውሃ ግፊት ተመሳሳይ ሲሆን እና ለመሽከርከሩም ምክንያት ውሃው የሚፈጥረው የኬኔቲክ ኢነርጂ ልዩነት ነው። የውሃው ኬኔቲክ ኢነርጂ ወደ ፖቴንሻል ኢነርጂ የሚቀየረው ኖዝል በሚባለው የተርባይኑ ክፍል ነው። በተርባይኑ ምላጭ ላይ ምንም አይነት የኢነርጂ ለውጥ አይከሰትም።
የዚህ የተርባይን አይነት መንቀሳቀሻ መርሁ የኒውተን 2ተኛ ህግ ነው። ትላልቅ Head (>300m) ላላቸው ሃይል ማመንጫዎች ተመራጭ ነው።
የኢምፐልስ ተርባይን አይነቶች፦

▶️Peltone turbine አይነቶች

✅Turgo turbine
✅Cross flow turbine
✅Jonval turbine
✅Screw turbine.....ወዘተ

🚧በዚህ አጭር ፅሁፍ ከኢምፐልስ ተርባይን ስለ ፔልቶን ተርባይን ከሪአክሽን ተርባይን ስለፍራንሲስ እና ካፕላን ተርባይን እናነሳለን
.
.
▶Pelton Turbine
.
ይህ የተርባይን አይነት ከኢምፐልስ ተርባይን አይነቶች አንዱ ሲሆን አገልግሎቱም ትልቅ Head ላላቸው የሃይድሮ ኤሌትሪክ ስራዎች ነው። በዚህ የተርባይን አይነት የውሃው ጉልበት ወደ ኬኔቲክ ኢነርጂ የሚቀየረው ኖዝል (nozzel) በሚባለው የተርባይኑ ክፍል ነው። ከዚ ክፍል የሚፈነጠረው የውሃ ሃይል ትይዩ በሆነ አቅጣጫ የሚገኘውን የተርባይኑን ምላጭ (buckets or blades) ይመታና ገፊ ሃይል (impulsive force ) እንዲፈጠር ያደርጋል ። ይህ ሃይል የተርባይኑ ተሽከርካሪ አካል (rotor part) እንዲሽከረከር ይዳርገዋል። የዚህ አካል መሽከርከር ጀነሬተሩን የኤሌትሪክ ሃይል እንዲያመነጭ ይረዳዋል።
.
ፔልቶን ተርባይን የሚከተሉት ክፍሎች አሉት
.
✅Nozzel
✅Runner and bucket
✔Casing
✔Breaking Jet
.
▶Nozzel- ዋና ጥቅሙ ውሃን ወደ ተፈለገው አቅጣጫ መምራት ነው በተጨማሪም የውሃውን ፍሰት ይቆጣጠራል
(ከታች ምስሉን ይመልከቱ)
.
▶Runner እና Bucket- Runner ማለት ክብ ሰሃን የመሰለ አካል ሲሆን ጫፍ ጫፉ ላይም የኩባያ አይነት ቅርፅ ያላቸው Bucket የሚባለውን አካል ይዟል። ይህ የተርባይን አካል ከፍተኛ ጉልበት ላለው ተወንጫፊ ውሃ ስለተጋለጠ ከጠንካራ የብረት አይነቶች (ብዙን ግዜ stillness
steel ተመራጭ ነው) በጥንቃቄ ይሰራል። የውሃው ተወንጫፊ ሃይል ካቪቴን ለሚባለው እንከን ብዙ ግዜ እንዲጋለጥ ያደርገዋል። (ከታች ምስሉን ይመልከቱ)
.
▶Casing- ይህ ከብረት የተሰራ ቁስ ሲሆን የፔልተን ተርባይኑ Runner ለመሸፈን ይጠቅመናል ። ተጨማሪ ጥቅሞቹ
- Runner 'ሩን ከአደጋ ይከላከልልናል
- በንፋስ አማካኝነት ሊፈጠር የሚችልን loss ይከላከላል
- የውሃን መፈናጠር፤ መረጨት ይከላከላል
- ባኬቱን የመታ ውሃ ወደ tail race እንዲሄድ ይመራልናል
.
▶Breaking Jet- ይህ አካል የውሃውን ተወንጫፊ ጉልበት በመገደብ ራነሩ ፍጥነት እንዲቀንስ ያደርጋል (ብዙን ግዜ ብልሽቶች ሲኖሩ አገልግሎት ላይ ይውላል)
፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨

➡Application
.
ፔልተን ተርባይን አገልግሎት ላይ የሚውለው  የሃይድሮ ኤሌትሪክ ማመንጫው ትልቅ የውሃ መፈንጠሪያ ከፍታ (Head) ኖሮት ነገር ግን የፍሰቱ መጠን (discharge) ዝቅተኛ ሲሆን ነው። ፔልተን ተርባይን ከ44.9-1799.8m ድረስ ባለው Head effective የሆነ ግልጋሎት ይሰጠናል።

ይቀጥላል......

