የኛ ግጥም
44 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 12
.
.
.
.
'በኛ ካምፕ ውስጥ ደግሞ አንድ ታሪኩ ብቻ ነበር ያለው ፤ እሱም ምርጥ ጓደኛዬ ነበር ። ከዛን ልጆች እሱን ጠቁመዋት አገኘችው ። ስታየው እኔ እንዳልሆንኩ አወቀች ። ታሪኩ ደግሞ ከኔጋር ሲገናኝ ስሟንና ከየት እንደመጣች እየጠቆመ የተፈጠረውን ነገረኝ ። ያኔ ነበር እኔን እየፈለገች እንደሆነ የተረዳሁት ። ቀኑን አላውቅም እንጂ እንደ ማገኛት አውቅ ነበር ። ከሁለት ዓመት በዋላ ያቺን ልጅ ድጋሜ አየዋት ። ቆንጅናዋ እንዳለ ነው ፤ ኧረ እንደውም ይበልጥ ተውባ ነበር ። ተገናኘን ፣ ተቃቀፍን ፣ ለብዙ ሰዓት ቁጭ ብለን አወራን ። ሲመሽብን ስልክ ቁጥር ተለዋውጠን ተለያየን ። ከዛን ቀን አንስቶ ወደ ዱከም እስክትመለስ ድረስ በየቀኑ እንገናኝ ነበር ። ሁለታችንም እንደ በፊቱ ዝምተኛ አልነበርንም ። ስለ ብዙ ነገር አወራን ፣ ተጫወትን ፣ ብዙ ቦታ አብረን ዞርን ። በቃ ባጠቃላይ ፊልም ላይ ወይንም ልቦለድ ላይ የምታውቂውን የፍቅር ህይወት አብረን አሳለፍን ። በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የሷን ከንፈር ነበር የሳምኩት ። ወክቱ ክረምት ነበር ፤ የቴዲ አፍሮ "ኢትዮጵያ" አልበም ደግሞ በብዛት ይደመጥ ነበር ። ከሱ አልበም ውስጥ ሁለታችንም "ማራኪዬ" የሚለውን ዘፈን ከቴዲ አፍሮ በላይ ወደድነው ። ልምድ ሆኖብን ሁለታችንም ከዛን በዋላ #ማራኪዬ እያልን መጠራራት ጀመርን ። ማንም ወንድ ቢቀርባት በፍቅር የሚወድቅላት ልጅ ነበረች ። እኔም ወደኩላት ። በጣም ነበር የምንዋደደው ፤ ከምነግርሽ በላይ ። የሚገርምሽ ቀኑን ሙሉ አብረን ውለን ሰለ ማንጠጋገብ ማታ ማታ ደግሞ በስልክ txt እንፃፃፍ ነበር ። እንደውም የሆነ ቀን የተፃፃፍነውን የመልዕክት ብዛት ሳይ #5000 አልፎ ነበር ። እና ማራኪዬ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነበረች ። የኔ አሳቢ ፣ የኔ እናት ፣ የኔ ፍቅር ፣ የኔ ረቡኒ ፣ በቃ ምን ልበልሽ ፡ እሷን ምድር ላይ ያሉ ቃላት አይገልጿትም ። በዚች ምድር ላይ እንደሷ የሚወደኝ ፤ እኔም እንደሷ የምወደው አልነበረኝም ። ፍቅርን ምድር ላይ ባሉት ነገሮች ግለፅልኝ ቢሉኝ #ማራኪዬን ነበር የምጠቁመው ። ያን ጊዜ እሷ የ #10ኛ ክፍል matric ፡ እኔ ደግሞ የ #12ኛ ክፍል entrance ፈተና ወስደን ውጤት የምንጠብቅበት