የኛ ግጥም
44 subscribers
2 photos
2 links
#Kehas

#For business

#gitm

#Tarik

#Feta 😁

#Zena😍

#Sak😀

#desta😇
Download Telegram
​የከንቲባው ልጅ

🔥ክፍል 4


.
.
.
ከእንቅልፌ ሳይሆን ከሶፋው ላይ ተነሳሁ ። ደግነቱ እሷም ተነስታ ኩሺና ውስጥ ሽር ጉድ እያለች ነው ። ሲመስለኝ እንቁላል ነገር እየተሰራልኝ ነው ። አፍንጫዬ ነው ሹክ ያለኝ ። ከጥቂት ደቂቃ በዋላ ድሬዳዋ ከመጣሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ልክ እናቴ ወይንም እህቴ ቤት እያለሁ እንደምትለኝ "ቁርስ ቀርቧል" የሚል የድግስ ጥሪ ከጆሮዬ ገባ ። ስላልተኛሁ ፊቴን ልታጠብ ...? አልታጠብ ...? በሚለው ሀሳብ አየተወዛገብኩ በስተመጨረሻ ታጥቤ ወደ ቁርሱ አቀናሁ ። ልክ እንደ ትናንት ማታው ተጎራርሰን ጀመርነው ። (የቤቱ ህግም አይደል ...) እውነት ለመናገር ልጅቷ ባለሞያ ናት ። የምትሰራው ምግብ ልክ እንደሷ ጣፋጭ ነገር ነው ። (እሷን ደግሞ መች ቀመስካት ...?) ምን እንደ ነካን አላውቅም ፡ ሁለታችንም ተስገብግበን ሳልፈልግ ጨረስነው ። ከቁርስ በዋላ ልክ እንደ ትናንቱ ሶፋው ላይ face to face ተቀምጠን መፋጠጥ ጀመርን ። እሷም እንደኔው ብዙም እንዳልተኛች አይኗ ይናገራል ። የግድግዳ ሰዓቱን ዞር ብላ አየችና "ዛሬ እንኳን እንደማታው አትሂድ ብዬ አላስጨንቅህም ። ማታም በዚያ ሰዓት ወተህ በኔ ምክንያት ችግር ላይ እንድትወድቅ ስላልፈለኩ ነበር ። አሁን ግን ነግቷል ፡ ከኔጋር እዚህ ብትቆይ ደስ ይለኛል ፡ መሄድ ከፈለክ ግን አላስጨንቅህም በሩ ክፍት ነው" አለችኝና ተነስታ በሩን ከፈተችው ። ቢሆንም ግን ቅር እያላት እንደሆነ ፊቷ በደምብ ያስታውቃል ። እኔም ተነሳሁና ወደ ተከፈተልኝ በር አመራሁ ። እሷ ደግሞ በሩን እንደከፈተች የበሩን መክፈቻ ሳትለቅ እዛው ቆማ ወደ መሬት አቀርቅራ ታያለች ። በሩጋ እስክደርስ ለመሄድ አስቤ ነበር ፤ ግን እሷን አልፌ የምሄድበትን ጉልበት አጣሁ ። እጇን ከበሩ መዝጊያ ላይ አንስቺ በራሴ እጅ ዘጋሁትና እጇን እንደያስኩ ወደ ሶፋው ተመለስን ። ጎበዝ ተማሪ ባለመሆኔ ዛሬ ገና ኮራሁ ። ጎበዝማ ብሆን ኖሮ ፡ "ኧረ ትምህርት ያመልጠኛል ፡ በዛላይ ብዙ assignment አስቀምጬ ነው የመጣሁት" እላት ነበር ። በዚች ምድር ላይ ካሉት ነገሮች ቁጥር #1 የምጠላው ትምህርትን ነው ። ጥናት አልተደረገም እንጂ በአለማችንም ለትምህርት ጥላቻ ካላቸው ሰዎች መካከል ቁጥር #1 እኔ ልሆን እችላለሁ ። ለትምህርት ብዙም ትኩረት አልሰጥም ። እሱ ላይ ጊዜዬን ሳጠፋ በጣም ያናድደኛል ። በተለይ የዩኒቨርስቲ ትምህርት ፡ final ፈተና ወሩን ሙሉ አንብበህም የማትሰራው ጉድ የንዴቴን መጠን ከፍ ያደርገዋል ። ከተሳካ አቋራጭ መንገድ ይመቸኛል ። እንደዚህ ስላችሁ ደግሞ የምኮርጅ እንዳይመስላችሁ ። ምን በወጣኝና ፤ የሚኮርጅ ጓደኛ አለኝ ፡ ከሱላይ ነው የምሰራው ። በዚች ምድር ላይ ከሰይጣን ውጪ የምጠላው ነገር ስለሌለ ፡ የሚያስጠሉኝን ነገሮች የሰይጣን ማህበርተኛ አድርጌያቸዋለው ። ለምሣሌ በኔ አይን illuminate የሆኑ ነገሮች እነዚህ ናቸው ፦ #1-ትምህርት ፣ #2-ትምህርት ፣ #3-ትምህርት ... ትምህርትን የጠላሁበት ትክክለኛ ምክንያት አላውቅም ። ለነገሩ ስንፍናዬኮ በቂ ምክንያት ይሆናል ። anyways ለጊዜው ትምህርቱን የራስህ ጉዳይ ብዬው ፡ እልጅቷ ቤት ቀርቻለሁ ። ከጥቂት ዝምታ በዋላ "እሺ ወጣት ተስፋዬ ፡ እስኪ ስላንተ ንገረኝ ፡ በትንሹም ቢሆን ስለኔ አውቀህ የሌ ...?" አለችኝ ።

'እንዳልኩሽ ስሜ ተስፋዬ ይባላል ። እናቴ ናት ያወጣችልኝ ። የተወለድኩት ሙገር ቀበሌ ውስጥ በምትገኝ ኩባ ሰፈር በምትባል ቦታ ነው ። ምናልባት ሙገርን በሲሚንቶ ልታውቂያት ትችያለሽ ። (ሙገር ሲሚንቶ ፣ ዳንጎቴ ሲሚንቶ) የትውልድ ሰፈሬ ኩባ የተባለው ፡ ያን ጊዜ ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካን የሰሩት ሰዎች ኩባውያን ስለነበሩ ነው ። ኩባ ሰፈር ደግሞ በፋብሪካው አጥር አጠገብ በታችኛው በኩል የተመሠረተ ሲሆን ፡ ያን ጊዜ የኩባውያን ፡ አሁን ደግሞ የፋብሪካው ሰራተኞችና ቤተሰቦች መኖሪያ ስፍራ ነው ። ሁለተኛ ክፍል እስክደርስ እዛው ነው ጥርሴን ነቅዬ ያደኩት ። #2ኛ ክፍል #2ኛ ሴሚስተር ላይ አባቴ ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ውስጥ የስራ እድገት አገኘና ቤታችንን ከኩባ ሰፈር ወደ ሙገር መኮዳ ቀየርን ። መኮዳ ከኩባ ሰፈር በእግር ከ #30-40 ደቂቃ የሚፈጅ መንገድ ሲሆን በመኪና ደግሞ ከ #5 ደቂቃ አያልፍም ። ሰፈሩም መኮዳ የተባለው በድሮ ጊዜ እዚህ አካባቢ የኦዳ ዛፍ እንደነበር ይነገራል ። ለዛም ነው ሰፈሩ በአፋን ኦሮሞ Muka odaa /ሙከ ኦዳ (የኦዳ ዛፍ) የተባለው ። ከዛን ቀስ በቀስ ስሙ ከልጅ ልጅ ሲያልፍና ሲቆላመጥ መኮዳ ሆኖ ቀረ ። እና እዚህ ድሬዳዋ እስክመጣ ድረስ ለ #10 አመታት እዛው ነው ከቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ጋር ያሳለፍኩት ። መኮዳም ኩባ ሰፈርም ካምፕ ናቸው ። የፋብሪካው ሰራተኞችና ቤተሰቦች ብቻ የሚኖሩበት ሰፈር ። አብዛኛው የሙገር ሰው ግን የሚኖረው ሬጂ በሚባል የሙገር ከተማ ውስጥ ነው ። አስተዳደጌ ያንቺ ተቃራኒ ነው ። እቤት ውስጥ አባቴ ፣ እናቴ ፣ #3ቱ እህቶቼ እና አጎቴ ሆነን ነው የኖርነው ። እንዳንቺ ብቻዬን ለአመታት ይቅርና ለሰዓታትም አሳልፌ አላውቅም ። ቤተሰብ ፣ ዘመድ ፣ ጎረቤት ፣ ጓደኛ ፣ ሁሉንም አለኝ ። ሰፈር መንደሩ ያውቁኛል ፤ እኔም እንደዛው ። ምናልባት እኔና አንቺን የሚያመሳስለን ነገር ቢኖር የሲሚንቶ ሀገር ልጆች መሆናችን ነው ። ለነገሩ ምናችንም ሲሚንቶ አይመስልም ። ከአፈር እንደተሰራን እናስፎግራለን ። ባይሆን ግን ነጮቹ ከሲሚንቶ የተሰሩ ይመስሉኛል ። anyways ብዙም ባያኮራም ፣ ደስ የሚሉ ብዙ ታሪኮችን አሳልፌ አሁን ላይ ደርሻለሁ ። እንደ ምታዪኝ አሁን የግቢ ተማሪ ነኝ ። በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ #2ኛ ዓመት የመካኒካል እንጂኔሪንግ ተማሪ ነኝ' አልኳት እና ብዙ እንዳወራሁ ስለተሰማኝ ዝም አልኩ ። ቀጥላም "ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በመሆንህ ደስተኛ ነህ ...?" አለችኝ ። አኔም 'መጀመሪያ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ እንደደረሰን ስናውቅ በደስታ አብደን ነበር ። ከ #1 ክፍል ውስጥ #10 ተማሪ ነበር አንድላይ እዚህ የደረሰን ። እዛ ሆነን የጠበቅነው ነገርና ፡ እዚህ መጥተን ያየነው ምንም አይገናኝም ። ባጠቃላይ ስለ ድሬ ባጭሩ ሙዚቃዋ ሸወደን ማለት ይቻላል ። anyways አማራጭ ስለሌለኝና "ነገር ሁሉ ለበጎ ናቸው" በሚለው ቃል ስለማምን አሜን ብዬ ተቀብየዋለሁ' አልኳት ። መጠየቅ ትወዳለች መሠለኝ ፡ ጥያቄው ቀጥሏል ። "ይቅርታ ግን ፡ መጠየቅ ይኑርብኝ አይኑርብኝ አላውቅም ። እእእ ... ፍቅረኛ አለህ ...?"

@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል...............
​የከንቲባው ልጅ

🔥ክፍል 5

.
.
.
'የፍቅር ታሪኬን ማወቅ ከፈለግሽ ፡ ፈጣሪ ከፈቀደ አንድ ቀን በሰፊው እነግርሻለሁ ። በአሁኑ ሰዓት ግን ፍቅረኛ የለኝም ። ባይሆን እናንተ ፍቅር ላይ ብዙ ልምድ አላችሁ ይባላል ፡ እንደውም ለምን ያንቺን አትነግሪኝም...?' አልኳትና እንዲህ አለችኝ "ብታምንም ባታምንም ከማንም ጋር የፍቅር ህይወት ኖሮኝ አያውቅም ። እስር ቤት ያለ ሰው ከማን ፍቅር ይይዘዋል ...? ያውም ብቻዋን በአንድ ቤት ውስጥ የታሰረች ነፍስ ። ባይገርምህ ምኞትሽ ምንድነው ብትለኝ ከነፃነት ቀጥሎ ፍቅር እንዲይዘኝ ነው ። እዚህ ቤት ውስጥ ሆኜ ያላየሁት የህንድ ፊልም ፡ ያላነበብኩት የልቦለድ መፅሐፍ የለም ማለት ትችላለህ" ስትለኝ ቤቱን በአይኖቼ መፈተሽ ጀመርኩ ። የመፅሐፍ መደርደሪያው ውስጥ የሀገር መፅሐፍ ተከማችቷል ። TV stand ስርም ብዙ ካሴቶች ይታዩኛል ። ስታወራኝ እምባዋ ይመጣል ፡ ሆድ ይብሳታል ። በሀይልና ቁጭት ስለምታወራ አንዳንዴ ታስፈራለች ። "በዚህ ሰዓት የምፈልገው ፡ በቃ እንደ ማንኛውም ሰው ፡ በነፃነት የፈለኩበት ቦታ ሄጄ ፡ የፈለኩትን ነገር ማድረግ ነው" አለችኝና እምባዋን ዱብ ዱብ አረገች ። ጥሎብኝ እኔ ደግሞ ሴት ልጅ ስታለቅስ ካየሁ ፡ የኔም እምባ ሳይጠሩት ይመጣል ። እንደዛ ስትሆን የማየት አቅሙ ስላልነበረኝ ፡ እቅፍ አረኳትና ለማፅናናት ሞከርኩኝ ። የሀገሬ ሰው ሲተርት "ሴት ልጅ ብቻዋን ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም" ይላል ። እኔ ግን እላችኋለሁ 'ሴትና ወንድ ብቻቸውን ይሆኑ ዘንድ መልካም አይደለም'። ደረቴ ላይ ተለጥፋ ዝም አለች ። ይሄን ጊዜ ሁሉን ነገር ረስታ የሰላም እንቅልፍ የምትተኛ ይመስለኝና እፎይታ ይሰማኛል ። ጠረንዋ ፣ ልብ ትርታዋ ፣ ሀዘኗ ፣ ጭንቀቷ ፣ ሁሉ ነገሯ ወርሶኛል ። ልጅቷ ያጣችው ነገር አንድና አንድ ነው ። እሱም የሰው ፍቅር ብቻ ነው ። ይሄን ለማግኘት ደግሞ መጀመሪያ ልጅቷ ነፃነቷን ማግኘት አለባት ። ሳላስበው በድንገት እንደሚባንን ሰው ከእቅፌ ውስት ብድግ ብላ "ለምን አንጠጣም...?" አለችኝና ወደ ፍሪጁ አመራች ። ከፈተችውና #4 ቢራ ይዛ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠችና ከጎኔ ተቀመጠች ። "አባዬ ቅዳሜና እሁድ እዚህ ሲያሳልፍ ፡ አንድ ሁለት የማለት ልምድ አለው ። እና እንደምታየው ፍሪጅ ውስጥ አንድ #10 የሚሆኑ አሉ ። እኔ እንኳን የሆነ ቀን የቢራን ጣዕም ለማወቅ ብዬ ጠጥቼ ፡ እየመረረኝም ቢሆን አንድ ጠርሙስ እንደምንም ጨርሼ ነበር ፡ ከዛን ቀን ውጪ ጠጥቼ አላውቅም ። ዛሬ ጠጪ ጠጪ ስላሰኘኝና የሚያጣጣኝ ሰው አንተን ስላገኘሁ ነው የጠየኩህ ። ካልደበረህ እንጠጣ ...?" አለችኝ በልመና አይነት ድምፅ ። 'እሺ ግን ሳናበዛ' አልኳትና አንድ ሁለት ማለቱን ጀመርነው ። ልምድ እንደሌላት ታስታውቃለች ። ስትጠጣ ፡ ፊቷ ጭምድድ ይላል ፤ በዛላይ በሆነው ባልሆነው ትስቃለች ። ደግሞ አስሬ "ጠጣ እንጂ" የምትለው ጉድ አለ ። ቀስ በቀስ ለሁለታችንም ሶስተኛው ቢራ ተከፈተ ። "ስማኝማ" እያለች ብዙ የማይገጥሙ ቀልዶችን እየነገረችኝ ልታስቀኝ ጥረት ታደርጋለች ። (እኔ ደግሞ ብዙ ጊዜ ጀማሪ ቀልደኞችን የማበረታታት አባዜ ስላለብኝ ፡ ባያስቅም እስቅላታው ።) አንዴ ደረቴን እየመታች "ሙት እሺ" ስትለኝ ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጥምጥም ስትልብኝ ፡ አራተኛ ቢራ ላይ ደረስን ። አይኖቿ ድብዝዝ ብለዋል ፤ ድምጿም እየሳሳ ሄደ...መላ ሰውነቷ ድክምክም ብሏል ። ባጭሩ ልጅት እራሷን ለመሳት ሶስት ሴኮንድ ነው የሚቀራት ። አይፈረድባትም ፡ ያውም ልምድ የሌላት ልጅ ፡ በዛላይ በዚህ ጠራራ ፀሀይ ። እኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት ቢራ የጠጣሁ እለት ፡ ሌሊቱ እንዴት እንደነጋልኝ ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው ። anyways ልጅቷ አራተኛውን ቢራ ከአንገቱ ላይ እንኳ ዝቅ ሳታደርገው እቅፌ ውስጥ አሸልባለች ። ልብስ እንኳን አልቀየረችም ነበር ፤ ልክ ማታ በሌሊት ልብስ እንደ ተኛች ነው ያለችው ። እቅፌ ውስጥ እንዳለች ተሸክሜያት ከሶፋው ላይ ተነሳሁና ወደ መኝታ ክፍሏ ጉዞ ጀመርኩኝ ። ብዙም አትከብድም ፡ አካሏ በሙሉ በጥንቃቄ የተሰሩ ይመስላሉ ። ማንኛውም ወንድ የሚመኘው አይነት የሰውነት ቅርፅ ያላት ልጅ ናት ። ቅዱሱ መፅሐፍ "ወደ ሴት አይቶ የተመኛት በልቡ አመነዘረባት" ይላል ። (ውሃ በላኝ ማለት ነው ...?) የተኛች መስሎኝ ነበር ፡ ግን ሙሉ በሙሉ እራሷን አልሳተችም ። ሲመስለኝ የሚሆነውን ነገር በቭዥታ መልክ እያየች ነው ። እንደውም ማውራት ጀመረች ። "አንተ ፡ የት አየወሰድከኝ ነው ...? ፡ እእእ ፡ ምን ልታደርገኝ ነው ...?" እያለች በልመና አይነት ድምፅ ሽቅብ ወደላይ እያየችኝ ፡ መልስ ሳልሰጣት መኝታ ክፍሏ ገብቼ አልጋዋ ላይ አስተኛዋት ። በትንሹም ቢሆን እኔም ዞሮብኛል ። እራሴን መቆጣጠር ግን ያን ያክል አይከብደኝም ። ልጅቷ አልጋዋ ላይ ሆና ወደላይ እያየችኝ በሹክሹክታ ማውራቷን አላቆመችም ። "አ ሰ ከ ር ከ ኝ ፡ አ ...? ፡ ምንድነው ሚዘጋክ ...? ፡ አንተን እኮ ነው ማወራው ...! ፡ እንደውም ና እስቲ ወደኔ ቅረብ ፡ ና...!" አለችኝ በእጆቿ ጭምር ። ምን ልትለኝ ይሁን እያልኩ ወደ አልጋው ቀርቤ ፡ ትንሽ እንደ መንበርከክም ብዬ ፡ ጆሮዬን አፏ ላይ ደቀንኩት ። ከትንፋሿ ውጪ ምንም አይነት ድምፅ አይሰማኝም ። ቀና ብዬ ሳያት ሄዳለች ። ደሀ እራሱ እንዲህ ለጥ አይልም ። ከተንበረከኩበት ተነሳሁና ፡ የክፍሏ ግድግዳ ላይ በጀርባዬ ተደግፌ ፡ ልክ እንደ ትናንት ማታው ፡ አትኩሬ እሷኑ ማየት ጀመርኩ ። የከንቲባ ቤት ነኝ ፡ ያውም የሴት ልጁ መኝታ ክፍል ። እኔና እሷ ብቻ ። ሰይጣን ይታይ ይመስል ባይኖቼ ቤቱ ውስጥ መፈለግ ጀመርኩኝ ። ሰይጣን ሆይ ፡ እንዴት እስካሁን ሁለት ሰክረው አንድ መኝታ ቤት ውስጥ ያሉ ወንድና ሴት አግኝተህ ዝም አልክ ...? ነው ወይስ በጉጉት እየጠበከን ነው ...? መኝታ ቤቷ ውስጥ ሰይጣን ሰምቶኝ መልስ ይሰጠኝ ይመስል ጆሮዎቼን አቁሜ እጠብቀዋለሁ ። እሱን ፍለጋ በአይኖቼ ሳማትር ፡ በልጅቷ ራስጌ ግድግዳ ላይ የኢየሱስ ክርስቶስ ስዕል "የሚጠብቀኝ አይተኛም ፡ አያንቀላፋም" ከሚል ጥቅስ ጋር ተዳምሮ ፤ በተቃራኒው ደግሞ በልጅቷ ግርጌ ግድግዳ ላይ ፡ የድንግል ማሪያም ስዕል "አይዞህ ትለኛለች ፡ ድንግል ከነልጇ" ከሚል ግጥም ጋር ተዋሕዶ የተለጠፈውን አየሁ ። በዚህ መሀል ፡ ልጅቷ የማይሰሙ ቃላት እያወጣች መገላበጥ ጀመረች ። ተኝታበት ከነበረው አቅጣጫ ወደ ተቃራኒው ስትገለበጥ ፡ አልብሻት የነበረውን አልጋ ልብስ ከራሷ ላይ ጣለች ። ከወገብ በታች አብዛኛው ሰውነቷ በግልጽ ይታያል ። እግሮቼም ወደ አልጋዋ ጉዞ ጀመሩ ።