#Hydraulics

@etconp
👍12🏆5❤1
👉አንዳንዴ እንዲ ያሉ ጥቃቅን ነገር ግን ትልቅ ጉዳት የሚያደርሱ ስህተቶች ይሰራሉ።

🚧Fence (አጥር) መስራት አንድን የውሃ ጋን (reservoir )  እኩል ቦታ ተሰጥቶት ዲዛይን ይደረጋል ፤ ይሰራልም።

ለምን ቢባል ምክንያት ደሞ..

- የውሃ ጋኑን (reservoir) ከሰዎችም ሆነ ከእንስሳት ንክኪ ለመጠበቅ
- የውሃ ጋኑን እድሜ ለማራዘም

እንደውም ጥበቃ ተመድቦላቸው ሊጠበቁ ሲገባ እንዲ ያለአጥር ቀርተው በየቦታው እናስተውላቸዋለን - አስቡት አንድ ክፉ አድራጊ በዚህ ጋን ውስጥ ያለን ውሃ ቢበክል ማህበረ ሰብን ሊያወድም አይችልም??

#Hydraulics

@etconp
👍15🏆1
የውሃ ጋኖች (water supply Reservoir)
.
የውሃ ጋኖች ከጥቅማቸው አንፃር ለ ሶስት ይከፈላሉ
.
1-Collector reservoir
2-Service reservoir
3-Supply reservoir
.
እያንዳንዱ ጥቅማቸው ምንድነው……
.
[Collector reservoir ]
.
ይህ የጋን አይነት ዋና ስራው ውሃው ከሚመነጭበት (የገጸ ምድር ወይም የከርሰ ምድር ውሃ) ቦታ ህክምና ከተደረገለት በኋላ የሚቀመጥበት ጋን ነው፡፡ ጥቅሙ የተሰበሰበውን ውሃ ወደተለያዩ ጋኖች እስኪሰራጭ በጊዜያዊነት እንዲቀመጥና ውሃው ለጋኖቹ እንዲደርስ የሚያደርገውን ጉልበት እንዲያገኝ ይረዳዋል፡፡ ብዙን ጊዜ ውሃው ከሚመነጭበት ቦታ አቅራቢያ ይተከላል፡፡ ውሃ ፈሳሽ እንደመሆኑ ብዙን ግዜ ሚፈልቀው ከፍታቸው ካነሱ ቦታዎች ስለሆነ ከሌሎች ጋኖች ይልቅ የዚህ ጋን ከፍታ (elevation) ያንሳል፡፡
.
[Service reservoir]
.
ይህ የጋን አይነት በቋሚነት ከcollecter reservoir የተቀበለውን ውሃ የሚያርፍበት ነው፡፡ አሰራሩም ከሌሎቹ ጋኖች ለየት ይላል ፡፡ ውሃው የሚያደርስበትን ግፊት ለመቋቋም የሚያስቸለውን መካች ጉልበት(reaction force) በበቂ ሁኔታ እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ በቁመትም በመጠንም ትልቅ ነው፡፡ ወጪ ለመቀነስ ከፍ ካለ ቦታ ይተከላል (ውሃ በ3 አይነት መንገድ ይከፋፈላል
.
1-የሞተር ሀይልን በመጠቀም

2-የመሬት የመሳብ ሃይልን (gravity force) በመጠቀም።

3-የሞተር ሃይልንና የመሬት የስበት ሃይልን በማጣመር በመጠቀም እንዲሰራጭ ይደረጋል ፡፡

በአሁን ጊዜ ሶስተኛው አማራጭ በስፋታ አገልግሎት ላይ ይውላል ይህ አማራጭ ከወጪም አንፃር በጣም ተመራጭ ነው ለዚህ ዘዴ ተመራጩ ደግሞ የservice reservoir ከፍ ካለ ቦታላይ መተከል ወሳኝነት አለው፡፡)
ከዚህ ጋን ቀጥታ ለስርጭት ቧንቧ አይገጠምም ምክንያቱም ከጋኑ የሚወጣው ውሃ ከፍተኛ ጉልበት ስላለው የማሰራጫ ቱቦዎችን ሊያፈነዳ ይችላል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት ቀጣዩን የጋን አይነት መገንባት አስፈላጊ ነው፡፡
.
[Supply  reservoir]
.

