የኛ ግጥም
44 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
​​🌺የከንቲባው ልጅ🌺
🔥ክፍል 32


"ግንቦት #17,1989 ዓ.ም ከለሊቱ #06 ሰዓት አካባቢ ። ሰማዩ ከሰይጣን በላይ ጠቁሯል ። (ቆይ ግን ሰይጣንን ማንም ሰው ካላየው ፡ መልኩ ጥቁር እንደሆነ በምን አወቅን ፣ ነው ወይስ የማይታይ ነገር ጥቁር ይመስለናል...?) ። ምድርም ያለ ፀሀይ ብርሃን የላትምና የሰማይ ተከታይ ሆናለች ። ከአንዲት እናት በስተቀር ሰፈሩ በሙሉ ፀጥ ረጭ ብሏል ። እናቲቱ ግን እያቃሰተችና እየጮኸች ትገኛለች ። እንዲህም ሆኖ ግን ማንም ሰው አልተረበሸም ። በተቃራኒው ሁሉም ሰው ተጨንቆ ወደላይ አንጋጦ ፀሎት እያደረገ ይገኛል ። በዚያች የጭንቅ ለሊት ሁሉንም ወደ ሳቅ ፣ ደስታና ዕልልታ የቀየረ አንድ ነገር ተፈጠረ ። በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው ወንድ ልጅ ይቺን ምድር በሰላም ተቀላቀለ ። እናቲቱም የልጁን ስም ተስፋዬ ብላ ሰየመችው ። የወደፊት ተስፋዋን እሱ ላይ ጥላለችና" ። ይሄን ታሪክ የስልኬ Note ላይ ፅፌው ስለነበር ፣ ህይወት የልደቴን ቀን ከዛ ላይ አይታ እንዳወቀች ነግራኛለች ። በ #17 ለሊት ስለ ተወለድኩኝ ልደቴን በ #18 ነው የማከብረው ። እና ዛሬ ልደቴ ነው ፤ #22 ዓመት ሞልቶኛል ። (እና ምን ይጠበስ ...) ። ዛሬ እንኳን ጥብስ አይደለም የምፈልገው ። ልደትም አይደል ፣ ለፎቶው ድምቀት ድፎ ዳቦ ፣ ብርቱካን ፣ ሙዝ ፣ ለስላሳ ፣ ፊኛ ፣ ፈንዲሻ እና ግብዳው ሻማ ይሁንልኝ ። እንደውም #21 ዓመት ስላለፍኩኝ አንድ ሳጥን ቢራ ይዛችሁልኝ ኑ ። በነገራችን ላይ በዚህ ዓመት መምረጥ ብቻ አይደለም ፤ መመረጥም እችላለሁ ። እንደውም በቀጣዩ ምርጫ ላይ መሳተፍ እፈልጋለሁ ። በዚሁም እግረ መንገዴን የምርጫ ቅስቀሳ ባደርግ ውስጤ ነበር ። ግን በልደት ቀን ስለ ፖለቲካ አይወራም ። እዛው #MA ሆቴል ምሳ በልተን ፣ ህይወትን ቤቷ ድረስ ሸኘዋትና ጊቢ ውስጥ ስለ ወቅታዊው ችግር ስብሰባ እንዳለና መቅረት እንደሚያስቀጣ ተደውሎ ስለተነገረኝ ለዛው ብዬ ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ገብቻለሁ ። ስብሰባው #08 ሰዓት ተብሎ #10 ሰዓት ተጀመረ ። ስብሰባውን የተጠሩት ሁሉም የጊቢው ተማሪዎች ሲሆኑ ፤ የተገኙት ግን ስብሰባ የሚወዱ ተማሪዎች (አብዛኛው የ Law ተማሪዎች ናቸው...) ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ ባለስልጣናት ፣ የጊቢው አመራር አካላትና የሰሙትን ወሬ ላልሰሙት የሚያወሩ ጋዜጠኞች ናቸው ። የስብሰባው አጀንዳ ፡ ሰሞኑን ጊቢ ውስጥ በተፈጠረው ረብሻ ምክንያት የተቋረጠውን ትምህርት ማስቀጠል ነው ። ይሄን ለማድረግ ደግሞ መጀመሪያ ተጣሉ የተባሉትን ተማሪዎች ማስታረቅ ግድ ነው ። ስብሰባው ላይ ደግሞ የተጣሉት ተማሪዎች አልተገኙም ። ሆኖም ግን በስተመጨረሻ ያልተጣላነውን እኛኑን አስታርቀውን ለሁለት ሳምንታት የተቋረጠው ትምህርት ነገ እንዲጀምር ተወስኖ ስብሰባው ተበተነ ። ምሽት ላይ ጓደኞቼ #ማራኪ club ይዘውኝ ሄደው አንድ ሁለት እያለን ቆንጆ ምሽት አሳልፈን ወደ ዶርም ገባን ። እንኳን ተወለድክልን ያላችሁኝ ቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ፈጣሪ ውለታ መላሽ ያድርገኝ ። ለዚህች ቀን ያደረሰኝ ፈጣሪ ነውና ከሁሉ በላይና በፊት ምስጋናውን እርሱ ይውሰድ ። ጠዋት ነግቶ ቁርስ ሳንበላ ለ #16 ቀን ተቋርጦ የነበረው ትምህርት ተጀመረ ። የልደቴ ቀን ግን ለጊቢው እንደዚህ በረከትን ይዞ ይመጣል ብዬ አላሰብኩም ነበር ። በጊቢው ሰላም መሆን ደስ ቢለኝም ትምህርት በመጀመሩ ግን ከፍቶኛል ። አስቡት እስኪ ፡ #2 ሳምንት ሙሉ ስለ ትምህርት ሳናስብ አሳልፈን በአንዴ ወደ ትምህርት ግቡ ሲባል ትንሽ አይከብድም...? እኔ በበኩሌ ለትምህርት የምንዘጋጅበትን ሌላ ሁለት የዕረፍት ሳምንት ቢሰጠን ባይ ነኝ ።