@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 8


.
.
.
እጄን ይዛኝ ፡ ወደ ቤት እየወሰደችኝ "እንዴት በዚህ ሰዓት መጣህ ...? ፡ ትምህርት የለም ወይንስ #03:00 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ናፈኩህ ...?" አለችኝ እንደ መሽኮርመም ነገር ሆና ። ስለ ጊቢው ሁኔታ ጓደኛዬ የነገረኝን እንዳለ ነገርኳት ። እሷም እንደኔው በረብሻው ደስተኛ ባትሆንም ትምህርት እስከ ቀጣይ እሮብ ባለመኖሩ በውስጧ እልል እያለች እንደሆነ ያስታውቅባታል ። ለምን እንዲህ አናደርግም "ዛሬ አርብም አይደል ፡ እስከ እሮብ ድረስ #5 ቀን አለን ። እና ይሄን ሁሉ ቀን #1 ቤት ውስጥ ከምንጎለት ፡ ለምን ከዚህ ርቀን የሆነ ቦታ ሄደን ፈታ ብለን አንመለስም ...?" አለችኝ ። አሰብኩበት ፡ ጉዳቱ አልታየኝም ፤ ተስማማሁላት ። በውሳኔው ሁለታችንም ደስተኞች ነን ። "ከበቂ በላይ ገንዘብና መኪና አለን ፡ ግን የት ነው የምንሄደው ...?" የሚል ሀሳብ አነሳች ።
"ብቻ አንቺ ኑሪልኝ ኑሪልኝ
ኑሪልኝ እንጂ ፣
የትም ይመቸኛል የትም
የትም ይመቸኛል የትም" ።
አይነት መልስ ሰጠዋት ። "ለመዝናናት ደብረ ዘይት እና ሀዋሳ አሪፍ እንደሆኑ በቲቪ አይቻለሁና ከሁለቱ አንዱ ቢሆን ደስ ይለኛል" አለችኝ ። እኔም 'ሀዋሳ ሄጄ አላውቅም ፤ ቡሾፍቱ ግን #3 ጊዜ ስለሄድኩኝ እዛ ሳይሻል አይቀርም' ስላት በደስታ ተስማማች ። ነገ በጠዋት ጉዞ ወደ ውቢቷ ደብረ ዘይት ከተማ ። ከባንክ ቤት ለጉዞው ብለን #10 ሺህ ብር አወጣች ። ATM ስላላት ተጨማሪም ካስፈለገን ፡ ባስፈለገን ሰዓት እናወጣለን ብላኛለች ። ምናልባት መንገድ ላይ ረሀብ ከለቀቀብን ብለን ለነገ ምግብ ተባብረን አዘጋጅተናል ። ነጋና ጉዞ በጠዋት ጀመርን ። ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ መካከል የ #512km ርቀት እንዳለ ታፔላ ላይ ተለጥፎ አምብቤያለሁ ፤ ሰዎች ስያወሩም ሰምቻለሁ ። Google ላይ search ሳደርግ ግን #452 km ነው የሚለው ። በዚህም በዚያም በመኪና (ኢትዮ ፣ ዘመን ፣ ገዳ ፣ ሰላም ፣ ወዘተ bus'ኦች) ከድሬ ሸገር ለመድረስ ከ #8 ሰዓት እስከ #9 ሰዓት ይፈጃል ። በባቡር እራሱ ሄደን ነበርና ከሸገር ጠዋት #02:00 ሰዓት ተነስቶ ቀን #10:00 ሰዓት ነው ድሬ የሚደርሰው ። እሱም መብራት ካልጠፋ ነው ፤ ከጠፋ ማታ #03:00 ሰዓትም ሊገባ ይችላል ። ከድሬ ደግሞ ቀን #07:00 ሰዓት ይነሳና ምሽት #03:00 ሰዓት ለቡ ፡ አዲስ አበባ ይገባል ። በፕሌን ደግሞ የ #45 ደቂቃ መንገድ ነው ። እኛ #01:00 ሰዓት ነበር በ Rava #4 መኪና ከድሬ የተነሳው ። ፈጣሪ ካለ እስከ #10:00 ሰዓት ፊንፊኔ እንገባለን ። anyways የከንቲባው ልጅ መኪናዋን አየር ላይ እያከነፈችው ነው ። ቢቻለኝና ስልጣኑ ቢኖረኝ የአምስት ዓመት ስራ ልምድ እፅፍላት ነበር ። በአነዳዷ ስገረም አየችኝ መሠለኝ "አይዞህ እሺ ፡ ከቢሾፍቱ ስንመለስ አለማምድሀለው" አለችኝ ። የድሬ ሸገር asphalt ብዙም ውጣ ውረድ የለውም ። በግራም በቀኝም አልፎ አልፎ ከሚታይ ትናንሽ ሰፈር ውጪ በረሀ ነው ማለት ይቻላል ። አብዛኛው መሬት ሰውም ፣ እንስሳም ፣ እፅዋትም የለውም ። አፈር ብቻ ። ከብዙ ደቂቃ ዝምታ በዋላ ፡ "እስቲ ሶስቴ ደብረ ዘይት የሄድክባቸውን ጊዜያት አስታውሰኝ ...?" አለችኝ ።

'ለመጀመሪያ ጊዜ ደብረ ዘይት ከተማ የሄድኩት #6ኛ ክፍል እያለሁ ነበር ። በወቅቱ scout የሚባል የወጣቶች ህብረት ነበር ። scout ማለት ወጣቶች ከትምህርት ሰዓታቸው ውጪ መጥፎ ቦታዎች እንዳይውሉ ፣ የሀገር ፍቅር እንዲኖራቸው ፣ ወላጆቻቸውን እንዲያከብሩ ፣ በትምህርታቸውም እንዲጠነክሩ የሚያደርግ ምርጥ ማህበር ነው ። ወጣቶች ላይ ትኩረት ያድርግ እንጂ ህፃናትና ጎልማሶችም የማህበሩ አባል መሆን ይችላሉ ። እና ያኔ ነበር ቢሾፍቱን ከጓደኞቼ ጋር ሀ ብዬ የረገጥኩኝ (ሀ እንኳን ያልኩ አይመስለኝም ...) ። እዛ የሚገኙትን አየር ሀይል ተቋምና ባቦጋያ ሀይቅን ጎብኝተን ገባን ። በዓመቱም ድጋሜ በ scout ሄደንና ሆራ አርሰዴንና የወጣቶች ማዕከልን አይተን ፡ ደስ የሚል ጊዜ አሳልፈን ተመለስን ። ለመጀመሪያ ጊዜ በጀልባ ሀይቅ ላይም የተንሳፈፍኩትም ያኔ ነበር ። እንዴት ደስ እንደሚል አጠይቂኝ ። በዛን ጊዜ ሙገር scout በእግረኛ ሰልፍ እንደ ኢትዮጵያ ታዋቂ ነበር ። ብዙ ፕሮግራም ላይ ተሳትፈናል ፣ ብዙ ቦታዎችን ሄደናል ። እንደውም ከአባሎቻችን መካከል አንዱ እድል አግኝቶ አሁን USA ነው ያለው ። አሁን ላይ ግን አባላቱ በትምህርት ምከንያት በየ ዩኒቨርስቲው ስለተበታተኑ ማህበሩ ፈርሷል' አልኳት ትንሽ እንደማዘን ሆኜ ። "እሺ ለሶስተኛ ጊዜስ እንዴት ሄድክ ...?" አለችኝ ። 'ለ #3ኛ ጊዜ እንኳን ደብረ ዘይት የሄድኩበት ምክንያት ለየት ይላል ። ታሪኩም ረዘም ስለሚል እንዳላሰለችሽ ሌላ ጊዜ ልንገርሽ' አልኳትና በረዥሙ ተንፍሼ አየር ወሰድኩኝ ። "የምለቅህ እንዳይመስልህ ፡ ምሳ ከበላን በዋላ ትተነፍሽያታለሽ" አለችኝ እየሳቀች ። "ስማኝማ ፡ ፊትለፊታችን ምንድነው ይሄ ሁሉ መኪናና ሰው...?" አለችኝ ትንሽ እንደ መደንገጥ ነገር ሆና ። 'አይዞሽ አትፍሪ ፡ አሁን አዋሽ ደርሰናል ። በዚህ መንገድ የሚያልፍ ማንኛውም መኪናና እቃ ሳይፈተሽ ንቅንቅ አይልም ። እንደ ኢትዮጵያ ብዙ የኮንትሮባንድ እቃዎች የሚያዙት እዚህ ነው ። ምክንያቱ ደግሞ ህገ ወጥ መሣሪያዎች ፣ ጫማ ፣ ልብስ ፣ electronics ፣ ወዘተ ቁሳቁሶች በውጫሌ በኩል ወደ ድሬዳዋ ስለሚገቡ ነው' አልኳትና መኪናችንን check አርገው ምንም የተለየ ነገር ስላልያዝን ሳያቆዩን ለቀቁን ። አዋሽ የሚሰሩ ፈታሾች ግን የሚሰሩት እንደ ሙዳቸው ነው ። ደስ ሲላቸው ያለሽን controband እቃ እንዳለ ፣ ሲያሻቸው ግማሹን ይወስዱብሻል ። መፈተሽ ሲሰለቻቸው ደግሞ ምንም ነገር ሳያዩ ያሳልፋሉ ። ይሄን ደግሞ ብዙ ጊዜ በዚህ ስናልፍ ታዚቤያለሁ ። የድሬ ሸገር መንገድ ርዝመት ከሙቀቱ ጋር ተዳምሮ በጣም አሰልቺና አድካሚ ነው ። ብዙ ሰዓት ሄደናል ። መተሃራ ለምሳ ወርደን ማታ የሰራነውን take away በልተን ፣ ትንሽ አረፍ ብለን ጉዞ ቀጠልን ። ከመኪናው ቴፕ ላይ የምትከፍታቸው ሙዚቃዎች ያበዱ ናቸው ። ለነገሩ ልጅቷም እብድ ነገር ናት ። እንደኔው የአስቱካ ወዳጅ ናት ። "ጨጨሆ ፡ ጨጨሆ" እያለች ከአስቴር አወቀ በላይ እየጮኸች ሳያት እብደቷ ተጋብቶብኝ እኔም ሙድ ውስጥ ገባሁ ።እንዲህማ ከቀጠልን መኪናዋ አክሮባት መስራቷ ነው ። አሁን ተገለበጠች ፡ አሁን ተፈጠፈጠች እያልኩ ከምሰጋ ብዬ ለትንሽ ደቂቃ መኪናውን አቁመን እብደታችንን እንድንጨርስ ነገርኳት ። አቆመችና "ስማኝማ ፡ ሽንቴ መጣኮ" አለችኝ....