ነበር ። ክረምቱን አብረን በፍቅር ዘመትን ። የመጣችሁ ክረምቱን ዘመድ ጋር ለማሳለፍ ነበርና ክረምቱ ሲገባደድ መሄጃዋ ደርሶ በእምባ ተለያየን ። ውጤት ተለቀቀ ፡ ሁለታችንም አለፍን ፡ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ደረሰኝ ። በስልክ ብቻ በየቀኑ txt እየተፃፃፍን ፡ በሳምንት እየተደዋወልን #8 ወር አለፈ ። ናፍቆታችን ገደቡን ሲያልፍ ቢሾፍቱ መጥቼ እንደማገኛት ቃል ገባሁላት ። በቃሌ መሠረትም ለፋሲካ በዓል ወደ ቤት ስመለስ አንድ ቀን ቀደም ብዬ ከድሬዳዋ ፡ ሸገር ፡ ከዛም ደብረ ዘይት እሷን ላገኛት ሄድኩኝ ። ለሶስተኛ ጊዜ ቢሾፍቱ የሄድኩት ያኔ ነበር ። #27-08-2010 ዓ.ም ። ተገናኘን ፣ በፍቅር ተቃቀፍን ። ስንተያይ እንዴት ደስ እንዳለን ideaw የለሽም ። የሆሳዕና ሳምንት ነበርና የሰራሁላትን የዘንባባ ቀለበት አደረኩላት ። ደብረ ዘይት ላይ አብረን ለ #3 ሰዓታት በፍቅር ሰከርን ። የመጀመሪያው ምሳችንን አብረን በላን ፣ ቢሾፍቱ ሀይቅ ሄደን juice እየጠጣን ተዝናናን ፣ photo ተነሳን ፣ ስለኛ ብዙ ነገር አወራን ፣ ተሳሳምን ፣ ተቃቀፍን ፣ ብቻ ያቺን ቀን በህይወቴ መቼም አልረሳትም ። ስጦታ የአንገት መስቀል አስራልኝ ልባችን እያለቀሰ ተለያየን ። እና አሁን አንገቴ ላይ የምታዪው ይህ መስቀል ማራኪዬ ያን ቀን ያደረገችልኝ ነው' አልኳትና በረጅሙ ተነፈስኩ.....
ምንም ሳትለኝ አልጋው ውስጥ ገብታ ተኛች ። እኔም ከዛን በዋላ አልተናገርኳትም ። እንደ መሸ አልቀረም ፡ ነጋና በጠዋት ተነሳን ። ቁርስ ከበላን በዋላ "እና ደብረ ዘይትን አታስጎበኘኝም ...?" አለችኝ ። 'እሺ' አልኳትና ባቦጋያ ፣ ምሳ ሰዓት ሆራ አርሰዴ ፣ ምሽት ላይ ደግሞ ቢሾፍቱ ሀይቅ ወስጃት ደስ የሚል ቀን አሳለፍን ። ትናንት ማታ በነገርኳት ታሪክ ምክንያት እንደ ከዚህ በፊቱ አትስመኝም ፣ አታቅፈኝም ፣ ሌላው ቢቀር ድንገት አይን ለአይን ስንጋጭ እራሱ አንገቷን ትደፋለች ። ወደ ኩሪፍቱ ተመልሰን እራት ከበላን በዋላ "ማታ ምንም ሳልልህ በመተኛቴ ይቅርታ ። ግን ታሪኩን እንድትጨርስልኝ እፈልጋለሁ" አለችኝ ። እኔም ካቆምኩበት ቀጠልኩላት ። 