የዚህ ጋን ዋና ጥቅም ውሃውን ለስርጭት ወደ ስርጭት ቱቦዎች እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት ከሰርቪስ ጋን ቀጥታ ወደ ስርጭት ቧንቧ ውሃ አይገባም ምክንያቱም ከፍተኛ ሀይል ስላለው የቧንቧዎቹን የመቆየት አቅም ያሳጥራል ብሎም እስከ ማፈንዳት ያደርሳል፡፡ ይህ እንዳይከሰት የሳፕላይ ጋኖች ይገነባሉ፡፡ ይህ ጋን በቱቦዎቹ የሚያልፈውን ውሃ ግፊት በመቀነስና ፈጥነቱን (velocity) ከ 0.5-2 m/s በማድረግ እና ወደ ቱቦዎቹ የሚገባን ሃይል በመቀነስ (Energy dissipate ) ቱቦዎቹ  ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ያስወግዳል፡፡ ይህ ጋን ከፍ ባለ ቦታ ይተከላል ነገር ግን ከፍታው ከService reservoir ያነሰ ነው።
.
Like | Share | Comment

#Hydraulics

@etconp
👍22
ግድብ (Dam) ማለት ገዝፈ አካል ሲሆን የውንዝን ሸለቆ ላይ ተገንብቶ የውሃን ተፋሰስ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሚገታ ነው።

ይህ መግታት (blockage) በውሃ ተፋሰስ ላይ መታቆርን (reservoir) ይፍጥራል ይህም ወሃውን ለተፈለገው አገልግሎት እንዲውል ቀሊል ያደርገዋል ። ይህ አጋጅ ገዝፈ አካል ወይም ግድብ ከተለያዩ ቁሶች ይሰራል ፦ ኮንክሪት፣ የድንጋይና አፈር መደምደም (compaction) ወዘተ...
.
ግድም በዋነኛነት ለነዚህ አገልግሎቶች ይገነባል፦
1- ጎርፍን ለመቆጣጠር - for flood control
2- ለውሃ አቅርቦት እና የመስኖ ስራ - for water supply and irrigation
3- የኤሌትሪክ ሃይልን ለማመንጨት - for electric power generation
4- የአንድን ወንዝ ፍሰት ለመመጠን እና ለመቆጣጠር - for regulation or balancing of a river flow

#Hydraulics

@etconp
👍17
👉Quantity of Water in a Rectangular Tank

💫1. Tank Volume

🚧Use the basic formula:

V = L×B×H
For the given tank:
12 ft × 8 ft × 6 ft = 576 cubic feet (cuft)

💫2. Convert Volume to Water (Liters)

1 cubic meter = 1000 liters
1 cubic meter = 35.31 cuft
So, 1 cuft ≈ 28.31 liters

💫3. Total Water in Tank

576 × 28.31 = 16,307 liters (≈ 16.3 m³)

💫4. Convert to Gallons

US gallon: ≈ 4,308 gallons
UK gallon: ≈ 3,592 gallons

💫5. Simple Shortcut (if dimensions in meters)
Volume × 1000 = liters

❇️Summary: The tank holds about 16,300 liters of water, depending on full capacity.


#WaterTank
#CivilEngineering #QuantityTakeoff #ConstructionBasics #SiteEngineering #WaterCalculation
#TankDesign #EngineeringStudents #VolumeCalculation #ConcreteTank
#Hydraulics #WaterEngineering #BuildingConstruction
#CivilNotes

@etconp
❤10🎉1
💧Design Period in Water Supply Scheme & Factors Affecting Per Capita Water Demand

A well-designed water supply system must ensure safe and adequate water for present and future needs.

Engineers select a suitable design period for each component based on its expected service life, future population growth, and economic considerations.

📌 What is Design Period?

The design period is the future time span for which a water supply system or its components are planned and designed to meet the anticipated water demand efficiently.

📊 Typical Design Period of Water Supply Components

🌊 Source & Intake Structures: 30–50 years

🏗️ Reservoirs: 30–50 years

🚰 Transmission & Distribution Mains: 30–40 years

🏠 Buildings & Pump Houses: 15–25 years

💦 Factors Affecting Per Capita Water Demand

1. 🌡️ Climate – Hot and dry climates increase water consumption.

2. 🏙️ Size of the City – Larger cities generally require more water per person.

3. 👨‍👩‍👧‍👦 Standard of Living – Higher living standards lead to greater water use.

4. 🛁 Habits and Customs – Bathing, washing, gardening, and lifestyle influence demand.

5. 🏭 Industrial & Commercial Development – More industries and businesses increase consumption.

6. ⚙️ Pressure in the Distribution System – Higher pressure often results in higher usage and leakage.

7. 💰 Water Tariff – Lower tariffs encourage greater consumption, while higher tariffs help reduce wastage.

📍 Key Note:

Per capita water demand varies with location, climate, population, economic conditions, and lifestyle.

Accurate estimation is essential for designing an economical, efficient, and reliable water supply system.

#CivilEngineering #WaterSupply #DesignPeriod #PerCapitaDemand #EnvironmentalEngineering #WaterResources #Hydraulics #PublicHealthEngineering #MunicipalEngineering #Infrastructure #EngineeringStudents #Construction #EngineeringNotes #StudyMaterial #WaterDistribution #WaterTreatment #SmartInfrastructure #EngineeringEducation

@etconp
❤9