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
💐የከንቲባው ልጅ💐

🔥ክፍል 6


.
.
.
ወደ አልጋዋ ቀረብኩኝ ። ወደ ግራ ዞሬ ቀና ስል የክርስቶስ ስዕል ግድግዳ ላይ ሆኖ አካል ለብሶ ታየኝ ። "ልጄ ሆይ ፡ የሰይጣንን ሀሳብ አትስማ" የሚለኝ ይመስለኛል ። በቀኝ በኩልም እመቤቴ ስጋ ለብሳ "ልጄ ሆይ ፡ ልጄ የሚልህን አድርግ" የምትለኝ ይመስለኛል ። እውነትም የሚጠብቃት አይተኛም ። አልጋ ልብሱን መልሼ አለበስኳትና ክፍሏን ለቅቄ ወጣሁ ። ሳሎን ውስጥ ሆኜ ፡ በሁለት ሀሳብ ከራሴ ጋር እየተሟገትኩ ነው ። አንደኛው ፡ 'እዚህ ትቻት ሄጄ ወደ ጊቢ ብመለስ ምን ትሆናለች...?' የሚለው ሲሆን ፤ ሁለተኛው ደግሞ 'እስክትነቃ ድረስ እዚህ ብቻዬን ብቆይ ምን ሊፈጠር ይችላል...?' የሚለው ነው ። በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆና ልጅቷን ትቼ መሄድ ከብዶኛል ። በዛውም ልክ ደግሞ እዚህ ቤት ብቻዬን መቀመጥም አስፈርቶኛል ። ቆይ ፡ ድንገት አባቷ ቢመጡስ ...? ፡ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ሳስበው ለመሄድ ወሰንኩና ከቤቱ ወጣሁ ። የውጪኛው በር ጋር ስደርስ ግን 'አባቷ ውጭ ሀገር ከሆኑ ፡ ሳያሳውቃት በዚህ ጠራራ ፀሀይ ምን ያስመጣቸዋል ...? ፡ እንደውም ድፍረቱ ከየት እንደመጣ ሳላውቅ ፡ እንደውም ይምጡ ፡ በዛላይ ጥሩ ሰው እንደሆኑ እራሷ ነግራኛለች' የሚለው ሀሳብ መጣልኝና ሀሳቤን ቀይሬ ወደ ቤቱ ተመለስኩ ። እስከ ቀን #10 ሰዓት ብቻዬን ጅዝብ ብዬ ከሶፋው ላይ ሳልንቀሳቀስ ዋልኩኝ ። ደህንነቷን ለማረጋገጥ ብዬ ወደ ክፍሏ ስገባ ፡ እሷ ሌላ አለም ውስጥ ናት ። ማታ ብዙም ስላልተኛች ልቀሰቅሳት አልፈለኩም ። እንዳለችውም ቀን ቀን የመተኛት ልምድ አላት ። እኔን ደግሞ ሲፈጥረኝ ፡ በታሪክ ቀን ቀን መተኛት አልወድም ። (ለዛ ነው ብቻዋን እንድትተኛ የተውኳት ። ቆይ ቆይ ፡ ማታ ቢሆን ምን ልታደርግ ነበር ...😂) ። መንቃትዋ ስለማይቀር ብዬ ኩሺና ገባሁ ። ለሰካራም ፍትፍት መዳኒት እንደሆነ ጭምጭምታ ደርሶኛል ። እሱን ልሰራላት ሽር ጉድ እያልኩኝ ነው ። ለ emergency ተብሎ ድሮ እቤት እያለሁ በእናቴና እህቴ ፍርፍር ፣ እንቁላል ጥብስ ፣ እንቁላል ፍርፍር እና ሽሮ መስራት ስልጠና ተሰቶኝ ነበር ። አፍንጫን የምትሰነጥቅ ቆንጂዬ ሽሮ ፍትፍት ሰርቼ ጨረስኩና #11 ሰዓት አካባቢ ፡ ልጅቷ ክፍለ ገብቼ ቀሰቀስኳት ። ስትነቃ በትንሹም ቢሆን ደንግጣ ነበር ። "አይዞሽ አትፍሪ ፡ እኔ ነኝ ምንም አልተፈጠረም" አልኳትና ተነሳች ። ጭንቅላቷን በደምብ ጭምቅ አርጋ "እራሴ ሊፈነዳ ነው" አለችኝ ። እኔም "እሱን አውቃለሁ ፡ አሁን ፊትሽን ታጠቢ ፡ ከዛን መዳኒቱን እኔ እሰጥሻለሁ" አልኳት ። በራሴ እጅ የሰራዋትን ፍትፍት ሽሮ አጎረስኳትና አድናቆቱን መጠበቅ ጀመርኩ ። ፊቷ ላይ ግን የሚታየኝ የአድናቆት መንፈስ ሳይሆን ፡ የሆነ ጨው በዝቶበት አይነት ነው ። እንደውም "ምን ሆነህ ነው እንደዚህ አይነት ምግብ የምታበላኝ...? ፡ እስቲ ቀምሰህ እየው" ብላኝ አጎረሰችኝ ። እየጣፈጠኝ በልቼ ዋጥኩት ። ከዛን ከት ብላ እየሳቀችብኝ "ወጣቱ ፡ አንተ እራሱ የቤት እመቤት አይደለህ እንዴ ...! ብላኝ ቀልቤን ገፈፈችው ። ጭራሽ "በናትህ ለጊዜው የቤት ሰራተኛዬ ስለሄደችብኝ እዚሁ ቆይና አገልግለኝ" እያለች ታሾፍብኛለች ። ይበዛል ብዬ የሰራሁትን ብቻዋን ለማለት በሚስችል ሁኔታ በልታ ጨረሰችው ። እንደውም ዛሬ ተረኛ እራት የምትሰራው አንተ ነህ የሚል ስሜት ከፊቷ ላይ ይነበባል።
ፍሪጅ ውስጥ ወተት ስለነበር እሱንም ሰጠዋትና በስተመጨረሻ ወደ ቀልቧ ተመለሰች ። እንደውም "የኔ ዶከተር ፡ መዳኒቶችህ ሰርተዋል ፡ ነገር ግን በየእለቱ መቋረጥ የለባቸውም ብዬ አስባለሁ" እያለች ታሾፍብኛለች ። ሳሎን ውስጥ እንደተለመደው ፡ ብቻችን ሶፋ ላይ ቁጭ ብለን መፋጠጥ ጀመርን ። ትኩር ብላ ታየኛለች ፤ እኔም እንደዛው ። ከፊቷ ላይ እንደሚታየኝ ከሆነ በጣም ደስ ብሏታል ። "ስማኝማ" ብላ መናገር ጀመረች ። "እንዴት እስካሁን ብቻህን እዚህ ልትቆይ ቻልክ ...? መሄድ ነበረብህ እያልኩ አይደለም ግን" አለችኝ ። 'ካየሁሽ ሰዓት ጀምሮ ቀልቤን ወስደሽዋል ፡ እራሴን ብቻ አይደለም ፤ ሁሉ ነገሬን አስረስተሽኛል ። ልክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይሽ ነበር ልቤን የጣልኩልሽ ። ብቸኝነትሽ ፣ ሚስኪንነትሽ ፣ ባጠቃላይ ሁለመናሽ ፡ እንኳን ለእንደኔ ቀርቦ ላየሽ ወንድ ይቅርና ፡ በሩቁ አይንሽን ብቻ ካዩሽ ይነበባል ። ደካማ ጎኔን ነው ያገኘሽው ። ልቤን እንዳይመለስ አርገሽ ጠልፈሽዋል ። በቃ ምን እያልኩሽ እንደሆነ ገብቶሻል ፤ አታስጨንቂኝ ። እንደውም ቁርጡን ልንገርሽ ...? ፡ ከዚህ ቤት እግሬን ለሴኮንድ እንኳን የማነሳ አይመስለኝም' እንድልሽ መቼም አጠብቂም አልኳትና አስደነገጥኳት ። "ሙት እሺ ...? ፡ እኔ እኮ የምርህን መስሎኝ በደስታ ላለቅስ ነበር ። እንደውም አሎድህም እሺ ...? ፡ በቃ እንደውም ተጣልተናል አታናግረኝ" አለችኝ እንደ ማኩረፍ ነገር ሆና ። 'እሺ በቃ አንቺን የሚያስከፋ ከሆነማ ውሸቱን እውነት አረግልሻለው' አልኳትና እቅፍ አረኳት ። በጣም መሽቷል ፤ አንድ ሰዓት አልፏል ። "አልቻልኩም እማምላክ ፡ ስቃዬ በረታ ፣
የመከራዬ እለት ፡ እንደምን ሊረታ ፣
ሳለቅስ አነጋለሁ ፡ ሳነባ ውላለሁ ፣
የሚያፅናናኝ የለም ፡ ብቸኛ ሆኛለሁ" ።
መዝሙር ከፍተን አይደለም ፡ የስልኳ ጥሪ ነው ። አባቷ ነው ደዋዩና እንዴት ደስ እንዳላት idea'ው የላቹም ። እኔን እራሱ ሶስቴ ስማኛለች (ጉንጬን) ። በር ላይ እንደቆመና ብዙም እንደማይቆይ ነገራት እና እኔን በጓሮ በኩል ይዛኝ ወጥታ የሆነ ጭልምልም ያለ ቦታ አስቀምጣኝ "እራሴ መጥቼ እወስድሃለሁ ፡ እስከዚያው ግን ከዚህ ንቅንቅ እንዳትል እሺ...?" ብላኝ ከፊትለፊቴ ተሰወረች ። ያለሁበት ቦታ ጊቢ ውስጥ ባይሆን ኖሮ በፍርሀት መሞቴ ነበር ። ጨለማ ነው ፡ በዛላይ ፀጥታው ነፍስን ከስጋ ይለያል ። ስልኬን አውጥቼ ሰዓት ሳይ #01:54 ይላል ። በልቤ ምን እየተባባሉ ይሁን እያልኩ ሳወጣ ሳወርድ ፡ ከ #15 ደቂቃ በዋላ መጣችና ወደ ቤቱ መለሰችኝ ። ከእስር ቤት የተፈታሁ ነበር የመሰለኝ ። 'ለምንድነው ለትንሽ ደቂቃ ብቻ የመጣው ...? ፡ የትስ ጠፍቶ ነበር ለዚህ ሁሉ ቀን ሳይደውል እንኳን ያስጨነቀሽ' አልኳት ። "እሱን የምጠይቅበት ጊዜ አላገኘሁም ። በጣም ናፍቆኝ ስለነበር መሄዱና አለመደወሉ ትዝም አላለኝም ። ባይሆን የመጣበት ጉዳይ ትንሽ አሳስቦኛል ። ምን ምን ወስዶ እንደሄደ ታውቃለህ ...? ፡ የኔን photo ፣ መንጃ ፍቃድ ፣ የትምህርት ማስረጃዎች ፣ በቃ ስለኔ ነክ የሆኑ ማስረጃዎችን እንዳለ ይዟቸው ሄደ ። ለምን ስለው ለሆነ process ነው ፡ ሲያልቅ surprise አረግሻለው አለኝ" ።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
​የከንቲባው ልጅ

🔥ክፍል 7

.
.
.
"ሁሌም እዚህ ሲመጣ ስጦታ ከእጁ አይጠፋም ። የዛሬውን ለየት የሚያደርገው ግን በፊት በፊት እሱ ፊትለፊት ነበር ከፍቼ የማየው ። ዛሬ ግን እሱ የለም ፤ እና በናትህ ስጦታውን ከፍቼ ደስ የሚለኝ ከሆነ እንደ አባቴ ሁንልኝና ጥምጥም ብዬብህ ፡ በጣም እንደ ምወደው ልንገርህ ...?" ብላኝ መልሴን እንኳን ሳታውቅ በካኪ ወረቀት የመጣላትን ስጦታ ከፈተችው ። ወረቀት እና የባንክ ደብተር ነው ። ቅድምያ ለወረቀቱ ሰጠንና ገልጠነው እኔ እንዳነበው ስልጣን ተሰጠኝ ። "የኔ ልጅ ፣ የኔ ስስት ፣ የኔ ህይወት ፡ አንቺን ያገኘሁባትን ያቺን እለት ፡ እስከ ህይወቴ ፍፃሜ ድረስ መቼም አልረሳትም ። ያን ቀን የኔ ልጅ ፡ ደምና እምባ ነበር ከአይኖቼ የፈሰሰው ። ደስታና ሀዘን በተመሳሳይ ሰዓት ገጥመውኝ ፡ አንድ ጊዜ ሳለቅስ ፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ስስቅ ብቻዬን ስሰቃይ ነበር ። በቀኝ እጄ አዲስ ህይወት ይዛ የመጣችልኝ የፈጣሪ ስጦታ አንቺን ይዣለሁ ። በግራዬ በኩል ግን በዚች ምድር ላይ አለኝ ብዬ የምኮራባት የአይኔ ብሌን የእናትሽ አስክሬን ተቀምጧል ። አንቺን አገኘሁ ብዬ ደስታዬን እንኳን ሳልጨርስ ፡ ፍቅሬን አጥቼ ህይወት ጨለመብኝ ። እናትሽ ስትወልድሽ ገና #18 አመቷ ነበር ። በዛላይ ብዙ ደም ፈሷት ስለነበር አቅም አጥታ ህይወቷ አለፈ ። የኔ ልጅ ህይወቴን እናትሽን ያቺ ቀን ብነጠቅም ፡ አንቺን እንደ ምትክ አግኝቻለሁ ። አንቺ ባትኖሪ ምን እንደምሆን አላውቅም ነበር ። ወይ በህይወት የለሁም ፤ ወይም ደግሞ ትርጉም የለሽ ኑሮ ይኖረኝ ይሆናል ። የኔ እናት ፡ በህይወቴ ብዙ አይነት ሰዎችን አይቻለሁ ። ሁሉንም ሰው መጠርጠር አለብሽ እያልኩ አይደለም ። ግን የኔ ልጅ ማንን ማመን እንዳለብሽ ጥንቃቄ አድርጊ ። እስካሁን ድረስ በኔ ምክንያት ከሰዎች ነጥዬሻለው ። በቅርቡ ግን ይሄ ሁሉ ታሪክ ይሆናል ። ትዝ ይልሻል የሆነ ቀን ፡ አንድ ቀን በጣም ደስ የሚያሰኝሽን ነገር አደርግልሻለሁ ያልኩሽን...? ፡ ከምንም በላይ ነፃነትሽን እንደምትፈልጊ አውቃለሁ ። ለእስከአሁኑ እራሱ ተፀፅቻለሁ የኔ ልጅ ። ለምን ለብቻሽ እዚህ እንዳስቀመጥኩሽም ወይ አንድ ቀን እነግርሽ ይሆናል ፤ ወይም ደግሞ ህይወት እራሷ ታስተምርሽ ይሆናል ። ለማንኛውም በቅርቡ ነፃ አወጣሻለሁ ። ይሄን ሳምንት ብቻ ስጪኝ ። ቀጣይ ሳምንት እመጣና ሁሉም ነገር ሰላም ይሆናል ። ውዱ አባትሽ" ። ከደስታ ብዛት የተነሳ ዘላብኝ ነበር የሳመችኝ ። እኔም ደስ ስላላት ብቻ ደስ ብሎኛል ። ሁለታችንም ሶፋ ላይ ቁጭ ብለን እየተያየን እያለ ፡ ድምፅ ሳታወጣ እምባዋ መፍሰስ ጀመረ ። እንደ ጉድ ይፈሳል ። ትንሽ ቆይታ ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች ። ይሄኔ ነበር second እንኳን ሳላባክን እቅፌ ውስጥ ያስገባዋት ። 'እሽሽሽ ፡ በቃ ፡ በቃ' እያልኳት እንደምንም ብዬ ለቅሶዋን አስቆምኩኝ ። አንዳንዴ ለብዙ ጊዜያት በናፍቆት ስንጠብው የነበረውን ነገር ስናገኝ በደስታ እናለቅሳለን ። አኛ በነፃ ያገኘነውና ምንም የማይመስለን ነፃነት ለሷ የስንት አመት ምኞቷ ነው ። ለብዙ ደቂቃዎች እቅፌ ውስጥ እንዳለች ለኛ ለሰዎች በነፃ ተሰጥተውን ፡ እኛ ግን አጠቃቀሙን ሳናውቅበት ስላጣናቸው እንዲሁም በሰዎች ምክንያት ስለተነፈግናቸው ነገሮች እያሰብኩ አሳለፍኩ ። በጣም ስለመሸ ተነሽና ተኚ ልላት ስል ፡ እሷ ለካ በእንቅልፍ አለም ተወስዳለች ። ተሸክሜያት ወደ መኝታ ክፍሏ አመራሁ ።

ከእንቅልፌ ስነቃ #01:00 ሰዓት ሆኖ ነበር ። ሶፋ ላይ ነው ያደርኩት ። የከንቲባው ልጅ ቀድማኝ ተነስታ ቆንጆ ቁርስ ሰርታ ደስ ብሎን በላን ። በእቅዴ መሠረት ወደ ጊቢ ለመመለስ ተነሳሁ ። እስከማውቀው ሰፈር ድረስ በመኪናዋ ሸኝታኝ ፡ ስልክ ቁጥር ተለዋውጠን ተመለሰች ። በመሄዴ እንደ ደበራት ታስታውቃለች ። እኔም ግድ ሆኖብኝ እንጂ መሄዱን አልፈለኩም ። ስለሷና ስለ አጋጣሚያችን እያሰብኩ ጉዞዬን ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ አደረኩ ። በሀሳብ ርቄ መሄዴን ያወኩት ID card ሳላሳይ የጊቢውን በር ሳልፍ ጥበቃው በስድብ ሲወርድብኝ ነበር ። እንዴት እንደደነገጥኩ ። ቆሌዬን ነው የገፈፈው ። (ቆሌ ግን ምንድነው ...🤔) ፡ ይቅርታ ጠይቄ ID አሳይቼ ወደ ዶርም አቀናሁ ። የዶርም ልጆች በመርዶ ነበር የጠበቁኝ ። "ባክህ ትናንት ጊቢው war ሆኖ ነበር የዋለው ። መጀመሪያ ጠዋት አካባቢ ተማሪዎች ከቤተ ክርስቲያን ወደ ጊቢ ሲመለሱ የለበሱት t-shirt የመስቀል ስዕል ነበረው ። (ጊቢ ውስጥ ሀይማኖታዊና ፖለቲካዊ ነክ ልብሶች መልበስ ክልክል ነው) ። በዚህ ምክንያት ተማሪዎቹ ከፌዴራል ጋር የአትገቡም እንገባለን ፀብ ውስጥ ገቡ ። በዚህ መሀል አንዱ ተማሪ አንዱን ፌደራል በድንጋይ ግንባሩን ይለዋል ። ከዛን ፌደራሎቹ ተናደው ጊቢ ውስጥ ያገኙትን ተማሪ እያባረሩ መደብደብ ጀመሩ ። እኛን እራሱ ለምሳ ስንወጣ እግዚአብሔር አተረፈን እንጂ ረግጠውን ነበር ። ይህ የሆነው እንግዲህ ከ #04:00 - #06:00 ሰዓት አካባቢ ነው ። ከዛን #10:00 ሰዓት ላይ ደግሞ ጊቢ ውስጥ GC cup final እግር ኳስ ነበር ። እሱም ተጀምሮ ብዙም ሳይቆይ ደጋፊዎች ለ #2 ተከፍለው ድብድብ ጀመሩ ። ያንዱ ደጋፊ ከሌላኛው መስሎክ ነው ...? ፡ አይደለም ፡ የብሔር ግጭት ነው ። turk/ኦሮ vs Wolfsburg/ማራ ። የሁለቱም ብሔር ተፋላሚዎች ያገኙትን ነገር እየተወራወሩ ፡ አብዛኛው ተማሪ ደግሞ እግሬ አውጪኝ እያለን እንደምንም ዶርም ገባን" ሲለኝ ፡ በሆዴ 'አይ ጎረቤት ሀገር ኢትዮጵያ' ብዬ ሳልጨርስ ፡ "በዚሁ ያበቃ መስሎክ ነው ...?" ብሎ የቀረውን ቀጠለልኝ ። "ማታ ላይ የስታዲየሙ ክፍል ሁለት ጦርነት ቀጠለ ። በብሔር ተከፋፍለው ጭራሽ ዶርም ለዶርም እየዞሩ መከሻከሽ ይጀምራሉ ። ብዙ ተማሪዎች ከተጎዱ በዋላ ፌደራል መጣና #5 ጊዜ ወደላይ ተኩሶ በታተናቸውና ወደ መጡበት ተመለሱ" ብሎ ትረካውን አጠቃለለልኝ ። history መፃፍ የሚያነብልኝ ነበር የመሰለኝ ። እና ቀጣይ ምን ሊሆን ነው ብዬ ስጠይቀው "ተማሪዎች ቀጣይ ሳምንት ለ #3 ተከታታይ ቀናት class አንገባም ብለዋል" አለኝ ። እንዴት ደስ እንዳለኝ ideaw የላችሁም ። ደስ ያለኝ በረብሻው ምከንያት አይደለም ፤ ትምህርት ስለሌለ እንጂ ። ቀኔ ብሩህ እንዲሆን ትምህርት ከሌለ ብቻ ይበቃኛል ። ከሱ በላይ ደስታ የሚሰጠኝ ነገር ያለም አይመስለኝም ። ሻዎር ወስጄ ፣ ልብሴን ቀይሬ ፡ አዲስ ነገር ካለ ደውለው እንዲያሳውቁኝ ለዶርሜ ልጆች ነግሬያቸው ወደ ከንቲባው ልጅ ለመሄድ መንገድ ጀመርኩኝ ። መንገዱ እንዳልጠፋብኝ ያወኩት በሩ ጋር ስደርስ ነበር ። ምናልባት እቤት ከመጣህ ደውልልኝ እንጂ አታንኳኳ እሺ ፡ ብላኝ ስለነበር ፤ ደውዬ ደጃፏ ላይ እንደቆምኩ ነገርኳት ። ደቂቃ ሳታባክን በሩን ከፍታልኝ ፡ በደስታ ተጠመጠመችብኝ ።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል..................
​የከንቲባው ልጅ