'እንዳልኩሽ ማራኪዬ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነበረች ። ይሄን ደግሞ የፍቅር ታሪኬን ለሚጠይቀኝ ሁሉ አወራ ነበር ። የሆነ ቀን ግን ታሪኬን ከነገርኳቸው ሰዎች መሀል አንዱ "ስለሷ ስታወራ ከልክ በላይ እርግጠኛ የሆንክ ይመስለኛል ። ግን ተስፍሽ አንድ ነገር ልንገርህ ። ከራስህ ውጪ በማንም እርግጠኛ አትሁን ። ሁሉም ሰው አንተ እንደ ምታስባቸው ላይሆኑ ይችላሉ ። እንደዚህ የምልህ ክፉ ነገር አስቤ አይደለም ። ስለ ልጅቷ ከልክ በላይ የተማመንክባት ስለመሰለኝና አንድ ቀን እንዳትጎዳ ስለፈለኩኝ ነው" አለኝ ። በሱ አስተያየት ምንም አልተሸበርኩም ነበር ። እንደውም 'አንተ ማራኪዬን ስለማታውቃት ነው' አልኩት ። ከዛ በዋላ ነው እንግዲህ ጨዋታው የተጀመረው ። "ስማ ተስፍሽ ፡ እንደ ነገርከኝ ከሆነ ማራኪዬ የምትላት ልጅ ፡ አንተ ምንም ብትሆን ፣ የትም ብትሄድ ፣ ሌላው ይቅርና አንተ ብትተዋት እንኳን የማትተውክ ፣ እስከ እለተ ሞቷ ድረስ የምታፈቅርክ የተለየች ሴት ናት ። ይሄን ያክል ደግሞ በሷ እርግጠኛ ከሆንክ ለምን እኔ የምነግርህን ፈተና አታቀርብላትም ...?" አለኝና ፈተናው ምን እንደሆነ ጠየኩት ። ቀጠለና "ምን መሰለህ ፡ #3 ነገሮችን እንድታደርግ እፈልጋለሁ ። #1ኛው ፡ የልደት ቀኗ ሲደርስ ምንም አይነት txt እንዳትልክላት ፣ እንዳት ደውልላትም ። በዚህም ከሁሉ በላይ አንተን ስለ ምትጠብቅህ በጣም ታዝንብሀለች ። #2ኛው ፡ ያንተ የልደት ቀንም ሲደርስ ፡ ከሷ ለሚመጡልህ የመልካም ምኞት መግለጫ መልስ አትስጥ ። ይሄ ነገርም የንዴት መጠኗን ከፍ ያደርጋል ። #3ኛውና ወሳኙ ደግሞ ፡ ክረምት ክረምት እናንተ ጋር ሙገር እንደ ምትመጣ ነግረኸኛል ። እናም ባሁኑም ክረምት መምጣቷ ስለማይቀር ፡ ያኔ ስትገናኙ ፊት ንሳት ፣ እንደ ማትወዳት act አርግ ፣ ከሷ ጋር በመሆንህም ደስተኛ እንዳልሆንክ አስመስል ። አንተን ብላ መጥታ እንደዛ ስትሆንባት መቼም ምን እንደሚሰማት መገመት አይከብድም ። እውነት እልሀለሁ ተስፍሽ እነዚህን ሶስቱን ነገሮች ተግብረህ ፡ ማራኪክ 'እኔ አልተውህም ፣ እንደዚህ ብትሆንብኝም እወድሃለሁ' የምትልህ ከሆነ she is the best girl in the world" አለኝ ። ሶስቱን ፈተና ብሎ የነገረኝን ስሰማ መጀመሪያ ስቄበት ነበር ። እንደ ቀላል አይቼው ፣ እንደ ምታልፈውም በሙሉ ልቤ ስለተማመንኩኝ ልፈትናት ወሰንኩኝ ። ስለዚህ ጉዳይ ከኔና ከልጁ ውጪ ማንም ሰው አያውቀውም ። ደስ የሚለው ነገር የልደቷ ቀን ያኔ የነበርንበት ወር ውስጥ ነበር ። የመጀመሪያው የፈተና ቀን ደረሰ ፡ የልደቷ ቀን....


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
💐የከንቲባው ልጅ💐
🔥ክፍል 13

.

