የኛ ግጥም
44 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
​​🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 31

.
"የኔ ሻህሩክ ፡ እኔኮ ስቀልድ እንጂ አትሆንም ብዬ አይደለም" አለችኝና ከወንበሩ ላይ ተነስታ በጀርባ በኩል ጥምጥም ብላብኝ ጉንጬን ግጥም አርጋ ሳመችኝና "ይቅርታ እሺ የኔ ጌታ ...!" ብላኝ ወደ ቦታዋ ተመለሰች ። እኔም 'አያሳስብም ፣ ደግሞም ምንም አለተቀየምኩሽም ። ቆይ ግን አንቺስ ምን መሆን ነው የምትፈልጊው ...? ያው ስታድጊ ያላልኩሽ already አርጅተሻል ብዬ ነው' አልኳት ። "ሙት እሺ ፡ እኔ እንኳን መሆን የምፈልገው እንዳንተ ቀላል ላይሆንልኝ ይችላል ። እንዳልከው ማንኛውንም ነገር ከተፋለምንለት ልናገኘው እንችላለን ። የኔ ህልም ግን ያን ያክል ቀላልና በዋዛ የሚኮን ነገር አይደለም ። በቃ ህልም ብቻ እንጂ እውን አይሆንም" ስትለኝ ፡ ይሄን ያክል ምን ለመሆን ብትመኝ ነው አልኩና ህልሟ ምን እንደሆነና በምችለው ሁሉ እውን እንዲሆንላት ከጎኗ እንደምሆን ነገርኳት ። እሷም "የወደፊቱን ህልሜን ብነግርህ እንዲሳካልኝ ከጎኔ እንደ ማትቆም አውቃለሁ ። ይሄን የምታደርገው ደግሞ እኔን ለመጉዳት እንዳልሆነም አውቃለሁ ። የኔ ህልም ያንተ ሚስት መሆን ነው ። እና እውን እንዲሆንልኝ ትረዳኛለህ ...?" አለችኝ ። 'እኔኮ እየቀለድኩ አይደለም የምሬን ነው' ስላት "በቃ እንደውም እሱን እርሳውና አንድ ነገር አምሮኛል" አለችኝ ። 'በአንድ ቀን አርግዘሽ እንዳይሆን ያማረሽ' ስላት "እኔም እየቀለድኩ አይደለም የኔ ጌታ ። ስወድህ ግን እምቢ እንዳትለኝ ። ዋና በጣም አምሮኛል ፤ በእናትህ የምታውቀው ቦታ ካለ እዛ ውሰደኝ" አለችኝ በነዚያ መንግስትን እንኳን ሀሳብ ለማስቀየር ሀይል ባላቸው አይኖቿ ጭምር እየተማፀነችኝ ። የለስላሳውን ሂሳብ ከፍለን በመኪናችን እዛው ድሬዳዋ ከተማ ውስጥ ወደ ሚገኘው #MA ሆቴል በረርን ። ደርሰን ልብሳችንን አውልቀን የዋና ልብስ ከዛው ተከራይተን ለመዋኘት ተዘጋጀን ። ደግነቱ ከኛና ከሚያስዋኘው ልጅ ውጪ ማንም ሰው በቦታው የለም ። "ስማኝማ ፡ ለምን ደብረ ዘይት ያለማመድከኝን ዛሬ ከ #10 test አትፈትነኝም ። ከፈለክ እንደውም final አርገው" አለችኝ ህይወት እየሳቀች ። እኔም 'በዋላ ከከበደሽ ግን የለሁበትም' አልኳትና ወደ ዋና ገንዳው ገፈተርኳት ። አንዴ ጠጥታው ስትወጣ ፣ ሌላ ጊዜ ወደ ውስጥ ስትሰምጥ መጨረሻ ላይ እንደምንም ተረጋጋችና ውሃውን ተቆጣጠረች ። ቀና ብላ ወደላይ እያየችኝ "ጨካኝ መምህር ነህ እሺ" አለችኝ ። 