🔥ክፍል 10


.
.
.
የሆነ ነገር ወዳልሆነ ነገር ሊመራክ ከሆነ ፡ ማድረግ ያለብህ ከሆነ ነገር መራቅ ነው ። አልጋ ልብሱን አልብሻት ወደ አልጋዬ ተመልሼ ተኛሁ ። ጠዋት ነግቶ ከእንቅልፋችን ስንነቃ ፡ #03 ሰዓት አልፎ ነበር ። እዛው ካለንበት ሆቴል ቆንጆ ቁርስ በልተን ፡ ያለብንን የ #1 ለሊት የቤት ኪራይ ከፍለን ወደ ቡቲክ አመራን ። ውቢቷ ቢሾፍቱ ላይ ፈክተን የምናበራበትን ልብስ ገዝተን #05:30 ላይ ጉዞአችንን ወደዛው አደረግን ። ለሸገር ቅርብ ስለሆነች ብዙም ደቂቃ አልፈጀብንም ። ኩሪፍቱ ሪዞርት ከበር ላይ በክብር ተቀበሉን ። የምንቆይበት ክፍል ይዘን ፈታ ለማለት ትጥቃችንን አሟልተን ወደ መዋኛ ገንዳ አመራን ። ዋና እንደማትችል ጠጋ ብላ በጆሮዬ ነገረችኝ ። እኔም ልክ እሷ እንደነገረችኝ ፈራ ተባ እያልኩ በጆሮዋ እንደማልችል ነገርኳት ። በድንጋጤ አየችኝና "እና ምን ልናደርግ ነው የመጣነው ...? ፡ እኔ ደግሞ ምትችል መስሎኝ አንተን ተስፋ ማድረጌ" አለችኝ አኩርፋ ። ከዛን ሳኩባትና 'ስቀልድ ነው ባክሽ ፡ ዶልፊን እራሱ ጉልበቴ ስር ቁጭ ብሎ ነው የተማረው' አልኳት ። (ዶልፊን ግን ቁጭ ማለት ይችላል እንዴ ...) ። "ሂድ ፡ ጉረኛ" አለችኝና ትከሻዬን በፍቅር መታችኝ ። እኔ ለክባድ ብዬ ተከርብቼ ውሃው ውስጥ ገባሁ ። እሷ ግን ውሃ ነክታ አታውቅም መሠለኝ በስንት ልመና በዳዴ ገባች ። ለመዋኘት ገብቼ አሰልጣኝ ሆኜ አረፍኩ ። ያን ያክል እንኳን አላስቸገረችኝም ። ነገሮችን በቀላሉ የመያዝ ልዩ ችሎታ አላት ። ዋና የለመድኩት እንዲህ ባማረ ገንዳ ሳይሆን እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወንዝ ውስጥ ነበር ። እየዋኘሁ ፣ እያለማመድኳት ፣ እያረፍን ፣ በድጋሜ ያሁኑን step እየደገምን ከአንድ ሰዓት በላይ ቆየን ። አይን አይኔን እያየች "አስቸገርኩህ አይደል ...? ፡ በቃ የመጨረሻ አንድ ዙር አለማምደኝና ይብቃን" አለችኝ ። ሁለቱ እጆቼን ውሃው ውስጥ እንደ ምንጣፍ ዘረጋሁላት ። በሆዷና ታፋዋ እጆቼ ላይ ተኝታ በእጆቿ ደግሞ ውሃውን ወደ ዋላዋ እየገፋች ወደ ፊት ትመነጠቃለች ። እኔም ከጎኗ ሆኜ እከተላታለሁ ። እንደዛ እያደረገን የገንዳው ጫፍ ላይ ደረስን ። ከእጆቼ ላይ ወርዳ እዛው ውሃው ውስጥ በኔ ፊትለፊት ቆመችና አይን ለአይን ተጋጨን ። ውበቷ እንዴት እንደ ሚያስደነግጥ ideaw የላቹም ። አላወቁም እንጂ ሴቶቻችን የሚያምሩት በሜካፕ ሳይሆን በተፈጥሮአቸው ነው ። በዋናው ውሃ ታጥባ ኩልል ብላ ቆማ ስታየኝ ፈዘዝኩኝ ። በጣም ተቀራርበናል ። እንደውም ንፋስ በመሃላችን ለማለፍ ፈልጎ ሲታገለን ይሰማኛል ። አይኖቼ ከንፈሯ ላይ ደርቀው ቀሩ ። እሷም እንደኔው በአይኖቿ ከንፈሬ አካባቢ እየሾፈችኝ ነው ። ወደ ከንፈሬ በጣም ቀረበች ። ከንፈሯ እንኳን እሁድ ተገኝቶ ፡ እሮብንና አርብን እራሱ ያስገድፋሉ ። የሁለታችንም ስሜት እናታችን ላይ ሲወጣ ተጎራረስን ። ከንፈሯ ከከንፈሬ ፣ ትንፋሿ ከትንፋሼ ተዳመረ ። የኔን ትንፋሽ ወስዳ የሷን ለገሰችኝ ። ትንፋሿ ይሞቃል ፤ ከንፈሯ ይጣፍጣል ። ለብዙ ሴኮንዶች ከንፈር ለከንፈር ተገጣጥመን ፡ የአለምን አየር ንቀን ውስጣችን ያለውን ተለጋግሰን ዋና ገንዳው ውስጥ ከቆየን በዋላ ከንፈራችን ተላቀቀ ፡ አይናችንም ተከፈተ ። ትንሽ እንደ መተፋፈር ሆነን ከውሃው ውስጥ ወጣን ። በርዷት ነው መሠለኝ መንሰፍሰፍ ጀመረች ። አሳዘነችኝና ፎጣ አልብሻት ተሸከምኳትና ወደ ክፍላችን ጉዞ ጀመርኩኝ ።
እሷን መሸከም ለኔ ብርቄም ድንቄም አይደለም ። ሶፋ ላይ በተኛችና በሰከረች ቁጥር እስከ መኝታ ክፍሏ የማድረስ የሁለት ቀን ስራ ልምድ አለኝ ። የዛሬው ግን ለየት ይላል ። አልሰከረችም ፣ አልተኛችም ፣ እራሷን አልሳተችም ፣ አይኖቿ አልተከደኑም ፣ ወዘተ ። ክፍላችንን እንደምንም በአንድ እጄ ከፍቼ ገባንና መልሼ በእግሬ ዘግቼው አልጋው ላይ ቀስ ብዬ አስተኛዋት ። አይኗን ቁልጭ ቁልጭ እያደረገች ወደላይ በስስት ታየኛለች ። እኔም ወደታች እንደዛው ። አንዲት ቃል ሳናወጣ በአይኖቻችን ብቻ እናወራለን ። ከዛን እጆቿን አንገቴ ላይ ጠምጥማ ወደራሷ ጎተተችኝና ድጋሜ ከንፈሮቻችን ህብረት ፈጠሩ ። ፎጣውን ከላዩዋ ላይ ወርውራ አልጋው ላይ ጣለችኝ ። ሁለታችንም ከዋና ገንዳው እንደ ወጣን ፡ እኔ ከላይ ራቁቴን ፡ ከስር ደግሞ በዋናው ቁምጣ ፤ እሷ ደግሞ ከላይ ጡት ማስያዣና ከስር በዋናው ፓንት ነው ያለነው ። ቅድም ከውሃው ስንወጣ በርዷት እንደዛ እንዳል ተንዘፈዘፈች ፡ አሁን ላይ ግን ገላዋ በሙሉ እንደ እሳት እየፈጀኝ ይገኛል ። አንገቷ ስር ገብቼ ስስማት ፡ አይኖቿን ጨፍና ፣ ትንፋሿን ዋጥ አድርጋ ፣ መልሳ ደግሞ በሀይል ትተነፍሳለች ። (አንገቷ ስር ከገባህ ፡ አይኗን ስትጨፍን እንዴት አየህ ...) ። ዛሬም እንደ በፊቱ 'ሴትና ወንድ ብቻቸውን ይሆኑ ዘንድ መልካም አይደለም' አልኩ ለራሴ ። ምን እያደረግን ነው ...? ፡ እዚህ ድረስ ለምን መጣን ...? ፡ ፈታ ማለት ምን ማለት ነው ...? ፡ አልኩኝ ለራሴ ። ከሀሳቤ ነቃሁ ፡ ከአንገቷ ምሽግ ወጣሁ ፡ ከአልጋዋ ላይ ተነሳሁ ፡ ወደ ራሴ አልጋ ሄድኩ ፡ ወደ ራሴም ተመለስኩ ። እሷም ግራ በመጋባትና በመናደድ አይነት ስሜት ከተኛችበት ቀና ብላ ታየኛለች ። የሆነ ነገር ልትለኝ ስትል በራችን ተንኳኳ ። እኔ እከፍታለሁ አልኳትና ከላይ ሸሚዝ ለብሼ ከፈትኩኝ ። አስተናጋጅ ነበር እና "የምትፈልጉት ነገር ካለ ማዘዝ ይቻላል" አለኝ በክብር እጅ እየነሳኝ ። እኔም 'ትንሽ ርቦናልና ምግብ ብናገኝ ደስ ይለናል' አልኩት ። እሱም "ከፈለጋችሁ እዚህ ፡ ፍቃዳችሁ ከሆነም ደስ የሚል ቦታ እወስዳችሁና እዛ ትበላላችሁ" አለኝ ። 'አይ ፡ ላሁኑ እዚህ እንበላለን ፤ ባይሆን ደስ የሚለውን ቦታ ማታ ትወስደናለህ' አልኩትና ሄደ ። #08 ሰዓት አልፏል ። አኩርፋኝ ቢሆንም አስተናጋጁ ያመጣልንን ምግብ እንደ ተለመደው ለራሷ ሳትበላ መጀመሪያ አጎረሰችኝ ። እኔም አጎረስኳትና ትንሽ በልተን ተውነው ። ከበላን በዋላም ሁለታችንም በአንድ ቤት ውስጥ ሆነን ሳናወራ ጀምበር እየታዘበችን ወደ ቤቷ ገባች ። ላወራት ብዬ ስነሳ በራችን ድጋሜ ተንኳኳ ። ስከፍት የቅድሙ አስተናጋጅ ነበርና ቅድም ወዳለኝ ቦታ ሊወስደን እንደ መጣ ነገረኝ ። #10 ደቂቃ ስጠን ብዬው ፡ ተመልሼ ፈራ ተባ እያልኩ ልጅቷን ቀሰቀስኳት ። 'ተነሽና ልብስሽን ቀይሪ ፡ ወደ ሆነ ቦታ እንሄዳለን' አልኳት ። አልተቃወመችኝም ፡ ልትቀይር ወደ ውስጥ ገባች ። ከሸገር የገዛነውን ልብስ አውጥቼ ለበስኩትና እሷ እስክትጨርስ መጠበቅ ጀመርኩኝ ። በዛ ውበቷ ላይ ቅድም የገዛነውን ልብስ እሷ ላይ ስስለው ፡ በቃ ጨረቃ እራሷ በአካል መጥታ የምታገኘኝ መሠለኝ ። ልጅቷ ከገባችበት ቀይራ ወጣች ።
"ደምቀሽ ስትወጪ ፡ ደምቀሽ ስትወጪ ፣
ደምቀሽ ስትወጪ ፡ ጨረቃ አፈረች" ።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
💐የከንቲባው ልጅ💐

🔥ክፍል 9


.
.
.
ስትሸና ያው እኔን ማፈሯ አይቀርም ብዬ እንድትከለል ፡ ጫካ እንደሌለ እያወኩ ለወጉ በአይኔ መፈለግ ጀመርኩኝ ። የድሬ ሸገር መንገድ ዳር ላይ መደበቅያ ጫካ ከመፈልግ ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዘረኝነትን ማስቆም ይቀላል ። ለነገሩ ሽንት ለመሽናት ጫካው አስፈላጊ አይመስለኝም ። ብዙ ጊዜ መንገድ ስንሄድ ሽንት ሲመጣብን ለዛፎቹ አስበን ይመስል ወደ ጫካ እንሮጣለን ። ከሰው ለመደበቅ ነው እኮ ... ። በነ ጦጢት እየተሾፈን እንደሆነ ማን በነገረን ። anyways ጫካ ስላጣን በመኪናው ተከልላ ሸንታለች ። እኔኮ ግርም የሚለኝ ሰው ሲሸና ጠብቆ ሽንቴ የሚመጣው ጉድ ነው ። ውሃ ስለማልጠጣ ሽንት አዘውትሮ የመሽናት ልምድ የለኝም ። (መሽናቴ ካልቀረ ምን አስጠጣኝ ...) ። #08:00 ሰዓት አልፏል ። አዲስ አበባ ለመግባት በግምት #2 ሰዓት ይቀረናል ። ሸገር ለ #1 ቀን ማደር ስለፈለግን እንጂ ቀጥታ ቢሾፍቱ መሄድ አላቃተንም ። ከስንት ድካም በዋላ ልክ #09:42 ደቂቃ ላይ በአቂቃ ቃሊቲ በኩል አዲስ አበባ ገባን ። መንገዶች ሁሉ በመኪናና ሰዎች ተሸፍኗል ። እንደምንም ክፍት መንገድ ባየን ቁጥር እየሾለክን ቦሌ ካንዱ ሆቴል ጎራ ብለን #1 ክፍል ያዝን ። በጣም ደክሞን ስለነበር ሁለታችንም ሻዎር ገባን (አንድላይ አይደለም ፡ ብቻ ለብቻ ነው ደግሞ...) ። እንግዲህ ዛሬን ሸገር ላይ ፍልስስ ልንል ነው ። አዲስ አበባ እንደ ድሬ አይደለችም ። የሰው ብዛት ፣ የመኪናው ጋጋታ ፣ የህንፃዎቹ ብዛትና ውበት ፣ የከተማው ስፋት ፣ ባጠቃላይ ሸገር እንደ ድሬ ቶሎ ምትለመድ አይነት አይደለችም ። እዛው ከያዝነው ሆቴል እራት በልተን ፡ ወይን እየጠጣን ስሟን ለመምሰል ሌት ተቀን ደፋ ቀና የምትለዋን ከተማ ከላይኛው ፎቅ ቁልቁል ወደታች እያየናት ነው ። ሆቴሉ ግሩም ነው ፤ ከላይ በሁሉም አቅጣጫ ከተማዋን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ። ምሽት ላይ ከላይ ስትታይ ስሟን ትመሰላለች ። የከንቲባው ልጅ "ወይ አዲስ አበባ" እያለች ትገረማለች ። ከዛን ወደኔ ዙራ "ስማኝማ ፡ ፈታ ልንል ነው አይደል ይሄን ሁሉ ርቀት አቋርጠን የመጣነው ...?" አለችኝ ። አዎ ስላት "እንደዛ ከሆነ ፡ በናትህ ፡ ስወድህ ፡ night club ውሰደኝ" አለችኝ ። "ጀማሪ እረኛ ፡ ከብት አያስተኛ" ይለዋል የሀገሬ ሰው ። ልጅቷ እቤት ሆና በፊልም ያየችውን ነገር ባካል ማየትና ማድረግ ትፈልጋለች ። ደግነቱ ከያዝነው ሆቴል አጠገብ club ይታየኛል ። እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደዛው አመራን ። entrance / መግቢያ ከፍለን ፡ ተፈትሸን ገባን ። ጎበዝ ፡ ወጣቱ እዚህ አ እንዴ ያለው ። ለካ ኢትዮጵያ ወደ ዋላ የቀረችው ወዳ አይደለም ። መደማመጥ የለም ፡ ጭፈራ ብቻ ነው ። የእስፒከሩ ጩኸት ፣ የሰው ጫጫታና ዳንስ ቦታውን ሶሪያ አስመስሎታል ። "እንቅስቃሴዎች ሁሉ dance ናቸው" የሚለውን ዘፈን teddy yo እዚህ ቤት ቁጭ ብሎ የፃፈ ይመስላል ። እኔ እንኳን club ስገባ የመጀመሪያዬ ስለሆነ ስራቴን ይዤ ቁጭ ብያለሁ ። ባይሆን መጠጧን አንድ ሁለት እያልኩኝ ፡ ትርዒቱን እያየሁ ልምድ እየቀሰምኩ ነው ። ልጅት ደግሞ በስሜት አሸሸ ገዳሜውን ለመቀላቀል #1mm ነው የቀራት።

