የኛ ግጥም
45 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
💐የከንቲባው ልጅ💐
🔥ክፍል 13

.

ከጠዋት እስከ ማታ ቀኑን ሙሉ በልቤ የልደቷን ቀን እያከበርኩ ፡ ድምፄን አጠፋሁ ። ሳልደውልላትና መልዕክት ሳልክላት ምሽቱ ወደ መገባደድ ደረሰ ።..ከምሽቱ #05 ሰአት አከባቢ ከማራኪዬ እንዲህ የሚል txt ግባልኝ ። "የልደቴን ቀን ብዙ የምወዳቸው ሰዎች አክብረውልኝ ደስ ብሎኝ ዋልኩኝ ። ነገር ግን ከሁሉም በላይ አስበልጬ ቦታ የሰጠሁት ልጅ ዝም ብሎ ዋለ ፤ ዝምም" ። እንዲህ ስትለኝ ምን ያክል ልቤን እንደ በላችው ፈጣሪ ያውቃል ። በጣም ነበር ያሳዘነችኝ ። ቢሆንም ግን ምንም አይነት መልስ ሳልሰጣት ያ ቀን አለፈ ። ከወር በዋላ ሁለተኛው የፈተና ቀን ደረሰ ፤ የልደቴ ቀን ። የሚገርምሽ ነገር ጠዋት #12:00 ላይ ነበር "እንኳን ተወለድክልኝ" የሚል መልዕክት መላክ የጀመረችው ። እስከ ማታ ድረስ እኔ ምንም ሳልመልስላት #14 txt ተስፋ ሳትቆርጥ ላከችልኝ ። መጨረሻ ላይ እንዲህ የሚል message ግባልኝ ። "ማራኪዬ ፡ ይኸው #15ኛ txt ላኩልህ ፡ አንተ ግን አንዱንም አልመለስክልኝም ፤ አላሳዝንህም ...?" አለችኝ ። በዚህ txt ልቤ ቢደማም እንደ ምንም ላለመመለስ እራሴን አስጨክኜ ያቺ ቀንም አለፈች ። ከዛም በዋላ በፈተናው ምክንያት txt ብዙም አላወራትም ነበር ። በዚህም ምክንያት ትምህርት እንደ ጨረሰች ክረምት ላይ ወደ ሙገር መጣች ። #3ኛው የፈተና ቀን ። ምን እንደ ተፈጠረ ጠየቀችኝ ። እኔ ግን እንኳን እሱን ልመልስላት ይቅርና በፈተናው መሠረት ጭራሽ ፊት ነሳዋት ። አይኗን እያየሁ መዋሸት ስለ ከበደኝ አንገቴን አቀርቅሬ እንደ ማልፈልጋት act አደረኩ ። ችላ አልኳት ፣ እንደ ድሮው አልስማትም ፣ አላጫውታትም ። ባጠቃላይ የቀደመውን ፍቅሬን ተውኩት ። ይሄን ሁሉ ሳደርግ ግን በውስጤ የደም እምባ እያነባሁ ነበር ። እሷንም ሳያት እንደዛው ነበረች ። ቃል አውጥታ ባትነግረኝም በኔ ልቧ ተሰብሯል ። ትንፋሿን ዋጥ አድርጋ ፡ ለኔ ስሜት ተጨንቃ ምንም እንዳልተጎዳች ታስመስል ነበር ። አብረን ባሳለፍናቸው ቀናት ምንም አይነት የፍቅር ስሜት አላሳየዋትም ነበር ። የመሄጃዋ ቀን ሲደርስ "ማራኪዬ ፡ አንተ ሁሉ ነገሬ ነህ ፤ እኔስ ላንተ ምንድነኝ ...?" የሚል ያላሰብኩትን ድንገተኛ ጥያቄ አቀረበችልኝ ። ሁለት ሀሳብ ውስጥ ገብቼ ነበር ። #1ኛው በፈተናው ህግ መሠረት 'ምኔም እንዳልሆነች act ማድረግ' ሲሆን #2ኛው ደግሞ እውነታውን 'ሁሉ ነገሬ እንደሆነች መናገር' የሚሉት ናቸው ። ፈተናውን ጀምሬ በስተ መጨረሻ ተስፋ መቁረጥ አልፈለኩም ። ከዛን ነበር አይኔን በጨው አጥቤ #3ኛውን ፈተና የተገበርኩት ። አፍ አውጥቼ ምኔም አይደለሽም አላልኳትም ። በዝምታ ብቻ ነበር የመለስኩላት ። ዝምታም መልስ ነው በሚለው ተረዳችኝና ምንም ሳትለኝ ከዱከም ይዛልኝ የመጣችውን ስጦታ ሰጥታኝ ወደ ሀገሯ ተመለሰች ። ስጦታውን እቤት እስክገባ አለማየት ስላላስቻለኝ መንገድ ላይ ነበር የከፈትኩት ። እንዲህ አይነት ስጦታ ከማንም ተሰቶኝ አያውቅም ነበር ። የኔን ስዕል በእንጨት ፍሬም ላይ በሰዓሊ አስላ ሰጠችኝ ። ስለኔ ወቅታዊ ፀባይ መቀየርም በደብዳቤ ፅፋልኝ ነበር ። anyways ከዛን ቀን በዋላ ማራኪዬን አይቻት አላውቅም ፣ ስልኬን አታነሳም ፣ txt አትመልስም ። ስልኳ እንደውም አብዛኛውን ጊዜ አይሰራም ነበር ። በጓደኞቼም ስልክ ስደውል አታነሳም ።