ከጠዋት እስከ ማታ ቀኑን ሙሉ በልቤ የልደቷን ቀን እያከበርኩ ፡ ድምፄን አጠፋሁ ። ሳልደውልላትና መልዕክት ሳልክላት ምሽቱ ወደ መገባደድ ደረሰ ።..ከምሽቱ #05 ሰአት አከባቢ ከማራኪዬ እንዲህ የሚል txt ግባልኝ ። "የልደቴን ቀን ብዙ የምወዳቸው ሰዎች አክብረውልኝ ደስ ብሎኝ ዋልኩኝ ። ነገር ግን ከሁሉም በላይ አስበልጬ ቦታ የሰጠሁት ልጅ ዝም ብሎ ዋለ ፤ ዝምም" ። እንዲህ ስትለኝ ምን ያክል ልቤን እንደ በላችው ፈጣሪ ያውቃል ። በጣም ነበር ያሳዘነችኝ ። ቢሆንም ግን ምንም አይነት መልስ ሳልሰጣት ያ ቀን አለፈ ። ከወር በዋላ ሁለተኛው የፈተና ቀን ደረሰ ፤ የልደቴ ቀን ። የሚገርምሽ ነገር ጠዋት #12:00 ላይ ነበር "እንኳን ተወለድክልኝ" የሚል መልዕክት መላክ የጀመረችው ። እስከ ማታ ድረስ እኔ ምንም ሳልመልስላት #14 txt ተስፋ ሳትቆርጥ ላከችልኝ ። መጨረሻ ላይ እንዲህ የሚል message ግባልኝ ። "ማራኪዬ ፡ ይኸው #15ኛ txt ላኩልህ ፡ አንተ ግን አንዱንም አልመለስክልኝም ፤ አላሳዝንህም ...?" አለችኝ ። በዚህ txt ልቤ ቢደማም እንደ ምንም ላለመመለስ እራሴን አስጨክኜ ያቺ ቀንም አለፈች ። ከዛም በዋላ በፈተናው ምክንያት txt ብዙም አላወራትም ነበር ። በዚህም ምክንያት ትምህርት እንደ ጨረሰች ክረምት ላይ ወደ ሙገር መጣች ። #3ኛው የፈተና ቀን ። ምን እንደ ተፈጠረ ጠየቀችኝ ። እኔ ግን እንኳን እሱን ልመልስላት ይቅርና በፈተናው መሠረት ጭራሽ ፊት ነሳዋት ። አይኗን እያየሁ መዋሸት ስለ ከበደኝ አንገቴን አቀርቅሬ እንደ ማልፈልጋት act አደረኩ ። ችላ አልኳት ፣ እንደ ድሮው አልስማትም ፣ አላጫውታትም ። ባጠቃላይ የቀደመውን ፍቅሬን ተውኩት ። ይሄን ሁሉ ሳደርግ ግን በውስጤ የደም እምባ እያነባሁ ነበር ። እሷንም ሳያት እንደዛው ነበረች ። ቃል አውጥታ ባትነግረኝም በኔ ልቧ ተሰብሯል ። ትንፋሿን ዋጥ አድርጋ ፡ ለኔ ስሜት ተጨንቃ ምንም እንዳልተጎዳች ታስመስል ነበር ። አብረን ባሳለፍናቸው ቀናት ምንም አይነት የፍቅር ስሜት አላሳየዋትም ነበር ። የመሄጃዋ ቀን ሲደርስ "ማራኪዬ ፡ አንተ ሁሉ ነገሬ ነህ ፤ እኔስ ላንተ ምንድነኝ ...?" የሚል ያላሰብኩትን ድንገተኛ ጥያቄ አቀረበችልኝ ። ሁለት ሀሳብ ውስጥ ገብቼ ነበር ። #1ኛው በፈተናው ህግ መሠረት 'ምኔም እንዳልሆነች act ማድረግ' ሲሆን #2ኛው ደግሞ እውነታውን 'ሁሉ ነገሬ እንደሆነች መናገር' የሚሉት ናቸው ። ፈተናውን ጀምሬ በስተ መጨረሻ ተስፋ መቁረጥ አልፈለኩም ። ከዛን ነበር አይኔን በጨው አጥቤ #3ኛውን ፈተና የተገበርኩት ። አፍ አውጥቼ ምኔም አይደለሽም አላልኳትም ። በዝምታ ብቻ ነበር የመለስኩላት ። ዝምታም መልስ ነው በሚለው ተረዳችኝና ምንም ሳትለኝ ከዱከም ይዛልኝ የመጣችውን ስጦታ ሰጥታኝ ወደ ሀገሯ ተመለሰች ። ስጦታውን እቤት እስክገባ አለማየት ስላላስቻለኝ መንገድ ላይ ነበር የከፈትኩት ። እንዲህ አይነት ስጦታ ከማንም ተሰቶኝ አያውቅም ነበር ። የኔን ስዕል በእንጨት ፍሬም ላይ በሰዓሊ አስላ ሰጠችኝ ። ስለኔ ወቅታዊ ፀባይ መቀየርም በደብዳቤ ፅፋልኝ ነበር ። anyways ከዛን ቀን በዋላ ማራኪዬን አይቻት አላውቅም ፣ ስልኬን አታነሳም ፣ txt አትመልስም ። ስልኳ እንደውም አብዛኛውን ጊዜ አይሰራም ነበር ። በጓደኞቼም ስልክ ስደውል አታነሳም ።
'በቅርብ ጊዜም ላወራት ፈልጌ ነበር ፤ እሷ ግን እኔ መሆኔን ስታውቅ መልስ አትሰጠኝም ። ባጠቃላይ ከኔጋር ስለምንም ነገር ለማውራት ፍቃደኛ አይደለችም ። ሲመስለኝ ረስታኛለች ፤ ወይም ደግሞ እኔን ለመርሳት እየሞከረች ይሆናል ። ለዚህ ሁሉ ምክንያት የሆነው ደግሞ ፈተናው ነበር ። እሷ ደግሞ እኔን ለማናገር ፍቃደኛ ባለመሆኗ ምክንያት ስለ ፈተናው እስካሁን ድረስ ምንም የምታውቀው ነገር የለም ። እንኳን ጊዜ ሰጥታኝ ሁሉንም ነገር ልትሰማኝ ይቅርና ከሰላምታ ውጪ ከኔጋር ምንም ነገር ማውራት አትፈልግም ። ባጠቃላይ ስለኔ ጉዳይ ከኔጋርም ይሁን ከሰዎች ጋር ማውራት እንደ ማትፈልግ ከሷም ከጓደኞቿም ሰምቻለሁ ። ከጓደኞቿ ጋርም ለማውራት ፈልጌ ነበር ፤ ግን ሁሉም እኔን ከመውቀስና ወንዶች ስትባሉ ግን ከማለት ውጪ የኔን እውነታ የሚሰማኝ አላገኘሁም ። በቃ ፈተናውን እንደ ቀላል ነገር አይቼው ፍቅሬን ተነጠኩኝ ። አጠገቧ ሆኜ እውነታውን ባላውቅም ይመስለኛል በኔ ተስፋ ቆርጣለች ወይንም ደግሞ ተስፋ መቁረጥ ትፈልጋለች ። በዚህ ሁሉ መሀል ግን ለአንድም ቀን ማራኪዬን ወቅሻት አላውቅም ። ምክንያቱም ጥፋቱ ሁሉ የኔ ስለነበር ። እሷ ከደሙ ንፁህ ናት ። ባይሆን ግን ትንሽም ቢሆን ቅር ያለኝ ነገር በቀላሉ በኔ ተስፋ መቁረጧ ነበር ። ለአንድም ቀን አስቤም ስለማላውቅ ይሄ ነገሩ አስከፍቶኛል ። እንዲህም ሆኖ ግን በጣም እንደ ጎዳዋት ይሰማኛል ። በኔ ክህደት የተፈፀመባት ስለሚመስላት አይኗ እስኪጠፋ ድረስ እንደ ምታለቅስ አውቃለሁ ። ልቧ ተሰብሮ ከሰዎች ተለይታ ለብዙ ቀናት ብቸኛ እንደ ምትሆን ይታየኛል ። እውነታውን ስታውቅ ግን ምን እንደ ምትለኝ አላውቅም ። "ይቅር" ብላኝ እንደ በፊቱ አብረን መሆን እንጀምር ይሁን ፤ ወይንም ደግሞ "ሁሉም አልፏል ፡ አንዴ ከልቤ አስወጥቼሀለው ፡ ከአሁን በዋላ እኛ የሚባል ነገር የለም" ትለኝ ይሁን አላውቅም ። እኔ እስካሁን ስለሷ ሳወራ በስሟ እንኳን ጠርቻት አላውቅም ። የእሷን ግን እንጃ ፤ እንኳን ማራኪዬ ብላ እኔን መጣራቷ ይቅርና ስለኔ ማሰቧም ጥያቄ ምልክት ውስጥ ነው' ። ከዚህ በላይ ለከንቲባው ልጅ ስለ ማራኪዬ የመተረክ አቅም አልነበረኝም ። 