"ሂድልኝ ሀዘን ጭንቀቴ ፡ ደስታዬ ና ወደኔ ፣
ጥፋልኝ ሀዘን ህመሜ ፡ ደስታዬ ና ወደኔ" ።
ብቻችሁን መምጣት ክልክል ነው የተባለ ይመስል ፡ ሁሉም ጥንድ ጥንድ ሆነው ነው የመጡት (ልክ እንደኛው ...) ። የፈራሁት አልቀረም ፡ የከንቲባው ልጅ እጄን ይዛ አስነስታኝ ትርዒቱ መሃል ቁጭ (ይቅርታ ቁም ለማለት ነው ...) ። እንቅስቃሴ ጀምረናል ፡ ለነገሩ dance ላይ ብዙም የስራ ልምድ ስለሌለኝ እየጨፈርኩ ሳይሆን እየተወላገድኩ ነው ብል ይቀለኛል ። በመሀል በመሀል አንድ ሁለቱን ፡ ሶስት አራት እያልነው ነው ። ፊልም ላይ አረቄ /Jin ባንድ ትንፋሽ እንደዛ ሲጨልጡት በውሃ የሚያታልሉን ይመስለኝ ነበር ። ዛሬ ግን በአይኔ በብረቱ አይቼ አምኛለሁ (አይን ብረት ነው እንዴ ...) ። ኧረ ሴቶቻችን ተበላሽተዋል ጎበዝ ። ከወንዶቹ ይልቅ እነሱ ባሱኮ ። የሌሎቹ ሲገርመኝ የኔዋ ጉድ ብሳ ተገኘች ። እየጠጣን ፣ እየጨፈርን ፣ እያረፍን ፣ በድጋሚ የአሁኑን step እየደገምን በስተመጨረሻ ልጅቷ ውሃ ሆና እላዬ ላይ ተዘረገፈች ። እንዴት ተሸክሜያት ከክለቡ እስከ ያዝንበት ሆቴል እንዳደረስኳት ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው (እኔም ግን አውቃለሁ ...) ። በስንት ድካም የያዝነው ክፍል ደረስንና አልጋው ላይ ዘረገፍኳት ። ንሰሐ ገብቼ ሀጥያቴን የተናዘዝኩ ያክል ነው ቅልል ያለኝ ። የለበሰችው አጭር ቀሚስ ገላዋን ሙሉ በሙሉ የመሸፈን አቅም አልነበረውም ። በቀላል maths ከወገብ በታች አካሏ #80% ይታያል ። አልተን ገዳገድኩም እንጂ መጠጡ አናቴ ላይ ወጥቷል ። እሷ ግን የት እንዳለች እራሱ የምታውቅ አይመስለኝም ። የያዝነው #1 ክፍል ቢሆንም #2 አልጋ አለው ። እኔ አልጋዬ ላይ ሆኜ በእውን እያየዃት ፤ እሷ ደግሞ በስካር አለም ተወስዳ ተኝታለች ። የሰው ልጅ ከእንስሳ የሚለየው እራሱን መግዛት በመቻሉ ነው ። እንስሳት እራሳቸውን መግዛት ስለማይችሉ ያገኙትን በልተው ፣ ካገኙት ጋር ወስበው ፣ ሂድ ወደ ተባሉበት ሄደው ይኖራሉ እንጂ እንደ ሰው በእቅድና አላማ አይንቀሳቀሱም ። የሰው አፈጣጠር ግን ይለያል ። ህሊና ከሚባል ዳኛ ጋር ስለተፈጠረ በጎ ሲያደርግ በርታ ፣ መጥፎውን ነገር ሊሰራ ሲል ደግሞ እረፍ ፣ ከሰራም በዋላ ደግሞ በድለሀል ይቅር በል የሚል ከሳሽ አይምሮው ውስጥ ተቀምጧል ። የሰው ልጅ በሁለት መንገድ ይበድላል ። አውቆና ሳያውቅ ። ሳያውቁ ያደረጉት ይሁን ፤ ነገር ግን እያወቁ ማጥፋት የጥፋት ሁሉ ጥፋት ነው ። ብዙ ጊዜ ስካርን ተገን በማድረግ ብዙ ስተት ይፈፀማል ። በዚች ሰዓት እኔ እራሴን አልሳትኩም ። ስለዚህ እራሴን መግዛት እችላለሁ ማለት ነው ። መጥፎ ነገርን አለማድረግ እየተቻለ ማድረግ ሰይጣንነት ነው ። ይቺ ልጅ እዚህ ድረስ አብራኝ የመጣችው ስላመነችኝ ነው ። በዚህ ዘመን ደግሞ የሰውን እምነት ማግኘት የማይገኝ ትልቁ ፀጋ ነው ። ወደሷ ጠጋ ብዬ ጫማዋን አወለኩላት ። ወደ ከንፈሯ ተጠጋሁና ጆሮዬን አፏ ላይ ደቀንኩት ። ትንፋሿ ሰውነቴን ውርር ስያደርገኝ በህይወት እንዳለች አረጋገጥኩኝ ። አይኖቼ ከእግር እስከ እራስ ፀጉሯ ድረስ scan አረጓት ። ይሄ ነገር ወንድነቴን እየተፈታተነው ነው መሰለኝ ።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
💐የከንቲባው ልጅ💐

🔥ክፍል 11


.
.
.
ይሄን የመሠለ ውበትማ ለትውልድ እንደ ቅርስ መተላለፍ አለበት ብዬ ስላሰብኩኝ አስተናጋጁን ፎቶ አንሳን ብዬው ተነሳን ። እኔ በሱፍ ነኝ ፤ እሷ ቬሎ ነገር ጣል ብታደርግ ኖሮ የሰርግ ፎቶ ነው የሚመስለው ። እጅ ለእጅ ተያይዘን አስተናጋጁ ወደ ሚወስደን ቦታ ደረስን ። በአበባ የተሽቆጠቆጠ መሬት ፣ እጅግ ውብ በሆኑ ምግብና ወይን የተሞላ ጠረጴዛ ፣ ለስለስ ብሎ ከተለቀቀ ሙዚቃ ጋር ተፋጠጥን ። የከንቲባው ልጅ ቅድም ተኮራርፈን ስትተኛ ከአስተናጋጁ ጋር በመተባበር

‍ ነበር እንዲህ ያስዋብነው ። ለቦታው ደግሞ ይበልጥ ውበት የሰጠው ፡ አጠገቡ ሀይቅ መኖሩ ነው ። አስተናጋጁ "መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ ፡ የምትፈልጉት ነገር ካለ ይችን ደወል መጫን ብቻ ነው" ብሎን ጠረጴዛ ላይ ወዳለው ነገር ጠቁሞን ሄደ ። ጨረቃዋ ቁልቁል በቅናት እያየችን ደስ የሚል እራት በልተን ወይን እየጠጣን ነው ። "ጨረቃዋ አታምርም የኔ ጌታ ...?" አለችኝ ። ትኩር ብዬ አይኖቿን እያየሁ 'ካንቺ ባትበልጥም ቆንጅዬ ናት' አልኳት ። እንደተለመደው በፍቅር ትከሻዬን እየመታች "ሙት እሺ" ትለኛለች ። ለጨዋታው ድምቀት 'አንቺ እንዳታለቅሺ አስቤ እንጂ እኔኮ መሞት አላቃተኝም' ስላት ፡ ባንዴ ፊቷ ተቀያይሮ ብርሃን ይመስሉ የነበሩ አይኖቿ ወደ ደመናነት ተቀይረው በእንባ ተሞሉ ። 'አንቺ አመረርሽው እንዴ ፡ እኔኮ እየቀለድኩ ነው' ስላት ፡ "ካሁን በዋላ ግን ለቀልድም ይሁን አይሁን ፡ እሞታለሁ እንዳትለኝ እሺ ...?" አለችኝ እንባ እየተናነቃት ። አንጀቴን ስትበላኝ ቁጭ ብዬ ማየት ከበደኝ ። ከወንበሬ ላይ ተነሳሁና ተንበርክኬ 'እሺ በቃ አይለምደኝም' አልኳትና እንባዋን ጠራርጌ ከተቀመጠችበት እጇን ይዤ ተነሳን ። ወደ ጆሮዋ በአፌ ተጠግቼ በለሆሳስ 'ከኔጋር መደነስ አትፈልጊም...?' አልኳት ። "አሎድህም እሺ ...!" አለችኝና በፈገግታ ለዳንሱ እጇን ዘረጋችልኝ ። ያው የተከፈተው ሙዚቃ ለስለስ ያለ ስለሆነ የኛም ውዝዋዜ ጠንከር ያለ አይደለም ። ግራ እጄን እንደ እናቶቻችን መቀነት ወገቧ ላይ ጠምጥሜ ፣ የቀኝ እጄን ጣቶች የግራ እጇን ጣቶች ክፍተት ሞልቼበት ፣ እሷም ቀኝ እጇን ትከሻዬ ላይ አሳርፋ ፣ በእግሮቻችን አንዴ ወደፊት ፡ አንዴ ወደዋላ ፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደ ጎን እያልን በመሀል በመሀል ደግሞ እያወራን ደቂቃዎች ተቆጠሩ ። ከደሬቴ ላይ ተነስታ ቀና ብላ አይን አይኔን ታያለች ። እንዲህ ስታየኝ ደግሞ ልቤን ታቆመዋለች ፤ ምድር ላይ መኖሬን ታስረሳኛለች ። አይኖቿ ውስጥ እስከ ዳግም ምፅአት ድረስ የሚበቃ የብርሃን ሀይል ይታየኛል ። ወረድ ብዬ ከንፈሯን ሳይ ደግሞ የቴዲ አፍሮ ሙዚቃ ትዝ ይለኛል ።
"ሳማት ሳማት አለኝና ፡
ቀልቤን ገዛው እንደገና ፣
ሳሙኝ ፡ ሳሙኝ የሚል ከንፈር ፡
ድንገት አጉል አርጎኝ ነበር" ።
ከዛ በዋላ ነው እንግዲህ ሳሙኝ ሳሙኝ የሚል ከንፈር ድንገት አጉል የሚያደርገኝ ። እነዚያ የህይወትን ነዳጅ የሚያመነጩ ከንፈሮቿን ስጎርስ እስከ እለተ ሞቴ ድረስ ምግብ ባልበላ እንኳ የሚያኖሩኝ ይመስሉኛል ። ስስማት አይኖቿን ጭፍን አርጋ ትቀልጥብኝ ነበር ። ከብዙ ደቂቃ ዝምታ በዋላ "ውጪው ይበርዳል አይደል የኔ ጌታ ፡ ወደ ውስጥ እንግባ ...?" አለችኝ ።
እንዳለችውም ውጪው ያን ያክል ባይበርድም ፡ ሃሳቧን ላለመቃወም ብዬ እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ክፍላችን አመራን ። ወደ ክፍላችን የሚወስደን ደረጃ ጋ ስንደርስ "እንደ ቅድሙ ተሸክመኸኝ አትገባም የኔ ጌታ" አለችኝ ። ልክ ሙሽሮች የሰርጋቸው ለት ማታ እንግዳውን "በሉ እናንተ ብሉ ፣ ጠጡ ፣ ጨፍሩ ፡ እኛ ልንተኛ ነው" ብለው ወደ መኝታቸው እንደ ሚሄዱ ፤ እኔም ልጅቷን እንደ ሙሽራ ተሸክሜያት ፡ እሷ ደግሞ በተዘረጉላት እጆቼ ላይ ፍልስስ ብላ ወደላይ እያየችኝ አልጋው ጋር ደረስን ። ዛሬ ፈርቻለሁ ፤ የፈሩት ደግሞ ይደርሳል ተብሎ ተፅፏል ። ከጠጣነው ወይን ይልቅ ትንፋሿ አሰከረኝ ። ከተቀባነው ሽቶ ይበልጥ የገላዋ መዐዛ ማረከኝ ። ልብሶቻችንን ማወላለቅ ጀመርን ። ኮቴ ፣ ሸሚዜ ፣ የሷም ልብስ እንደዛው ። እኔ ከላይ ፤ እሷ ከታች ። በዚህ መሀል ነበር የአንገት መስቀሌ ከአንገቴ ላይ በመሀላችን ሲንጠለጠል በድንጋጤ የተነሳሁት ። እንደ ቅድሙ ዝም አላለችኝም ። "የሆንከው ነገር ካለ ለምን አትነግረኝም ፡ እእእ ...?" አለችኝ በልመና አይነት ድምፅ ። አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ ልነግራት ተዘጋጀሁ ። 'እየውልሽ ህይወት ፡ የፍቅር ታሪኬን አንድ ቀን እነግርሻለሁ ብዬሽ ነበር ። እና እሱን ዛሬ ብነግርሽ ነው የሚሻለው ብዬ ታሪኩን ጀመርኩላት ። #2007 ዓ.ም ክረምት ላይ አንዲት ቆንጅዬ ልጅ ከዱከም / ደብረ ዘይት ከተማ ዘመድ ጥየቃ ወደ ሙገር ትመጣለች ። ለመጀመሪያ ጊዜ ያየዋት በካምፓችን ውስጥ በሚገኘው ሆቴል ቁጭ ብላ መፅሐፍ ስታነብ ነበር ። ብዙ የሰፈራችን ልጆችም በስፍራው ላይ ነበሩ ። አዲስ ሴት በሰፈራችን ከታየች ደግሞ አብዛኛው ወንድ ይጋደልባታል ። እዛ የነበሩት ወንዶች ተራ በተራ ወደሷ እየሄዱ አፍረው ተመለሱ ። ልጅቷ መስሚያዋ ጥጥ ነበር ። እኔ ደግሞ በዚያን ጊዜ ሴት ልጅን እንኳን ቀርቤ ላናግራት ይቅርና አይኔን ብቻ ካዩኝ በፍርሃት እምባዬ ይመጣል ። ያቺን ቀን ያቺን ልጅ በቅርብ ርቀት ላይ ሆኜ በማየት ብቻ ቀኑ አለፈ ። ከዛን ቀን በዋላ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ተማሪ ነበርኩና ፕሮግራም አዘጋጅተን ነበር ። እና ያቺን ልጅ ድጋሜ እዛ አየዋት ። ያን ምሽት ተዋውቀን ከቤተ ክርስቲያን አብረን ወደ ቤት እየተመለስን እያለ መንገድ ላይ ዝናብ መጣብን ። ፀጉሯ ቱክስ ስለነበር እንዳይበላሽባት እንሩጥ አልኳት ። እሷ ግን "ዝናብ በጣም ስለምወድ እንደውም ቀስ ብለን እንሂድ" አለችኝ ። ሁሉም ሰው ከዝናቡ ሸሽቶ ወደቤት ገብቷል ። እኔና እሷ ብቻ በእግዚአብሔር ፀበል እየተጠመቅን በኩራት ዝናብ ውስጥ እየሄድን ፡ እሷ ስለምትወድ ብቻ ብርዱን እየጠጣሁ እስከ ዘመዷ ቤት አደረስኳት ። ብዙም አልተግባባንም ፤ ልጅቷ ብዙም አታወራም ነበር ። ግን በጣም ሳቂታ እንደ ነበረች አሁንም ድረስ ትዝ ይለኛል ። ብዙም ሳላውቃት መሄጃዋ እንደ ደረሰ ነገረችኝ ። የተገናኘነው ከሶስት ቀን አያልፍም ፤ እሱንም ለትንሽ ደቂቃ ፡ ያውም ብዙም ሳናወራ ። ስልክ ቁጥሬን የ #2008 የእንቁጣጣሽ ፖስት ካርድ ላይ ፅፌ ሰጥቻት ተሰነባበትን ። ከዛን ቀን በዋላ ያቺን ልጅ ሳላያት አንዱ ክረምት አልቆ ሌላኛው ተተካ ። ከሁለት ዓመት በዋላ #2009 ዓ.ም ክረምት ላይ ድጋሜ ወደ ሙገር መጣች ። ስለሷ ከስሟና ከመጣችበት ዘመድ ቤት ውጪ ምንም ነገር አላውቅም ነበር ። እሷ ደግሞ ከመጣች በዋላ ስሜ ጠፍቶባት ታሪኩ በሚል ስም እኔን ፍለጋ ጀመረች ።...