'በቅርብ ጊዜም ላወራት ፈልጌ ነበር ፤ እሷ ግን እኔ መሆኔን ስታውቅ መልስ አትሰጠኝም ። ባጠቃላይ ከኔጋር ስለምንም ነገር ለማውራት ፍቃደኛ አይደለችም ። ሲመስለኝ ረስታኛለች ፤ ወይም ደግሞ እኔን ለመርሳት እየሞከረች ይሆናል ። ለዚህ ሁሉ ምክንያት የሆነው ደግሞ ፈተናው ነበር ። እሷ ደግሞ እኔን ለማናገር ፍቃደኛ ባለመሆኗ ምክንያት ስለ ፈተናው እስካሁን ድረስ ምንም የምታውቀው ነገር የለም ። እንኳን ጊዜ ሰጥታኝ ሁሉንም ነገር ልትሰማኝ ይቅርና ከሰላምታ ውጪ ከኔጋር ምንም ነገር ማውራት አትፈልግም ። ባጠቃላይ ስለኔ ጉዳይ ከኔጋርም ይሁን ከሰዎች ጋር ማውራት እንደ ማትፈልግ ከሷም ከጓደኞቿም ሰምቻለሁ ። ከጓደኞቿ ጋርም ለማውራት ፈልጌ ነበር ፤ ግን ሁሉም እኔን ከመውቀስና ወንዶች ስትባሉ ግን ከማለት ውጪ የኔን እውነታ የሚሰማኝ አላገኘሁም ። በቃ ፈተናውን እንደ ቀላል ነገር አይቼው ፍቅሬን ተነጠኩኝ ። አጠገቧ ሆኜ እውነታውን ባላውቅም ይመስለኛል በኔ ተስፋ ቆርጣለች ወይንም ደግሞ ተስፋ መቁረጥ ትፈልጋለች ። በዚህ ሁሉ መሀል ግን ለአንድም ቀን ማራኪዬን ወቅሻት አላውቅም ። ምክንያቱም ጥፋቱ ሁሉ የኔ ስለነበር ። እሷ ከደሙ ንፁህ ናት ። ባይሆን ግን ትንሽም ቢሆን ቅር ያለኝ ነገር በቀላሉ በኔ ተስፋ መቁረጧ ነበር ። ለአንድም ቀን አስቤም ስለማላውቅ ይሄ ነገሩ አስከፍቶኛል ። እንዲህም ሆኖ ግን በጣም እንደ ጎዳዋት ይሰማኛል ። በኔ ክህደት የተፈፀመባት ስለሚመስላት አይኗ እስኪጠፋ ድረስ እንደ ምታለቅስ አውቃለሁ ። ልቧ ተሰብሮ ከሰዎች ተለይታ ለብዙ ቀናት ብቸኛ እንደ ምትሆን ይታየኛል ። እውነታውን ስታውቅ ግን ምን እንደ ምትለኝ አላውቅም ። "ይቅር" ብላኝ እንደ በፊቱ አብረን መሆን እንጀምር ይሁን ፤ ወይንም ደግሞ "ሁሉም አልፏል ፡ አንዴ ከልቤ አስወጥቼሀለው ፡ ከአሁን በዋላ እኛ የሚባል ነገር የለም" ትለኝ ይሁን አላውቅም ። እኔ እስካሁን ስለሷ ሳወራ በስሟ እንኳን ጠርቻት አላውቅም ። የእሷን ግን እንጃ ፤ እንኳን ማራኪዬ ብላ እኔን መጣራቷ ይቅርና ስለኔ ማሰቧም ጥያቄ ምልክት ውስጥ ነው' ። ከዚህ በላይ ለከንቲባው ልጅ ስለ ማራኪዬ የመተረክ አቅም አልነበረኝም ። 'በጣም ደክሞኛል' አልኳትና ወደ መኝታዬ አመራሁ ። በጣም ከፍቶኛል ፤ በዛላይ ሳልፈልግ እምባዬ እየፈሰሰ አስቸገረኝ ። ብዙም ሳልቆይ እንደ ተገረፈ ህፃን ድምፅ አውጥቼ ማልቀስ ጀመርኩኝ ። ይሄኔ ነበር የከንቲባው ልጅ በፍጥነት ከመኝታዋ ተነስታ አልጋዬ ላይ ወጥታ እቅፍ አድርጋኝ እያባበለችኝ ፣ ግንባሬን እየሳመችኝ ፣ ፀጉሬን ልጅ እያለሁ እናቴ እንደ ምታደርገው በጣቶቿ እየዳበሰችኝ ፣ "እሽሽሽ ..." የሚል ለስላሳ ድምጿን በጆሮዬ ተጠግታ እያሰማችኝ ዝም ያስባለችኝ ። ግን ዝምታዬ በዛው አልፀናም ነበር ። ተነስቼ ምንም የማታውቀው ልጅ ላይ ጮህኩኝ ፣ አለቃቀስኩባት ፣ ማራኪዬ እሷ የሆነች ይመስል 'ለምንድነው የማታዳምጠኝ ፣ ለምንስ ነው እውነታዬን የማትሰማው ...? ፡ እኔኮ ማንም ሰው እንዲያምነኝ አይደለም ፍላጎቴ ። በቃ እውነቱን ብቻ እንዲሰሙ ነው' እያልኳት በሀይል ተናገርኳት ። በሁኔታዬ ብትደናገጥም ለብቻዬ አልተወችኝም ፤ በተቃራኒው ተጠምጥማብኝ በማባበል "እኔ እሰማሀለው ፡ እኔ አምንሀለው የኔ ጌታ" እያለችኝ ከኔጋር ማልቀስ ጀመረች ።

@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................