'በጣም ደክሞኛል' አልኳትና ወደ መኝታዬ አመራሁ ። በጣም ከፍቶኛል ፤ በዛላይ ሳልፈልግ እምባዬ እየፈሰሰ አስቸገረኝ ። ብዙም ሳልቆይ እንደ ተገረፈ ህፃን ድምፅ አውጥቼ ማልቀስ ጀመርኩኝ ። ይሄኔ ነበር የከንቲባው ልጅ በፍጥነት ከመኝታዋ ተነስታ አልጋዬ ላይ ወጥታ እቅፍ አድርጋኝ እያባበለችኝ ፣ ግንባሬን እየሳመችኝ ፣ ፀጉሬን ልጅ እያለሁ እናቴ እንደ ምታደርገው በጣቶቿ እየዳበሰችኝ ፣ "እሽሽሽ ..." የሚል ለስላሳ ድምጿን በጆሮዬ ተጠግታ እያሰማችኝ ዝም ያስባለችኝ ። ግን ዝምታዬ በዛው አልፀናም ነበር ። ተነስቼ ምንም የማታውቀው ልጅ ላይ ጮህኩኝ ፣ አለቃቀስኩባት ፣ ማራኪዬ እሷ የሆነች ይመስል 'ለምንድነው የማታዳምጠኝ ፣ ለምንስ ነው እውነታዬን የማትሰማው ...? ፡ እኔኮ ማንም ሰው እንዲያምነኝ አይደለም ፍላጎቴ ። በቃ እውነቱን ብቻ እንዲሰሙ ነው' እያልኳት በሀይል ተናገርኳት ። በሁኔታዬ ብትደናገጥም ለብቻዬ አልተወችኝም ፤ በተቃራኒው ተጠምጥማብኝ በማባበል "እኔ እሰማሀለው ፡ እኔ አምንሀለው የኔ ጌታ" እያለችኝ ከኔጋር ማልቀስ ጀመረች ።

@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​​😘የከንቲባው ልጅ😘
🔥ክፍል 33


ተነሳሁ አፌም ተከፈተ ። 'ለዚህ ሁሉ ነገር ሶስት አካላትን መውቀስ እፈልጋለሁ ። (ጥቅም ባይኖረውም ...😢) ። #1ኛው :- ያው ሁላችንም በስም ብቻ የምናውቀው መንግስት ተብዬው ነው ። ወንጀል በማንኛውም ሁኔታ ፣ ቦታና ፣ ጊዜ ፡ በሆነ ሰው/ቡድን ሊፈፀም ይችላል ። የመንግሥት ዋነኛ ስራው ወንጀል እንዳይፈጸም መከላከል ፤ ካልሆነም ወንጀለኞቹን ይዞ ህግ ፊት ማቅረብ ነው ። ይህን ካላደረገ መንግስት የለም ማለት ነው ። እባክህ መንግስት ሆይ ፡ ከሰማኸኝ በጣም ናፍቀህኛል ፡ ላገኝህ እፈልጋለሁ ። ብቻህን ቢሆን ይመረጣል ስል ሁሉም ባንድነት አሽካኩ ። #2ኛው :- ከሁሉ ደግሞ የገረመኝ ነገር ፡ የሚዲያዎቹ ነው ። "በኮርያ በተቀሰቀሰው የተማሪዎች ግጭት የሁለት ተማሪ ህይወት አልፏል" EBC ። ስንቱ ምስኪን ሀገሩ ላይ እየሞተ እያለ ስለማያገባን ፈረንጅ ይተርክልናል ። ምናለበት እስኪ ብያንስ እንኳን ነፍስ ይማር ቢል ...?