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 12
.
.
.
.
'በኛ ካምፕ ውስጥ ደግሞ አንድ ታሪኩ ብቻ ነበር ያለው ፤ እሱም ምርጥ ጓደኛዬ ነበር ። ከዛን ልጆች እሱን ጠቁመዋት አገኘችው ። ስታየው እኔ እንዳልሆንኩ አወቀች ። ታሪኩ ደግሞ ከኔጋር ሲገናኝ ስሟንና ከየት እንደመጣች እየጠቆመ የተፈጠረውን ነገረኝ ። ያኔ ነበር እኔን እየፈለገች እንደሆነ የተረዳሁት ። ቀኑን አላውቅም እንጂ እንደ ማገኛት አውቅ ነበር ። ከሁለት ዓመት በዋላ ያቺን ልጅ ድጋሜ አየዋት ። ቆንጅናዋ እንዳለ ነው ፤ ኧረ እንደውም ይበልጥ ተውባ ነበር ። ተገናኘን ፣ ተቃቀፍን ፣ ለብዙ ሰዓት ቁጭ ብለን አወራን ። ሲመሽብን ስልክ ቁጥር ተለዋውጠን ተለያየን ። ከዛን ቀን አንስቶ ወደ ዱከም እስክትመለስ ድረስ በየቀኑ እንገናኝ ነበር ። ሁለታችንም እንደ በፊቱ ዝምተኛ አልነበርንም ። ስለ ብዙ ነገር አወራን ፣ ተጫወትን ፣ ብዙ ቦታ አብረን ዞርን ። በቃ ባጠቃላይ ፊልም ላይ ወይንም ልቦለድ ላይ የምታውቂውን የፍቅር ህይወት አብረን አሳለፍን ። በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የሷን ከንፈር ነበር የሳምኩት ። ወክቱ ክረምት ነበር ፤ የቴዲ አፍሮ "ኢትዮጵያ" አልበም ደግሞ በብዛት ይደመጥ ነበር ። ከሱ አልበም ውስጥ ሁለታችንም "ማራኪዬ" የሚለውን ዘፈን ከቴዲ አፍሮ በላይ ወደድነው ። ልምድ ሆኖብን ሁለታችንም ከዛን በዋላ #ማራኪዬ እያልን መጠራራት ጀመርን ። ማንም ወንድ ቢቀርባት በፍቅር የሚወድቅላት ልጅ ነበረች ። እኔም ወደኩላት ። በጣም ነበር የምንዋደደው ፤ ከምነግርሽ በላይ ። የሚገርምሽ ቀኑን ሙሉ አብረን ውለን ሰለ ማንጠጋገብ ማታ ማታ ደግሞ በስልክ txt እንፃፃፍ ነበር ። እንደውም የሆነ ቀን የተፃፃፍነውን የመልዕክት ብዛት ሳይ #5000 አልፎ ነበር ። እና ማራኪዬ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነበረች ። የኔ አሳቢ ፣ የኔ እናት ፣ የኔ ፍቅር ፣ የኔ ረቡኒ ፣ በቃ ምን ልበልሽ ፡ እሷን ምድር ላይ ያሉ ቃላት አይገልጿትም ። በዚች ምድር ላይ እንደሷ የሚወደኝ ፤ እኔም እንደሷ የምወደው አልነበረኝም ። ፍቅርን ምድር ላይ ባሉት ነገሮች ግለፅልኝ ቢሉኝ #ማራኪዬን ነበር የምጠቁመው ። ያን ጊዜ እሷ የ #10ኛ ክፍል matric ፡ እኔ ደግሞ የ #12ኛ ክፍል entrance ፈተና ወስደን ውጤት የምንጠብቅበት ነበር ። ክረምቱን አብረን በፍቅር ዘመትን ። የመጣችሁ ክረምቱን ዘመድ ጋር ለማሳለፍ ነበርና ክረምቱ ሲገባደድ መሄጃዋ ደርሶ በእምባ ተለያየን ። ውጤት ተለቀቀ ፡ ሁለታችንም አለፍን ፡ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ደረሰኝ ። በስልክ ብቻ በየቀኑ txt እየተፃፃፍን ፡ በሳምንት እየተደዋወልን #8 ወር አለፈ ። ናፍቆታችን ገደቡን ሲያልፍ ቢሾፍቱ መጥቼ እንደማገኛት ቃል ገባሁላት ። በቃሌ መሠረትም ለፋሲካ በዓል ወደ ቤት ስመለስ አንድ ቀን ቀደም ብዬ ከድሬዳዋ ፡ ሸገር ፡ ከዛም ደብረ ዘይት እሷን ላገኛት ሄድኩኝ ። ለሶስተኛ ጊዜ ቢሾፍቱ የሄድኩት ያኔ ነበር ። #27-08-2010 ዓ.ም ። ተገናኘን ፣ በፍቅር ተቃቀፍን ። ስንተያይ እንዴት ደስ እንዳለን ideaw የለሽም ። የሆሳዕና ሳምንት ነበርና የሰራሁላትን የዘንባባ ቀለበት አደረኩላት ። ደብረ ዘይት ላይ አብረን ለ #3 ሰዓታት በፍቅር ሰከርን ። የመጀመሪያው ምሳችንን አብረን በላን ፣ ቢሾፍቱ ሀይቅ ሄደን juice እየጠጣን ተዝናናን ፣ photo ተነሳን ፣ ስለኛ ብዙ ነገር አወራን ፣ ተሳሳምን ፣ ተቃቀፍን ፣ ብቻ ያቺን ቀን በህይወቴ መቼም አልረሳትም ። ስጦታ የአንገት መስቀል አስራልኝ ልባችን እያለቀሰ ተለያየን ። እና አሁን አንገቴ ላይ የምታዪው ይህ መስቀል ማራኪዬ ያን ቀን ያደረገችልኝ ነው' አልኳትና በረጅሙ ተነፈስኩ.....
ምንም ሳትለኝ አልጋው ውስጥ ገብታ ተኛች ። እኔም ከዛን በዋላ አልተናገርኳትም ። እንደ መሸ አልቀረም ፡ ነጋና በጠዋት ተነሳን ። ቁርስ ከበላን በዋላ "እና ደብረ ዘይትን አታስጎበኘኝም ...?" አለችኝ ። 'እሺ' አልኳትና ባቦጋያ ፣ ምሳ ሰዓት ሆራ አርሰዴ ፣ ምሽት ላይ ደግሞ ቢሾፍቱ ሀይቅ ወስጃት ደስ የሚል ቀን አሳለፍን ። ትናንት ማታ በነገርኳት ታሪክ ምክንያት እንደ ከዚህ በፊቱ አትስመኝም ፣ አታቅፈኝም ፣ ሌላው ቢቀር ድንገት አይን ለአይን ስንጋጭ እራሱ አንገቷን ትደፋለች ። ወደ ኩሪፍቱ ተመልሰን እራት ከበላን በዋላ "ማታ ምንም ሳልልህ በመተኛቴ ይቅርታ ። ግን ታሪኩን እንድትጨርስልኝ እፈልጋለሁ" አለችኝ ። እኔም ካቆምኩበት ቀጠልኩላት ። 'እንዳልኩሽ ማራኪዬ ለኔ ሁሉ ነገሬ ነበረች ። ይሄን ደግሞ የፍቅር ታሪኬን ለሚጠይቀኝ ሁሉ አወራ ነበር ። የሆነ ቀን ግን ታሪኬን ከነገርኳቸው ሰዎች መሀል አንዱ "ስለሷ ስታወራ ከልክ በላይ እርግጠኛ የሆንክ ይመስለኛል ። ግን ተስፍሽ አንድ ነገር ልንገርህ ። ከራስህ ውጪ በማንም እርግጠኛ አትሁን ። ሁሉም ሰው አንተ እንደ ምታስባቸው ላይሆኑ ይችላሉ ። እንደዚህ የምልህ ክፉ ነገር አስቤ አይደለም ። ስለ ልጅቷ ከልክ በላይ የተማመንክባት ስለመሰለኝና አንድ ቀን እንዳትጎዳ ስለፈለኩኝ ነው" አለኝ ። በሱ አስተያየት ምንም አልተሸበርኩም ነበር ። እንደውም 'አንተ ማራኪዬን ስለማታውቃት ነው' አልኩት ። ከዛ በዋላ ነው እንግዲህ ጨዋታው የተጀመረው ። "ስማ ተስፍሽ ፡ እንደ ነገርከኝ ከሆነ ማራኪዬ የምትላት ልጅ ፡ አንተ ምንም ብትሆን ፣ የትም ብትሄድ ፣ ሌላው ይቅርና አንተ ብትተዋት እንኳን የማትተውክ ፣ እስከ እለተ ሞቷ ድረስ የምታፈቅርክ የተለየች ሴት ናት ። ይሄን ያክል ደግሞ በሷ እርግጠኛ ከሆንክ ለምን እኔ የምነግርህን ፈተና አታቀርብላትም ...?" አለኝና ፈተናው ምን እንደሆነ ጠየኩት ። ቀጠለና "ምን መሰለህ ፡ #3 ነገሮችን እንድታደርግ እፈልጋለሁ ። #1ኛው ፡ የልደት ቀኗ ሲደርስ ምንም አይነት txt እንዳትልክላት ፣ እንዳት ደውልላትም ። በዚህም ከሁሉ በላይ አንተን ስለ ምትጠብቅህ በጣም ታዝንብሀለች ። #2ኛው ፡ ያንተ የልደት ቀንም ሲደርስ ፡ ከሷ ለሚመጡልህ የመልካም ምኞት መግለጫ መልስ አትስጥ ። ይሄ ነገርም የንዴት መጠኗን ከፍ ያደርጋል ። #3ኛውና ወሳኙ ደግሞ ፡ ክረምት ክረምት እናንተ ጋር ሙገር እንደ ምትመጣ ነግረኸኛል ። እናም ባሁኑም ክረምት መምጣቷ ስለማይቀር ፡ ያኔ ስትገናኙ ፊት ንሳት ፣ እንደ ማትወዳት act አርግ ፣ ከሷ ጋር በመሆንህም ደስተኛ እንዳልሆንክ አስመስል ። አንተን ብላ መጥታ እንደዛ ስትሆንባት መቼም ምን እንደሚሰማት መገመት አይከብድም ። እውነት እልሀለሁ ተስፍሽ እነዚህን ሶስቱን ነገሮች ተግብረህ ፡ ማራኪክ 'እኔ አልተውህም ፣ እንደዚህ ብትሆንብኝም እወድሃለሁ' የምትልህ ከሆነ she is the best girl in the world" አለኝ ። ሶስቱን ፈተና ብሎ የነገረኝን ስሰማ መጀመሪያ ስቄበት ነበር ። እንደ ቀላል አይቼው ፣ እንደ ምታልፈውም በሙሉ ልቤ ስለተማመንኩኝ ልፈትናት ወሰንኩኝ ። ስለዚህ ጉዳይ ከኔና ከልጁ ውጪ ማንም ሰው አያውቀውም ። ደስ የሚለው ነገር የልደቷ ቀን ያኔ የነበርንበት ወር ውስጥ ነበር ። የመጀመሪያው የፈተና ቀን ደረሰ ፡ የልደቷ ቀን....


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
💐የከንቲባው ልጅ💐

🔥ክፍል 15


.
.
.
"ከአራት ዓመት በፊት #9ኛ ክፍል እንደጀመርኩ ነበር ። የከዚራ ልጅ ብሆንም Elementery እያለን በጣም የምወደውና የምቀርበው ብቸኛው ልጅ አቤል የሳቢያን ሰፈር ልጅ ስለነበር አንድላይ ለመሆን ሳብያን high school ተመዘገብኩኝ ። ከእለታት በአንዱ ቀን በትምህርት ቤታችን ጊቢ ውስጥ crazy day የሚባለውን የፈረንጆች የዕብደት ቀን ለማክበርና ለየት ብሎ የሚመጣ ሰውም እንደ ሚሸለም ጭምር ከተማሪዎች ጋር ወስነን የሚከበርበት ቀን ደረሰ ። አብዛኛው ተማሪ የተቀዳደደ ልብስ ለብሰው እንደ ሚመጡ ግልፅ ነውና እኛ ግን ከነሱ ለየት ብለን ለመቅረብ የግድ አዲስ ፈጠራ መጠቀም ነበረብን ። በደምብ አስበንበትና ተዘጋጅተንበት ሁለታችንም የዕብደቱን ቀን ለማክበር ተያይዘን ወደ ሳቢያን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አቀናን ። እንዳሰብነውም አብዛኞቹ የተቀዳደደና የቆሸሸ ልብስ ለብሰው ፣ ፊታቸውን ደግሞ ከሰል ተቀብተው ነበር የመጡት ። ትኩረት መሳብ የቻልነው ግን እኛ ነበርን ። ያን ዕለት እኔን አይቶ ይቺማ ሴት ናት የሚል ፤ ልክ እንደኔው አቤልንም አይተው ወንድ መሆኑን የሚያውቅ ከሁለታችን በስተቀር አንድም አልነበረም ። ከፆታችን ውጪ ሁሉንም ነገር ተቀያይረናል ። እሱ የኔን ቀሚስ ፣ ጡት ማስያዣ ፣ ሹራብ ፣ ሂል/ታኮ ጫማ ፣ human hair ጭምር ገዝተን አድርጎ ፣ ሁሌም ከኔላይ የማጠፋዋን pink ሻርፕ በአንገቱ ዙሪያ ጠምጥሞ ፣ ቦርሳዬንም በጀርባው ተሸክሞ ፣ ከንፈሩንም Lip stick ተቀብቶ ምን የመሰለች ቆንጆ ኮረዳ መስሏል ። እኔ ደግሞ የሱን ሰፊ ጂንስ ሱሪ ፣ ሸሚዝ ፣ Adidas ጫማ ፣ ፀጉሬ እንዳይታይ ደግሞ ከላይ በሱ ኮፊያ ሸፍኜ ፣ እሱ ፂም ባይኖረውም ጉንጮቼ ላይ ፀጉር ለጣጥፌ ምን የመሠለ ሸበላ ወንድ ሆኛለሁ ። ለኛ ዕብደት ልብስ መቅደድ ፣ የቆሸሸ መልበስ ፣ ፊትን በቀለም ማጥቆር ሳይሆን ፈጣሪ ወንድ አድርጎ ፈጥሮት እንደ ሴት የሚሆን ፤ ሄዋን አድርጎ ፈጥሯት እንደ ወንድ የሚያረጋት ፣ ባጠቃላይ ወንድና ሴት ቦታቸውን ተቀያይረው ተፈጥሮን ሲቃወሙ ማየት ነው ዕብደት ። ይህ ነገር ደግሞ ከነጮቹ ከነ ሰልባጃቸው ወደ ሀገራችን እየገባና እየተስፋፋ ያለው ጉዳይ ነው ። ወንዱ ሴት ይመስል ከንፈሩን ደም የጠጣች ድመት አስመስሎ ፣ ፀጉሩን አሳድጎ እንደ ጭላዳ ዝንጀሮ ነስንሶ ፣ ከሰውነቱ ጋር የተጣበቀ ሱሪ ለብሶ ፣ ጆሮውን ተበስቶ ፤ ሴቷም ፀጉሯን ተቆርጣ ፣ ሱሪ ለብሳ ፣ ጡንቻ እያሳየች የወንድ አካሄድ እየሄደች ማየት ቀስ በቀስ በሀገራችን እየተለመደ መቷል ። አላማችንም ይህን ነገር መፀየፍና መከላከል ስለነበር ይህ አይነቱ ድርጊት ዕብደት መሆኑን ማሳወቅ እንጂ ፆታ ተቀያየሩ የሚል አልነበረም ። በዚህም ሁሉም ተስማምተውበት ሽልማቱን ወስደን ዝግጅቱም አለቀ ። ከት/ቤት ጊቢ ወተን አቤል ሊሸኘኝ ወደኛ ሰፈር አቀናን ። በሰዓቱ በጣም ጠምቶኝ ስለነበር እዚው ጠብቀኝ መጣው ብዬው በቀኝ በኩል ወደሚታየው ሱቅ ሄድኩኝ ። ባለሱቁን #2 ጁስ ስጠኝ ብዬው መቶ ብር ሰጠውት ። ወንድ መስዬው ስለነበር ድምፄን ሲሰማ ደንግጦ ነበር ። መልሱን እስኪፈልግ ድረሰ ዞር ብዬ አቤልን እያየሁት ፤ እሱም ወደኔ ዞሮ በአይኑ እየቃየኝ ነበር ። እውነት ለመናገር ከራስ ፀጉሩ እስከ እግር ጥፍሩ ድረስ እንዳለ የኔን ልብሶች ስለተጠቀመ ላየው ሰው እሱ አቤል ሳይሆን ህይወት ናት ። ባለሱቁ 'ይኸው የኔ ወንድም ይቅርታ እህት ለማለት ነው' ብሎኝ መልሱን ሲሰጠኝ ከዋላዬ የተኩስ ድምፅ ሰማሁ" ።
"ስዞር ፡ አቤል እዚው ጠብቀኝ ባልኩበት ቦታ ላይ ተዘርሮ ወድቆ አየሁት ። መኪና ውስጥ ሆነው ነበር የተኮሱትና መኪናዋ ሳትቆም በዛው ሄዳ ተሰወረች ። በቃ በዛች ሰዓት የማስታውሰው ነገር ቢኖር ለአባቴ ደውዬ ያለንበትን ቦታ ነግሬው ፤ እስኪመጣ ድረስ ሰው ተሰብቦ እንዳይበዛ ባለሱቁን ለምኜው አቤልን ተሸክመን ወደ ቤቱ ውስጥ እንዳስገባን ነው ። አቤል በጣም ተዳክሞ ነበር ፤ ብዙ ደምም ከተተኮሰበት የዋላው ጭንቅላት ፈሶታል ። ሆስፒታል መውሰዱ አማራጭ አልነበረም ፤ መጀመሪያውኑ ወደሱ ሮጬ ስደርስ ህይወቱ አልፏል ። አባዬም በፍጥነት መጥቶ ሁለታችንንም ወሰደን ። ቦታው በከዚራ እና በሳቢያን መካከል ስለነበር ባለሱቁ ሁለታችንንም አያውቀንም ነበር ። ሳስበው አባቴ መጥቶ እስኪወስደን ድረስ ተጠምጥሜበት እያለቀስኩ ስለነበር ከአለባበሱ አንፃር አቤል ሴት እንደሆነ ነው የሚያምነው ። ከዛን አባቴ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ ...? ገዳዮቹ ማንም ይሁኑ ማንም እኔን እንደገደሉ አድርገው ስለሚያምኑ በአቤል መቃብር ላይ የኔን ስም አፃፈበት ። ከኔና ከአባቴ ውጪ ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቅ ሶስተኛ ሰው አንተ ብቻ ነህ ። አቤል ዘመድና ቤተሰብ አልነበረውም ። በቃ ብቻውን በራሱ ለራሱ ሰርቶ የሚማር ልጅ ነበር ። እኔ እሱን እሱም እኔን ብቻ ነው የሚቀርበው ። የዋህ ፣ ለሰው አሳቢ ፣ መልከ መልካም እና ጠንካራ ልጅ ነበር ። ልባቸውን አቆሽሸው ልብሳቸውን ከሚያሳምሩት ወገን አልነበረም ። ባለው አቅም ያለውን ፅድት ያለች ዩኒፎርም ከንፁህ ልቡ ጋር ያዋሀደ ምርጥ ልጅ እንጂ ። ለዛም ነበር እሱ የሚማርበት ት/ቤት የተመዘገብኩት ። አባቴ የኔን ምርጫ ስለሚያከብር ብቻ ሳያቅማማ ነበር እዛ ያስመዘገበኝ ። ምን ዋጋ አለው ፡ አሁን ላይ ስሙ እንጂ እሱ የለ ። ለኔ የታሰበውን አፈር እሱ ቀመሰልኝ ። እሱንና እናቴን ለይቼ እላያቸውም ። እናቴ ህይወት ልትሰጠኝ ህይወቷን አጣች ። አቤል ደግሞ ህይወቴን ሊያስቀጥል ህይወቱ ተቋረጠ ። ሁለቱም አስበውበትና አቅደውበት ባያድኑኝም ለዛሬው ህይወቴ ምክንያቶች ናቸው ። ከአቤል ቀብር በዋላ አባቴ እንኖርበት ከነበረው ከዚራ ከሚገኘው ቤት ሌላ አዲስ ቤት ገዛና በድብቅ እዛ አስቀመጠኝ ። ቤቱ ላይም ከላይ 'የሚከራይ' ብሎ ለጠፈበት ። ሰዎች ሊከራዩ ሲደውሉ ብዙ ብር ስለሚጠራባቸው ማንም አይከራየውም ። ከኔና ከአባቴ ውጪ እዛ ቤት ውስጥ እኔ እንዳለሁ የሚያውቅም አልነበረም ። በዛ ቤት ውስጥ ለ #4 ተከታታይ ዓመታት አብዛኛውን ጊዜ ብቻዬን ፤ ጥቂቱን ደግሞ ከአባቴ ጋር አሳለፍኩኝ ። አንተን እስካወኩበት እለት ድረስ ከቤት መውጣት ፣ መልበስ ፣ መብላት ፣ መጫወት ፣ ምንም ነገር አያምረኝም ነበር ። የሁሉም ቀናት ውሎዬ ተመሳሳይ ናቸው ። መተኛት ፣ ማንበብ ፣ ፊልም ማየት ፣ ትንሽ መብላት ፣ በጊታሬ መዝፈን ፣ ቅዳሜና እሁድ ደግሞ ከአባቴ ጋር መሆን ነው ። ይሄንንም ለማድረግ አንድ ዓመት ፈጅቶብኛል ። ከአቤል ሞት በዋላ ለአንድ ዓመት በአንድ መኝታ ቤት ውስጥ የሱ ደም የለበሰ አካል በህሊናዬ ውስጥ እየተመላለሰ እየወቀሰኝ ደንዝዤ አሳለፍኩኝ ። ከዛን በዋላ ነው ቀስ በቀስ ወደ ቀልቤ የተመለስኩት ። ከነዚህ ሁሉ ጊዜያት በዋላ አንተን ሳገኝ ለምን በአንዴ እንደ ተለወጥኩ ታውቃለህ ...?" አለችኝና ከቦርሳዋ ውስጥ የሆነ ፎቶ አውጥታ ሰጠችኝ ። ፎቶው ላይ ያለውን ልጅ ሳይ ለማመን ነበር የከበደኝ ።