'እሺ የኔ ጉረኛ ተማሪ' አልኳትና ወደ ውሃው ውስጥ ዘልዬ dive ገባሁ ። ብዙም perfect ስላልሆነች ትንሽ አለማመድኳት ። ለመልመድ ብዙም አልተቸገረችም ። እንደውም ከባለፈው ይልቅ በጣም ተሻሽላ ከኔም ጋር ፉክክር ጀምራለች ። ዕረፍት እየወሰድን እየዋኘን ከአንድ ሰዓት በላይ ቆየን ። "ካሁን በዋላ እንደውም እኔ እራሴ እንዳላለማምድህ" አለችኝ እዛው ውሃ ውስጥ የገንዳውን ጫፍ ግድግዳ ተደግፈን እንደቆምን ። make up ስለማትጠቀም ውሃ ነክቷትም መልኳ እንደዛው ውብ እንደሆነ ነው ያለው ። እንደውም ውሃ ሲነካው ይብስበታል ። እጆቼን በእጆቿ ስትይዘኝ ውሃ ውስጥ ቆሜ ሙቀት ይገለኛል ። መላ ሰውነቴን የሆነ ነገር ውርር ያደርገዋል ። አይኖቿን አይኖቼ ላይ ከጣለች ደግሞ በቃ ልቤ ወጥቼ ከሷ ልብ አጠገብ ካልተቀመጥኩ ይላል ። "እኔን ውሃ ውስጥ አቁመህ ስለምን እያሰብክ ነው ...?" አለችኝና ከሃሳቤ ባነንኩኝ ። 'ስላንቺ ነዋ ፣ ሌላ ስለማን አስባለሁ' ስላት "ስለኔ ምን የኔ ጌታ" ብላኝ ይበልጡኑ ወደኔ ተጠግታ አይን አይኔን ማየቱን ቀጠለች ። የሆነ ነገር ልነግራት እፈልጋለሁ ። ግን ይተናነቀኛል ። አፌ ለመናገር ሲጨናነቅ አይኖቼ አውቀውበት ከንፈሯ ላይ ጣሉኝ ። ያ የማይፋታኝ የቴዲ አፍሮ ዘፈን ፊቴ ላይ ድቅን ሲል ከንፈሬን ከከንፈሯ ጋር አዋሀድኩት ። መቼም ልቀቁኝ የማይል ጣፋጭና ስስ ከንፈር ።

"ሳማት ሳማት አለኝና ቀልቤን ገዛው እንደገና ፣
ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል ከንፈር ድንገት አጉል አርጎኝ ነበር...


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​​🌺የከንቲባው ልጅ🌺
🔥ክፍል 32


"ግንቦት #17,1989 ዓ.ም ከለሊቱ #06 ሰዓት አካባቢ ። ሰማዩ ከሰይጣን በላይ ጠቁሯል ። (ቆይ ግን ሰይጣንን ማንም ሰው ካላየው ፡ መልኩ ጥቁር እንደሆነ በምን አወቅን ፣ ነው ወይስ የማይታይ ነገር ጥቁር ይመስለናል...?) ። ምድርም ያለ ፀሀይ ብርሃን የላትምና የሰማይ ተከታይ ሆናለች ። ከአንዲት እናት በስተቀር ሰፈሩ በሙሉ ፀጥ ረጭ ብሏል ። እናቲቱ ግን እያቃሰተችና እየጮኸች ትገኛለች ። እንዲህም ሆኖ ግን ማንም ሰው አልተረበሸም ። በተቃራኒው ሁሉም ሰው ተጨንቆ ወደላይ አንጋጦ ፀሎት እያደረገ ይገኛል ። በዚያች የጭንቅ ለሊት ሁሉንም ወደ ሳቅ ፣ ደስታና ዕልልታ የቀየረ አንድ ነገር ተፈጠረ ። በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው ወንድ ልጅ ይቺን ምድር በሰላም ተቀላቀለ ። እናቲቱም የልጁን ስም ተስፋዬ ብላ ሰየመችው ። የወደፊት ተስፋዋን እሱ ላይ ጥላለችና" ። ይሄን ታሪክ የስልኬ Note ላይ ፅፌው ስለነበር ፣ ህይወት የልደቴን ቀን ከዛ ላይ አይታ እንዳወቀች ነግራኛለች ። በ #17 ለሊት ስለ ተወለድኩኝ ልደቴን በ #18 ነው የማከብረው ። እና ዛሬ ልደቴ ነው ፤ #22 ዓመት ሞልቶኛል ። (እና ምን ይጠበስ ...) ። ዛሬ እንኳን ጥብስ አይደለም የምፈልገው ። ልደትም አይደል ፣ ለፎቶው ድምቀት ድፎ ዳቦ ፣ ብርቱካን ፣ ሙዝ ፣ ለስላሳ ፣ ፊኛ ፣ ፈንዲሻ እና ግብዳው ሻማ ይሁንልኝ ። እንደውም #21 ዓመት ስላለፍኩኝ አንድ ሳጥን ቢራ ይዛችሁልኝ ኑ ። በነገራችን ላይ በዚህ ዓመት መምረጥ ብቻ አይደለም ፤ መመረጥም እችላለሁ ። እንደውም በቀጣዩ ምርጫ ላይ መሳተፍ እፈልጋለሁ ። በዚሁም እግረ መንገዴን የምርጫ ቅስቀሳ ባደርግ ውስጤ ነበር ። ግን በልደት ቀን ስለ ፖለቲካ አይወራም ። እዛው #MA ሆቴል ምሳ በልተን ፣ ህይወትን ቤቷ ድረስ ሸኘዋትና ጊቢ ውስጥ ስለ ወቅታዊው ችግር ስብሰባ እንዳለና መቅረት እንደሚያስቀጣ ተደውሎ ስለተነገረኝ ለዛው ብዬ ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ገብቻለሁ ። ስብሰባው #08 ሰዓት ተብሎ #10 ሰዓት ተጀመረ ። ስብሰባውን የተጠሩት ሁሉም የጊቢው ተማሪዎች ሲሆኑ ፤ የተገኙት ግን ስብሰባ የሚወዱ ተማሪዎች (አብዛኛው የ Law ተማሪዎች ናቸው...) ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ ባለስልጣናት ፣ የጊቢው አመራር አካላትና የሰሙትን ወሬ ላልሰሙት የሚያወሩ ጋዜጠኞች ናቸው ። የስብሰባው አጀንዳ ፡ ሰሞኑን ጊቢ ውስጥ በተፈጠረው ረብሻ ምክንያት የተቋረጠውን ትምህርት ማስቀጠል ነው ። ይሄን ለማድረግ ደግሞ መጀመሪያ ተጣሉ የተባሉትን ተማሪዎች ማስታረቅ ግድ ነው ። ስብሰባው ላይ ደግሞ የተጣሉት ተማሪዎች አልተገኙም ። ሆኖም ግን በስተመጨረሻ ያልተጣላነውን እኛኑን አስታርቀውን ለሁለት ሳምንታት የተቋረጠው ትምህርት ነገ እንዲጀምር ተወስኖ ስብሰባው ተበተነ ። ምሽት ላይ ጓደኞቼ #ማራኪ club ይዘውኝ ሄደው አንድ ሁለት እያለን ቆንጆ ምሽት አሳልፈን ወደ ዶርም ገባን ። እንኳን ተወለድክልን ያላችሁኝ ቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ፈጣሪ ውለታ መላሽ ያድርገኝ ። ለዚህች ቀን ያደረሰኝ ፈጣሪ ነውና ከሁሉ በላይና በፊት ምስጋናውን እርሱ ይውሰድ ። ጠዋት ነግቶ ቁርስ ሳንበላ ለ #16 ቀን ተቋርጦ የነበረው ትምህርት ተጀመረ ። የልደቴ ቀን ግን ለጊቢው እንደዚህ በረከትን ይዞ ይመጣል ብዬ አላሰብኩም ነበር ። በጊቢው ሰላም መሆን ደስ ቢለኝም ትምህርት በመጀመሩ ግን ከፍቶኛል ። አስቡት እስኪ ፡ #2 ሳምንት ሙሉ ስለ ትምህርት ሳናስብ አሳልፈን በአንዴ ወደ ትምህርት ግቡ ሲባል ትንሽ አይከብድም...? እኔ በበኩሌ ለትምህርት የምንዘጋጅበትን ሌላ ሁለት የዕረፍት ሳምንት ቢሰጠን ባይ ነኝ ።በበላይ አካላትና የሀይማኖት አባቶች በየክፍሉ አስቸኳይ ስብሰባ ተደረገና ስለ ኢትዮጵያዊነት እና ስለ ወደ ፊቷ ኢትዮጵያ እጣ ፋንታ እንድንነጋገር ተደረገ ። እንደ ዕድል ሆኖ እኛ ክፍል የደረሰው የጊቢው president ናቸው ። ስሜን ማን እንደነገሯቸው አላውቅም ፤ "ተስፋዬ እስቲ ኢትዮጵያዊነት ላንተ ምንድነው...?" አሉኝ ከዛ ሁሉ ተማሪዎች እኔን መርጠውኝ ። መጀመሪያ ስሜን ሲጠሩ ደንግጬ ነበር ። ከተነሳሁ በዋላ ግን የኢትዮጵያ አምላክ እረድቶኝ ሰይጣን ይዞት ፀበል እንደ ገባ ሰው መለፍለፍ ጀመርኩኝ ። 'እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም' ብዬ ንግግሬን ስጀምር ሁሉም አፈጠጡብኝ ። 'አይገርማችሁም ፡ እናንተም ኢትዮጵያዊ አይደላችሁም ። በልባችሁ ፡ "አሜሪካዊ ናችሁ በለን" እንደ ምትሉ ተስፋ አደርጋለሁ ። ሁልሽም ኢትዮጵያ ውስጥ ስለተወለድሽ ብቻ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብለሽ የምታስቢ ከሆነ ተሳስተሻል ። ትንሽ እንኳን አናፍርም ...? ፡ ለዚች ክብርት ሀገር ብለው የሞቱ ስንቱ ደግና አንበሳ አባት ፡ ስንቷ ሩህሩና ጀግና እናት በተጠሩባት ፤ እኛ በዘር በሀይማኖት እየተባላን ፡ ከነሱ እኩል ኢትዮጵያዊ ተብለን ስንጠራ ትንሽ እንኳን አይሰቀጥጠንም ...? ፡ እኔ በበኩሌ ስማቸውን ጠርቼ ከማልጨርስና ከማልጠግብ የሀገራችን ባለውለታዎች እኩል ኢትዮጵያዊ ተብዬ መጠራት አልፈልግም ። እስቲ ለዚች ሀገር ሲሉ የሞቱትን ጀግኖች እናስባቸው ። አፄ ቴዎድሮስና በላይ ዘለቀ የሞቱት ለአማራ ክልል ነው ...? ፡ ጀነራል ታደሳ ብሩና ገረሱ ዱኪ የሞቱት ለኦሮሚያ ክልል ይመስላችኋል ...? ፡ አቡነ ጴጥሮስስ የሞቱት ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነው ...? ፡ ነው ወይስ አሚር የሞተው ለእስልምና ይመስላችኋል ...? ። እንደዛ ካሰብባችሁ ተሳስታችኋል ። እነሱ በጊዜያቸው ክልል የሚል ድንበር አልነበራቸውም ። በሀይማኖት መከፋፈል ሀሳቡም አልፈጠረባቸውም ። እነሱና እነሱን የመሰሉ ስንቶቹ ለዚች ክብርት ሀገር ኢትዮጵያ ብለው እንጂ ለዘራቸው አልነበረም ጥብቅናቸው ። ምን ነካን ጎበዝ ...? ፡ ጠላት ከውጪ ሲመጣብን አንድላይ ሆነን እንዳልመከትን ፡ ዛሬ ላይ እርስ በእርስ መጫረስ ምን የሚሉት ጉድ ነው ...! አሁንም ሳስበው ጥላቻው የኛ አይመስለኝም ። እናም ወገኖቼ ፡ የኛን አንድነት የማይፈልጉትን አንድ ላይ ሆነን በፍቅር እንመክታቸው ። ጥፋታችንን የሚፈልጉትን ተቃቅፈን እናሳፍራቸው ። እንደ ክልልና ሀይማኖት ሳይሆን ፡ እንደ ሰው አስበን ኢትዮጵያን ከጥፋት እናድናት ። ያኔ እኔም እናንተም ልክ እንደ ቀደምቶቻችን ኢትዮጵያዊ ተብለን እንጠራለን ። ክልል ሳይሆን ሀገር ስላስረከብናቸው ልጆቻችንም ይኮሩብናል' ብዬ ቁጭ አልኩኝ ። እናንተ ፡ እህህህ የሚለኝ አጣሁ እንጂ እተነትነው የለ እንዴ ...? ። ሁሉም ተራ በተራ የሚሰማቸውን ከተናገሩ በዋላ ፕሬዚዳንቱ "እስቲ ለዚህ ሁሉ ችግር ምክንያቱ ምንድነው ትላለህ ወጣት ተስፋዬ" አሉኝ በድጋሜ ።ይቀጥላል......


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................