በበላይ አካላትና የሀይማኖት አባቶች በየክፍሉ አስቸኳይ ስብሰባ ተደረገና ስለ ኢትዮጵያዊነት እና ስለ ወደ ፊቷ ኢትዮጵያ እጣ ፋንታ እንድንነጋገር ተደረገ ። እንደ ዕድል ሆኖ እኛ ክፍል የደረሰው የጊቢው president ናቸው ። ስሜን ማን እንደነገሯቸው አላውቅም ፤ "ተስፋዬ እስቲ ኢትዮጵያዊነት ላንተ ምንድነው...?" አሉኝ ከዛ ሁሉ ተማሪዎች እኔን መርጠውኝ ። መጀመሪያ ስሜን ሲጠሩ ደንግጬ ነበር ። ከተነሳሁ በዋላ ግን የኢትዮጵያ አምላክ እረድቶኝ ሰይጣን ይዞት ፀበል እንደ ገባ ሰው መለፍለፍ ጀመርኩኝ ። 'እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም' ብዬ ንግግሬን ስጀምር ሁሉም አፈጠጡብኝ ። 'አይገርማችሁም ፡ እናንተም ኢትዮጵያዊ አይደላችሁም ። በልባችሁ ፡ "አሜሪካዊ ናችሁ በለን" እንደ ምትሉ ተስፋ አደርጋለሁ ። ሁልሽም ኢትዮጵያ ውስጥ ስለተወለድሽ ብቻ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብለሽ የምታስቢ ከሆነ ተሳስተሻል ። ትንሽ እንኳን አናፍርም ...? ፡ ለዚች ክብርት ሀገር ብለው የሞቱ ስንቱ ደግና አንበሳ አባት ፡ ስንቷ ሩህሩና ጀግና እናት በተጠሩባት ፤ እኛ በዘር በሀይማኖት እየተባላን ፡ ከነሱ እኩል ኢትዮጵያዊ ተብለን ስንጠራ ትንሽ እንኳን አይሰቀጥጠንም ...? ፡ እኔ በበኩሌ ስማቸውን ጠርቼ ከማልጨርስና ከማልጠግብ የሀገራችን ባለውለታዎች እኩል ኢትዮጵያዊ ተብዬ መጠራት አልፈልግም ። እስቲ ለዚች ሀገር ሲሉ የሞቱትን ጀግኖች እናስባቸው ። አፄ ቴዎድሮስና በላይ ዘለቀ የሞቱት ለአማራ ክልል ነው ...? ፡ ጀነራል ታደሳ ብሩና ገረሱ ዱኪ የሞቱት ለኦሮሚያ ክልል ይመስላችኋል ...? ፡ አቡነ ጴጥሮስስ የሞቱት ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነው ...? ፡ ነው ወይስ አሚር የሞተው ለእስልምና ይመስላችኋል ...? ። እንደዛ ካሰብባችሁ ተሳስታችኋል ። እነሱ በጊዜያቸው ክልል የሚል ድንበር አልነበራቸውም ። በሀይማኖት መከፋፈል ሀሳቡም አልፈጠረባቸውም ። እነሱና እነሱን የመሰሉ ስንቶቹ ለዚች ክብርት ሀገር ኢትዮጵያ ብለው እንጂ ለዘራቸው አልነበረም ጥብቅናቸው ። ምን ነካን ጎበዝ ...? ፡ ጠላት ከውጪ ሲመጣብን አንድላይ ሆነን እንዳልመከትን ፡ ዛሬ ላይ እርስ በእርስ መጫረስ ምን የሚሉት ጉድ ነው ...! አሁንም ሳስበው ጥላቻው የኛ አይመስለኝም ። እናም ወገኖቼ ፡ የኛን አንድነት የማይፈልጉትን አንድ ላይ ሆነን በፍቅር እንመክታቸው ። ጥፋታችንን የሚፈልጉትን ተቃቅፈን እናሳፍራቸው ። እንደ ክልልና ሀይማኖት ሳይሆን ፡ እንደ ሰው አስበን ኢትዮጵያን ከጥፋት እናድናት ። ያኔ እኔም እናንተም ልክ እንደ ቀደምቶቻችን ኢትዮጵያዊ ተብለን እንጠራለን ። ክልል ሳይሆን ሀገር ስላስረከብናቸው ልጆቻችንም ይኮሩብናል' ብዬ ቁጭ አልኩኝ ። እናንተ ፡ እህህህ የሚለኝ አጣሁ እንጂ እተነትነው የለ እንዴ ...? ። ሁሉም ተራ በተራ የሚሰማቸውን ከተናገሩ በዋላ ፕሬዚዳንቱ "እስቲ ለዚህ ሁሉ ችግር ምክንያቱ ምንድነው ትላለህ ወጣት ተስፋዬ" አሉኝ በድጋሜ ።ይቀጥላል......


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................