@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል..........
🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 16



"አንተን የሚመስል ሰው አውቃለሁ ፣ አንተን የሚመስል ዘመድ አለኝ ፣ እኛ ሰፈር አንተን የሚመስል ልጅ አለ ፣ ወዘተ" ነገሮችን ብዙ ሰዎች ሲሉኝ 'ይሆናል እንግዲህ የፈጣሪ ጥበቡ ብዙ ነው' ከሚል መልስ ውጪ ብዙም ትኩረት አልሰጠዋቸውም ነበር ። science እንደ ሚለው በአለማችን ላይ ከ #4 በላይ በመልክ የሚመሳሰሉ ሰዎች አሉ ። እኔን የሚመስል ሰው እስካሁን ባካል ባይገጥመኝም ፡ ከብዙ ሰዎች ግን እሰማ ነበር ። በዚህ ዓመት ብቻ #4 ሰዎች በቁምነገር እንደዛ ብለውኛል ። አንዱ ልጅ እንደውም መንገድ ላይ አስቁሞኝ "ባህር ዳር አውቅሀለሁ እኮ እንዴት ነህ ...?" ብሎኛል ። እኔ ግን ባህርዳርን በስም እንጂ በአካል አላውቃትም ። ከሁሉ ነገር ግን ያስገረመኝ ፡ እኔን የሚመስሉ #4ቱ ሰዎች የተገኙት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ። ቆይ ግን እንዴት እኔን የሚመስል ሰው ህንድ ወይንም ደግሞ Spain ውስጥ አልተገኘም ...? ሌላው ቢቀር ቢጠፋ ቢጠፋ እኔን የሚመስል ሰው ቱርክና brazil ውስጥ ይጠፋል ...? science እኮ ያለው በአለማችን ላይ እንጂ በአንድ ሀገር ውስጥ ብቻ አላለም ። anyways ምናልባት የኔ ሌላ የቀረ high copy ሰው ካለ ግን ባልኳቸው ሀገራት ውስጥ ባይገኙም ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለበዛሁ ቻይና ወይ Nigeria ውስጥ ቢገኙ አይከፋኝም ። (ደግሞ ስቀልድ ነው ...) ። ሳሉት እስኪ እኔን የሚመስል ቻይናዊ ። (በናታችሁ አትሳሉት ...) ። ከከንቲባው ልጅ ጋር ያንን ሰውዬ አይተን አጣድፋኝ መኪና ውስጥ ገብተን ወደ ኩሪፍቱ ማረፊያ ክፍላችን ገብተን አረጋግቻት ሁሉን ነገር ከነገረችኝ በዋላ በሰጠችኝ ፎቶግራፍ ላይ ፈዝዤ ቀርቻለሁ ። እኔን የሚመስል ልጅ በአካል አይቼ ባላውቅም ዛሬ ግን በፎቶ አየሁኝ ። ሰው እንዴት በተለያየ ቦታና ከተለያየ ሰው ተወልዶ እንዲህ ሊመሳሰል ይችላል ...? አልኩኝ ለራሴ ። እውነትም የፈጣሪ ጥበቡ ብዙ ነው ። የከንቲባው ልጅ አንዴ ፎቶውን ፡ አንዴ ደግሞ እኔን እያየች ማውራቷን ቀጠለች ። "ለመጀመሪያ ጊዜ በመኪናዬ ውስጥ ሆኜ ሳይክ አቤልን ያገኘሁ ፤ በቃ ፈጣሪ የኔን ዕምባ አይቶልኝ ወደ ምድር የመለሰው ነበር የመሠለኝ ። ወርጄ ተጠመጠምኩብህ ፣ ሳምኩህ ፣ እጅህን ያዝኩህ ፣ አይኖችህን ጎበኘሁ ፣ አለቀስኩብህ ፣ አስጨነኩህ ፣ አዝነህልኝ እቤት ድረስ ይዘኸኝ መጣህ ፣ አወራሁክ ፣ አብረን ተመገብን ፣ ሳታውቀኝ ሳላውቅህ እቤት አሳደርኩህ ፣ ሀሳቤን ጭንቀቴን ነገርኩክ ፣ ሰማኸኝ ፣ ትምህርቴን ብለክ ብቻዬን አልተውከኝም ፣ ከአባቴም በላይ ቀርበኸኝ ለኔ ደስታ ስትል እዚህ ድረስ አብረኸኝ መጣህ ። አየህ ካየውክ ሰዓት ጀምሮ እንደ አቤል ስለማይክ መጥፎ ነገሮችን ማሰብ አልፈለኩም ። አላውቀውም ፣ ይጎዳኛል ፣ እንዴት ልመነው የሚሉ ነገሮች ውስጥ አልገባውም ። በቃ እንዳየውክ አመንኩህ ። የሚፈጠረው ነገር ሁሉ ይፈጠር ብዬ እራሴን አሳመንኩኝ ። እምነቴ ገደል አልገባም ፤ ካሰብኩህና ከጠበኩህ በላይ ሆነኽልኛል ። ይሄን ሁሉ ደግሞ የደበኩህ ማስታወስ የማልፈልገው ታሪኬ ስለሆነ ነው ። አሁንም የነገርኩህ ልክ እኔን ለመግደል አስበው አቤልን እንደ ገደሉት አንተንም እንዳይ ነጥቁኝ ስለፈራሁ ነው እሺ የኔ ጌታ" አለችኝና አሁኑኑ መተው የሚገድሉን ይመስል ተጠምጥማብኝ "ከዚህ ቤት ውስጥ አኖጣም እሺ ...?" ትለኛለች ። ነገሩ ትንሽም ቢሆን ቢያስፈራም ለማፅናናት ብዬ 'አንቺን እንደገደሉ ነው የሚያውቁት ፣ በዛላይ ከቤት ወተሽም ስለማታውቂና እዚህም በለሊት ስለሆነ ከድሬ የመጣነው በምንም ተዐምር ስላንቺ ሊያውቁ አይችሉም አይዞሽ' አልኳትና ተረጋጋች ።
.....
ሞትን ባልፈራም ፡ በዚህ ሰዓት ግን መሞት አልፈልግም ። ቁጥሩ ይብዛም ይነስም ወደፊት መኖር እፈልጋለሁ ፤ ግን ዛሬ መሞት አልፈልግም ፡ ነገም እንደዛው ። ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ ከሞት አምልጫለሁ ። (ደግሞ በሩጫ አይደለም...😜) ። እናቴ እንደ ነገረችኝ ከሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ሞትን የተጋፈጥኩት ልጅ እያለሁ ነፍስ ሳላውቅ በሁለት ዓመቴ ነበር ። ታሪኩም እንዲህ ነው "የጠዋት ፀሀይ ለልጆች ጥሩ እንደሆነ የትኛውም ዶክተር ሳይነግራቸዉ እናቶች በራሳቸው ጥበብ ስለሚያውቁት ፡ እናቴም ጠዋት ከአልጋ ላይ አንስታኝ ግቢ ውስጥ ወደሚበራው የማለዳ ብርሃን አውጥታኝ እሷ ደግሞ እቤት ውስጥ ምሳ እየሰራች ነበር ። ቆሜም ፣ በዳዴም መሄድ አልጀመርኩም ። እንደዛ ለመሄድ ብዙ ዓመት እንደ ፈጀብኝ እናቴ ነግራኛለች ። እናቴ ምሳ እየሰራች ፡ በመሀል ደግሞ ደህንነቴን ለማረጋገጥ እየወጣች ታየኛለች ። አይኔ ተከድኗል ፣ ተኝቼ እንደሆነ ለማረጋገጥ ጠጋ ብላ በጆሮዋ ትንፋሼን ለመስማት ስትሞክር ምንም አይነት የመተንፈስ ነገር አልነበረም ። ልብ ምቴንም ስታዳምጠው ቆሟል ። ይሄኔ ነበር እናቴ ብቻዋን ማንም በሌለበት ሰፈር እምቧዋን ወደላይ መርጨት የጀመረችው ። የደም እምባ አለቀሰች ። እንዴት አሳይተኸኝ ትነሳኛለህ ብላ የፈጣሪ ልብስ ይመስል የመሬቱን ሳር ጭምድድ አርጋ ይዛ አነባች ። ምነው እመቤቴ ፡ የልጅን ፍቅር ካንቺ በላይ የሚያውቅ የለ ፤ ልጄን እኮ ባንቺ ቤት ክርስትና ማስነሳቴ በፍቅርሽ እንድታኖሪልኝ ነበር ፤ ምነው ታድያ ሳልጠግበው ነጠቅሽኝ እያለች አምርራ አለቀሰች ። በዚህ መሀል ግን እናቴ ከሷ ለቅሶ በተጨማሪ የሌላ ሰው የለቅሶ ድምፅ ሰምታ ዝም አለች ። ወደኔ ስታይ እኔ ነበርኩ የማለቅሰዉ ። ያቺ ቀን ለኔ ለደቂቃዎች ምድርን ለቅቄ ሰማይን ነክቼ ፡ ፈጣሪ ከእናቱ ጋር የእናቴን እምባ አይቶላት ድጋሜ ወደ ምድር የመለሰኝ እለት ነበረች" ። ተወልጄ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በጣም እታመም ነበር ። እንደውም ሀኪም ቤት በየቀኑ ከመመላለሴ የተነሳ ቂጤ በመርፌ ብዛት ወንፊት ይመስል ነበር አሉ ። በሽታው በግልፅ ባይታወቅም ፡ ለማስታገሻ ተብሎ ሁሌም መርፌ እወጋ ነበር ። በዚያ ምክንያት እንደውም ነጭ ልብስ የለበሰ ሰው ካየሁ ዶክተር ስለሚመስለኝ ኡ ኡ ታውን እንደ ምለቅ እናቴ ነግራኛለች ። ያን ቀን ግን ሞቼ ከተነሳሁ በዋላ እስካሁኗ ሰዓት ድረስ አሞኝ ሀኪም ቤት ስሄድ ትዝ አይለኝም ። ያቺ እለት ለኔ ከሞት ወደ ህይወት ብቻ ሳይሆን ከህመም ወደ ሙሉ ጤንነት የተመለስኩባትም ናት ። ለ #2ኛ ጊዜ ደግሞ ከሞት አፋፍ ላይ የተመለስኩት ከ #5 ዓመት በፊት የጥምቀት በዓል ላይ ነበር ። በዓሉን ለማክበር ከጎረቤት ልጅ ቤቲ ጋር ተያይዘን ወደ ጥምቀተ ባህሩ ወረድን ። ቤቲ ለትምህርት እንዲያመቻት ወላጆቿ ጋር ሳይሆን ለት/ቤቱ ቅርብ በነበሩ ዘመዶቿ (ጎረቤታችን) ጋር ነው የምትኖረው ። በወቅቱ ደግሞ እሷ ኢዶ የሚባል ፍቅረኛ ነበራት ። ምክንያቱን ባላውቅም ወላጅ አባቷ ደግሞ ይሄን ነገር ሰምቶ ልጁን ሊገድለው ይፈልግ ነበር ። ሆኖም ግን የልጁን መልክ ለይቶ ስለማያውቅ የጥምቀት ቀን እኔንና ቤቲን አንድላይ አይቶን ኢዶ መስዬው ሽጉጡን አወጣና ሊገድለኝ ወደኛ አመራ ። ይሄኔ ነበር የቤቲ አሳዳጊ ጎረቤታችን ኡኡኡ እያለች እግሩ ስር ወድቃ "እሱ አይደለም ፣ ይሄ የአበቡ ልጅ ነው ፣ ይሄ የጎረቤት ልጅ ነው" ብላው ከሞት ያስጣለችኝ ።
💐የከንቲባው ልጅ💐
🔥ክፍል 13

.