😢 ። ነው ወይስ ግዴታ ባለስልጣን ወይንም አርቲስት መሆን አለብን ...? ። ለስሙ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው ። እኔ ግን የመንግስት ቴሌቪዥን ብዬዋለሁ ። እስቲ እውነት የኛ ሚዲያ ከሆኑ "ተማሪዎች ላይ ስቃይ እየደረሰ ነው ፡ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል" ይበሉ ። #3ኛው :- ህዝብ ነው ። ምነው ይህ ህዝብ ለስንቱ እንዳልተሰለፈ ፡ ዛሬ ለተማሪ ሲሆን ዝም አለ ። ለዘይት ፣ ስኳር ፣ አብይ ፣ ኦነግ ፣ ግንቦት #7 ፣ ጃዋር ፣ እንደዛ በየ አደባባዩ እንዳላሽቃበጠ ፡ ምነው ዛሬ የራሱ ልጅ ባደባባይ ሲገደል ፀጥ አለ ...?😥 ። ብያውቁ ሁላቸሁም ተማሪ ሆነው አልፈዋል ። ተማሪዎች ሲገደሉ ፣ ሲሰደዱ ፣ ሲደበደቡ ፣ ሲሰደቡ እያዩ ባልሰማ ዝም ፤ በተቃራኒው ግን ለአንድ ለማይረባ ነገር ብለው #5 ሚሊዮን ሆነው አደባባዩን ይሞሉታል ። እስቲ የተማሪዎች ህመም ከተሰማቸው ለምን "እኔም ተማሪ ነኝ" ብለው አደባባይ አይወጡም ። ለማንኛውም ፡ በዚህ ዘመን ሰው አለኝ ማለት ከንቱ ነው ። መንግስትም ህዝብም ያጣ generation ...😔 ። እንደኔ የዚህ ክፉ ዘመን የዩኒቨርስቲ ተማሪ ለሆናችሁ ተስፋችሁን እግዚአብሔር ብቻ አድርጉ ። "አሁንስ ተስፋዬ ማነው ፡ እግዚአብሔር አይደለምን ...?" አይደል ቅዱሱ መፅሐፍም የሚለው ። ይህን ስናገር ታዛቢ እንጂ ሰሚ እንደሌለኝ እያወኩኝ ነው ። ግን ብያንስ ስለተነፈስኩኝ ቀሎኛል ። እውነቱን ሸሽገህ የህሊና እስር ቤት ከምትገባ ፡ እውነቱን ተናግረህ የመንግስት እስር ቤት ብትገባ ይሻልሀል' ብዬ ስቀመጥ ሁሉም ተማሪዎች በጭብጨባ ክፍሉን አናወጡት ። እኔም 'አመሰግናለሁ ፣ ኧረ አይገባም አመሰግናለሁ' እያልኩ አሽቃበጥኩ ። ወዲያው ግን ግንባሬን የሆነ ነገር ቋ ሲያደርገኝ ደንግጬ ከተቀመጥኩበት ብድግ አልኩኝ ። ከዛን የ Fluid አስተማሪያችን "ምንድነው የምታመሰግነው ...?" አለኝ ኮስተር ብሎ ። ለካ ያን ሁሉ ስብሰባው ላይ ያወራሁት ክፍል ውስጥ ሆኜ ስቃዥና ሳንቀላፋ ነበር ። ውሃ በላኝ ።....

ከህይወት ጋር የልደቴ ቀን ለመጨረሻ ጊዜ ከተያየን እንደ ቀልድ አምስት ቀናት ተቆጠሩ ። በጣም እንደናፈቀችኝ ያወኩት ክፍል ውስጥ ሴት መምህራችን ስታስተምረን መልኳ ወደ ህይወት ፊት ተቀይሮ ፈገግ ብዬ በፍቅር አይን ስመለከታት ተገርማ "ተስፋዬ ምን ፈገግ የሚያስብል ነገር ተገኘ ...?" ስትለኝ ነበር ። ጥቁር ሰሌዳው ላይ ፣ ደብተሬ ላይ ፣ ጠረጴዛ ላይ ፣ ግድግዳ ላይ ፣ በሄድኩበት ሁሉ የምትታየኝ እሷ ብቻ ሆናለች ። ከሷ ጋር ያሳላፍኳቸውን እያንዳንዷን ቅፅበት ሳስታውስ ነፍሴ በደስታ ትፈነድቃለች ። ለሊት ብቻዬን በዶርማችን በር በኩል ሽቅብ ከማያቸው እልፍ አእላፍ ከዋክብት ይልቅ በልቤ ውስጥ የምታንፀባርቀው እሷ ሆናለች ። ከሷ ጋር ሳሳልፍ የተሻሉ ቃላትን ተጠቅሜ ደስ ላላሰኛት እችላለሁ ። ነገር ግን በክንዶቼ መሃል አስገብቻት ፣ ደረቴ ላይ ተለጥፋ ፣ ጆሮዎቼ የሷን ድምፅ ብቻ ሲሰሙ ፣ አይኖቼም እሷኑ ብቻ እያዩ ፣ ከልቤ ሃሳቧን ፣ ጭንቀቷን ፣ ሀዘኗን ፣ ደስታዋን ፣ ሳቅና ሰቀቀንዋን ሁሉ ስካፈላት ከምን ጊዜውም በላይ ስለምትደሰት ፤ ደስታዋ ደስታዬ ሆኖ ከዋለ ካደረ ቀናቶች ተቆጥረዋል ። ከረገጠችው መሬት በላይ በኔ ላይ ዕምነት ኖሯት ሳያት ታስደምመኛለች ። እኔም ልክ እጆቿን ይዤ አይኖቿ

​​ን ስመለከት ብርሃን ይታየኛል ፤ ጉልበት ይኖረኛል ። እራሷ ደካማ ጎኔ ሆኗ እራሷ ታበረታኛለች ። በስልክ በየ ሰዓቱ እናወራለን ። አባቷ ያንኑ ዕለት እሁድ ምሽት ወደ ቤት እንደ ተመለሱና የዛሬ ሳምንት ማለትም ልክ እኔና እሷ በተዋወቅን በወሩ ግንቦት #30 ወደ አሜሪካ እንደ ሚበሩ ነግራኛለች ። ልክ ይሄንን ነገር ለመጀመሪያ ጊዜ ስሰማ ልቤ ለሁለት ስንጥቅ ብሎ ነበር ። ከአካላቶቼ መሃል አንዱ የተቆረጠ ያህል ህመም ተሰማኝ ። የመጨረሻ ውሳኔዬን ነገ እቤታቸው ሄጄ እንዳሳውቃቸው አባቷ ደውለው ነገሩኝ ። በህይወት መንገድ ላይ መመለስ የለም ። ጉዞው ሁሉ ወደፊት ብቻ ነው ። በመንገዴ ውስጥ ብዙ ሰው ላይኖር ይችላል ። እኔን እሱ አያሳስበኝም ። ነገር ግን የሷ አለመኖር ያማል ። የኔ አለም ለመሆን በተቃረበች ማግስት ከተለየችኝ ከአለም ጋር መጣላት ይሆንብኛል ። እሷን በፀሃይ ፋንታ እንደ ምትክ ሆና በተሰጠችኝ በመጨረሻዋ ሰዓት መሄጃዋ ሲደርስ ብርሃን ማጣት ይሆንብኛል ። ትታኝ መሄዷን ሳስብ ፀሃይ ፊቷን አዙራብኝ ፣ ጨለማ የዋጠኝ ያክል ተሰማኝ ። ጨለማ ውስጥ ወደኩኝ ፣ ምንም አይታየኝም ። ጭር ያለ ቦታ ላይ ተጣልኩኝ ፣ ምንም አይሰማኝም ። እልም ያለ በረሃ ውስጥ ነኝ ፣ በናፍቆት ውሃ ጥም ልሞት ነው ። ቀኑን እና ለሊቱን መለየት ከብዶኛል ። አሁንስ ነጋልኝ ስል ተመልሶ ይጨልምብኛል ። እኔ እሷን ካጣሁ እንኳን ቀኑን እራሴንም መርሳቴ አይቀርም ። የኔና የሷ ፍቅር ቀናት ስለተቆጠሩ አይደለም ። ፍቅር የጊዜ ማጠርና መርዘም አይደለም ። ፍቅር ማለት ፡ ያ በማንኛውም አጋጣሚ ፣ በማንኛውም ሁኔታ ፣ በየትኛውም ቦታ ላይ ያሳለፍናት ያቺ ጊዜ ፣ ደቂቃም ትሁን ቅፅበት የማይረሳ ትዝታን ያሳለፍንባት ፣ በልቤ በልቧ የተነጋገርንባት ፣ በደስታ ሰክረን ያሳለፍናት ፣ አዎ እሷ ናት ። ልክ ፀሃይ አለምን ለማብራት እንደ ተፈጠረች ፣ ህይወትም ለመኖር ፣ ዝናቡም ሊዘንብ ፣ አበቦች ሊፈነዱ ፣ ሌሎችም ሌሎችም ለአላማቸው ልክ እንደተፈጠሩ ፣ የኔ መፈጠርም እሷን ለማፍቀር ቢሆንስ እያለ ልቤ ከራሴ ጋር ይሟገቱ ጀመር

@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................