ከጠዋት እስከ ማታ ቀኑን ሙሉ በልቤ የልደቷን ቀን እያከበርኩ ፡ ድምፄን አጠፋሁ ። ሳልደውልላትና መልዕክት ሳልክላት ምሽቱ ወደ መገባደድ ደረሰ ።..ከምሽቱ #05 ሰአት አከባቢ ከማራኪዬ እንዲህ የሚል txt ግባልኝ ። "የልደቴን ቀን ብዙ የምወዳቸው ሰዎች አክብረውልኝ ደስ ብሎኝ ዋልኩኝ ። ነገር ግን ከሁሉም በላይ አስበልጬ ቦታ የሰጠሁት ልጅ ዝም ብሎ ዋለ ፤ ዝምም" ። እንዲህ ስትለኝ ምን ያክል ልቤን እንደ በላችው ፈጣሪ ያውቃል ። በጣም ነበር ያሳዘነችኝ ። ቢሆንም ግን ምንም አይነት መልስ ሳልሰጣት ያ ቀን አለፈ ። ከወር በዋላ ሁለተኛው የፈተና ቀን ደረሰ ፤ የልደቴ ቀን ። የሚገርምሽ ነገር ጠዋት #12:00 ላይ ነበር "እንኳን ተወለድክልኝ" የሚል መልዕክት መላክ የጀመረችው ። እስከ ማታ ድረስ እኔ ምንም ሳልመልስላት #14 txt ተስፋ ሳትቆርጥ ላከችልኝ ። መጨረሻ ላይ እንዲህ የሚል message ግባልኝ ። "ማራኪዬ ፡ ይኸው #15ኛ txt ላኩልህ ፡ አንተ ግን አንዱንም አልመለስክልኝም ፤ አላሳዝንህም ...?" አለችኝ ። በዚህ txt ልቤ ቢደማም እንደ ምንም ላለመመለስ እራሴን አስጨክኜ ያቺ ቀንም አለፈች ። ከዛም በዋላ በፈተናው ምክንያት txt ብዙም አላወራትም ነበር ። በዚህም ምክንያት ትምህርት እንደ ጨረሰች ክረምት ላይ ወደ ሙገር መጣች ። #3ኛው የፈተና ቀን ። ምን እንደ ተፈጠረ ጠየቀችኝ ። እኔ ግን እንኳን እሱን ልመልስላት ይቅርና በፈተናው መሠረት ጭራሽ ፊት ነሳዋት ። አይኗን እያየሁ መዋሸት ስለ ከበደኝ አንገቴን አቀርቅሬ እንደ ማልፈልጋት act አደረኩ ። ችላ አልኳት ፣ እንደ ድሮው አልስማትም ፣ አላጫውታትም ። ባጠቃላይ የቀደመውን ፍቅሬን ተውኩት ። ይሄን ሁሉ ሳደርግ ግን በውስጤ የደም እምባ እያነባሁ ነበር ። እሷንም ሳያት እንደዛው ነበረች ። ቃል አውጥታ ባትነግረኝም በኔ ልቧ ተሰብሯል ። ትንፋሿን ዋጥ አድርጋ ፡ ለኔ ስሜት ተጨንቃ ምንም እንዳልተጎዳች ታስመስል ነበር ። አብረን ባሳለፍናቸው ቀናት ምንም አይነት የፍቅር ስሜት አላሳየዋትም ነበር ። የመሄጃዋ ቀን ሲደርስ "ማራኪዬ ፡ አንተ ሁሉ ነገሬ ነህ ፤ እኔስ ላንተ ምንድነኝ ...?" የሚል ያላሰብኩትን ድንገተኛ ጥያቄ አቀረበችልኝ ። ሁለት ሀሳብ ውስጥ ገብቼ ነበር ። #1ኛው በፈተናው ህግ መሠረት 'ምኔም እንዳልሆነች act ማድረግ' ሲሆን #2ኛው ደግሞ እውነታውን 'ሁሉ ነገሬ እንደሆነች መናገር' የሚሉት ናቸው ። ፈተናውን ጀምሬ በስተ መጨረሻ ተስፋ መቁረጥ አልፈለኩም ። ከዛን ነበር አይኔን በጨው አጥቤ #3ኛውን ፈተና የተገበርኩት ። አፍ አውጥቼ ምኔም አይደለሽም አላልኳትም ። በዝምታ ብቻ ነበር የመለስኩላት ። ዝምታም መልስ ነው በሚለው ተረዳችኝና ምንም ሳትለኝ ከዱከም ይዛልኝ የመጣችውን ስጦታ ሰጥታኝ ወደ ሀገሯ ተመለሰች ። ስጦታውን እቤት እስክገባ አለማየት ስላላስቻለኝ መንገድ ላይ ነበር የከፈትኩት ። እንዲህ አይነት ስጦታ ከማንም ተሰቶኝ አያውቅም ነበር ። የኔን ስዕል በእንጨት ፍሬም ላይ በሰዓሊ አስላ ሰጠችኝ ። ስለኔ ወቅታዊ ፀባይ መቀየርም በደብዳቤ ፅፋልኝ ነበር ። anyways ከዛን ቀን በዋላ ማራኪዬን አይቻት አላውቅም ፣ ስልኬን አታነሳም ፣ txt አትመልስም ። ስልኳ እንደውም አብዛኛውን ጊዜ አይሰራም ነበር ። በጓደኞቼም ስልክ ስደውል አታነሳም ።
'በቅርብ ጊዜም ላወራት ፈልጌ ነበር ፤ እሷ ግን እኔ መሆኔን ስታውቅ መልስ አትሰጠኝም ። ባጠቃላይ ከኔጋር ስለምንም ነገር ለማውራት ፍቃደኛ አይደለችም ። ሲመስለኝ ረስታኛለች ፤ ወይም ደግሞ እኔን ለመርሳት እየሞከረች ይሆናል ። ለዚህ ሁሉ ምክንያት የሆነው ደግሞ ፈተናው ነበር ። እሷ ደግሞ እኔን ለማናገር ፍቃደኛ ባለመሆኗ ምክንያት ስለ ፈተናው እስካሁን ድረስ ምንም የምታውቀው ነገር የለም ። እንኳን ጊዜ ሰጥታኝ ሁሉንም ነገር ልትሰማኝ ይቅርና ከሰላምታ ውጪ ከኔጋር ምንም ነገር ማውራት አትፈልግም ። ባጠቃላይ ስለኔ ጉዳይ ከኔጋርም ይሁን ከሰዎች ጋር ማውራት እንደ ማትፈልግ ከሷም ከጓደኞቿም ሰምቻለሁ ። ከጓደኞቿ ጋርም ለማውራት ፈልጌ ነበር ፤ ግን ሁሉም እኔን ከመውቀስና ወንዶች ስትባሉ ግን ከማለት ውጪ የኔን እውነታ የሚሰማኝ አላገኘሁም ። በቃ ፈተናውን እንደ ቀላል ነገር አይቼው ፍቅሬን ተነጠኩኝ ። አጠገቧ ሆኜ እውነታውን ባላውቅም ይመስለኛል በኔ ተስፋ ቆርጣለች ወይንም ደግሞ ተስፋ መቁረጥ ትፈልጋለች ። በዚህ ሁሉ መሀል ግን ለአንድም ቀን ማራኪዬን ወቅሻት አላውቅም ። ምክንያቱም ጥፋቱ ሁሉ የኔ ስለነበር ። እሷ ከደሙ ንፁህ ናት ። ባይሆን ግን ትንሽም ቢሆን ቅር ያለኝ ነገር በቀላሉ በኔ ተስፋ መቁረጧ ነበር ። ለአንድም ቀን አስቤም ስለማላውቅ ይሄ ነገሩ አስከፍቶኛል ። እንዲህም ሆኖ ግን በጣም እንደ ጎዳዋት ይሰማኛል ። በኔ ክህደት የተፈፀመባት ስለሚመስላት አይኗ እስኪጠፋ ድረስ እንደ ምታለቅስ አውቃለሁ ። ልቧ ተሰብሮ ከሰዎች ተለይታ ለብዙ ቀናት ብቸኛ እንደ ምትሆን ይታየኛል ። እውነታውን ስታውቅ ግን ምን እንደ ምትለኝ አላውቅም ። "ይቅር" ብላኝ እንደ በፊቱ አብረን መሆን እንጀምር ይሁን ፤ ወይንም ደግሞ "ሁሉም አልፏል ፡ አንዴ ከልቤ አስወጥቼሀለው ፡ ከአሁን በዋላ እኛ የሚባል ነገር የለም" ትለኝ ይሁን አላውቅም ። እኔ እስካሁን ስለሷ ሳወራ በስሟ እንኳን ጠርቻት አላውቅም ። የእሷን ግን እንጃ ፤ እንኳን ማራኪዬ ብላ እኔን መጣራቷ ይቅርና ስለኔ ማሰቧም ጥያቄ ምልክት ውስጥ ነው' ። ከዚህ በላይ ለከንቲባው ልጅ ስለ ማራኪዬ የመተረክ አቅም አልነበረኝም ። 'በጣም ደክሞኛል' አልኳትና ወደ መኝታዬ አመራሁ ። በጣም ከፍቶኛል ፤ በዛላይ ሳልፈልግ እምባዬ እየፈሰሰ አስቸገረኝ ። ብዙም ሳልቆይ እንደ ተገረፈ ህፃን ድምፅ አውጥቼ ማልቀስ ጀመርኩኝ ። ይሄኔ ነበር የከንቲባው ልጅ በፍጥነት ከመኝታዋ ተነስታ አልጋዬ ላይ ወጥታ እቅፍ አድርጋኝ እያባበለችኝ ፣ ግንባሬን እየሳመችኝ ፣ ፀጉሬን ልጅ እያለሁ እናቴ እንደ ምታደርገው በጣቶቿ እየዳበሰችኝ ፣ "እሽሽሽ ..." የሚል ለስላሳ ድምጿን በጆሮዬ ተጠግታ እያሰማችኝ ዝም ያስባለችኝ ። ግን ዝምታዬ በዛው አልፀናም ነበር ። ተነስቼ ምንም የማታውቀው ልጅ ላይ ጮህኩኝ ፣ አለቃቀስኩባት ፣ ማራኪዬ እሷ የሆነች ይመስል 'ለምንድነው የማታዳምጠኝ ፣ ለምንስ ነው እውነታዬን የማትሰማው ...? ፡ እኔኮ ማንም ሰው እንዲያምነኝ አይደለም ፍላጎቴ ። በቃ እውነቱን ብቻ እንዲሰሙ ነው' እያልኳት በሀይል ተናገርኳት ። በሁኔታዬ ብትደናገጥም ለብቻዬ አልተወችኝም ፤ በተቃራኒው ተጠምጥማብኝ በማባበል "እኔ እሰማሀለው ፡ እኔ አምንሀለው የኔ ጌታ" እያለችኝ ከኔጋር ማልቀስ ጀመረች ።

@babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 19


.
.
.
የከንቲባው ልጅ በጣም ተጨንቃለች ። የአባቷ ስልክ አለመስራት ፣ ደብረ ዘይት ያየነው ሰውዬ ፣ ወደ ቤት ስንመለስ መብራቶቹ በርተው ማግኘታችን ፣ በቃ ሁሉም ነገር መጥፎ መጥፎውን እንድናስብ አርጎናል ። ከዚህም በላይ ደግሞ ያሳሰባት ነገር እኔን የሷ ችግር ውስጥ ማስገባቷ ነው ። አዚህ ቤት ውስጥ መሆን ይበልጥ ስለ ችግሩ እንድናስብ እንደሚያደርገን አውቃለሁ ። ይዣት ወጥቼ እንዳላስረሳት ፤ አባቷ እንዳሉትም ዛሬ የሚመጡ ከሆነ ከቤት እንዳያጧት ስለሰጋሁ ነው ። ለፖሊስ እንዳናመለክት ስለጉዳዩ ትተው ወደኛ እንደ ሚዞሮ ግልፅ ነው ። የሚከታተለንን ሰውዬ ትተው እኛን "እናንተ ማናችሁ ፣ ይሄ ቤት የማነው ፣ ይሄን ሁሉ ንብረትስ ከየት አመጣችሁ ...?" ከማለት አያልፉም ። ለጊዜው እንደ መፍትሔ ያየሁት ፊልም ማየቱን ነውና After የሚል ምርጥ የፍቅር ፊልም ሶፋ ላይ ሆነን እያየን ነው ። በመሀል በመሀል ሲሳሳሙ እየተሳሳምን ፣ ሲተቃቀፉ እየተቃቀፍን ፣ ሲጣሉ ደግሞ በመሃላችን ክፍተት እየፈጠርን በስተመጨረሻ ተቃቅፈን ፊልሙ አለቀ ። በፊልሙ ላይ ቅር ያለን ነገር ቢኖር ሲያልቅ ተዋንያን ሲፅፍ የኛን ስም አለመጥቀሳቸው ነበር ። እሱን እንደ ጨረስን ቁርስም ስላልበላን በጣም እርቦን ስለነበር ተያይዘን ወደ ኩሽና ገባን ። የጊቢ ተማሪ ሞያ + የቤት ልጅ ሞያ = ሞያሽ ሞያሽ ይዘርዘርልሽ ። ቁርስን መቀነስ ፣ ምሳን መሰረዝ ፣ እራትን ማሳነስ ብዙ ዕድሜ ለመኖር ዋስትና ነው ይላሉ ከቤተሰብ የተላከላቸውን ብር በአንድ ሳምንት የሚጨርሱ የጊቢ Non cafe ተማሪዎች ። በአለማችን ላይ በረሃብ የሞቱ ሰዎች ጥቂቶች ናቸው ። በተቃራኒው ግን በጥጋብ የሞቱት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ናቸው ። ስንቶቻችን ነን በምላሳችንና በጥርሳችን መቃብራችንን ስንቆፍር የምንውለው ...! ሆድ እንዳሳዩት ነው ፣ ወስፋታችንን መግታት ከብዶን ሁሉንም እችላለሁ ብለን አግበስብሰን ቁንጣን እስኪይዘን ድረስ የምንበላ ከሆነ መጨረሻችን እስኪሻለን ድረስ መፆም መሆኑን ማወቅ ይኖርብናል ። አንዳንድ ሰዎች "ስትበላ እንደልብ ፣ ስትጠጣ እንደልክህ" ይላሉ ። እኔ ግን እላችኋለሁ 'ሲርብህ ብላ ፣ ሲጠማህ ጠጣ' ። ፈላስፋው ሶቅራጥስም በዘመኑ "እኔ ለመኖር ስበላ ፣ ሌሎች ግን ለመብላት ይኖራሉ" ብሎ ነበር ። በዚህ ዘመን ግን ሀብታም ከሆነ በፈለገ ጊዜ ፣ ደሀ ከሆነ ደግሞ በአገኘ ጊዜ ሆኗል ነገሩ ። anyways ቤት ውስጥ ስጋ ነክ ነገሮችና እንጀራ ለጊዜው ስለሌሉ ቆንጆ ፓስታ ከከንቲባው ልጅ ጋር ተባብረን ሰርተን ተባብረን በልተናል ። ከሰዓታችንን ደግሞ መፅሐፍ በማንበብና ሙዚቃ በመስማት ልናሳልፈው አቅደናል ። ከአጫጭር የልቦለድ መፅሐፍት ውስጥ የአሌክስ አብርሃም "ዶክተር አሸብር" የሚለውን በጣም ስለምወደው እሱን ተራ በተራ የምንወደውን ርዕስ እየመረጥን አንዳችን ላንዳችን እያነበብን ከልባችን እየሳቅን ሳናስበው ቀኑ ለምሽት መንበርከክ ጀመረ ። በስተመጨረሻም ካሏት የግጥም መፅሐፍት ውስጥ አንዱን መርጬ በጣም የምወደውን አንድ ግጥም እንዳነብላት ጋበዘችኝ ። እኔ ግን Control ብፌው ውስጥ የሚታየኝን ወይን ከሁለት ብርጭቆ ጋር አውጥቼ ፣ እጇን ይዤ ከሳሎን ወደ ጊቢ ውስጥ ወጣን በረንዳ ላይ ተቀመጥንና ወይን እየጠጣን ጨረቃዋን እያየን የምወደውንና በቃሌ የማውቀውን አንድ ግጥም በዜማ እልላት ጀመር እንዲህ ብዬ

"አመሻሽ ላይ ሆኜ ፡ ሳስብሽ ሳስብሽ
በረንዳ ላይ ሆኜ ፡ አንቺኑ ስስልሽ
ስላንቺ የሚያወሳ ግጥም ስፅፍልሽ
ዕምባ ከአይኖቼ ፡ ዱብ ዱብ እያሉ
አይኔና ጉንጮቼ ፡ በዕንባ ሲሞሉ
ከሰማይ ላይ ሆና ፡ ትታዘበኛለች
እጇን በአፏ ጭና ፡ ታፈጥብኛለች
ደንገጥ አልኩኝና ፡ ዕምባዬን ጠረኩኝ
እሷም ቀስ በቀስ ፡ እኔን ቀረበችኝ
ብርሃኗ ልዩ ነው ፡ ሁሉን የሚያስረሳ
ፈዝዤ ቀረሁኝ ፡ ፎቶ እንደሚነሳ
እኔጋር ደረሰች ፡ ከዋክብት አጅቧት
መንቀጥቀጥ ጀመርኩኝ ፡ እኔም በፍርሃት
ጠጋ አለችና ፡ አይዞህ ጨረቃ ነኝ አለችኝ
አትፍራ አትሽሽ ፡ ብላ አቀፈችኝ
ኮከብ እንዳጀባት እየነገረችኝ
እንባዬን ጠራርጋ ፡ አይኖቼን እያየች
በሹክሹክታ መንፈስ ፡ ማውራት ጀመረች
አይዞህ ጠንከር በል ምንም አትሆንም
እውነት ካፈቀርቃት የትም አትሄድም
ለፍቅርክ ምስክር ፡ እሆንልሀለው
ካለችበት ሄጄ እነግርልሃለው
ያቺ ውብ ጨረቃ ቀርባ አፅናናችኝ
ለተከፋው ልቤ ደስታን ሰጠችኝ
"ጤዛ ሞቷን ሞታ ፡ ኮከብ ባናት ስትወጣ ፣
ድምፅ ወደኔ መጣ ፡ አለኝም ጠጣ
አንተ ድንቅ ፍጡር ጠጣ ፡ ወደኔ እስክትመጣ"

የሚለውን ግጥም መረኩላትና ወይናችንን እየጠጣን የጨረቃን ውበት ማድነቅ ጀመርን አይኖቻችን ግን እሷ ላይ ለመቆየት ብዙም የፈለጉ አይመስለኝም ከኛ በብዙ ሺህ እጥፍ የምትርቅ ፣ ያውም የማናገኛት ጨረቃ ላይ ከማፍጠጥ ይልቅ የቅርባችን ይሻላል ብለን አይኖቻችን ውስጥ ያለውን ጨረቃ ለመፈለግ ይመስል እርስ በእርስ መፋጠጥ ጀመርን ብዙም ሳንቆይ ህይወት ወለላዋ ፣ ነክታኝ በስምያዋ ኑር ለዘላለም ስትል ፣ ከንፈሮቿ ነፍሴን ከአፋፍ ላይ አወጧት ፣ ባይኔ እያየሁ ወደ ጨረቃዋ አከነፏት ። መቼም የማልደርስባት ፣ ማገኛት ማይመስለኝ ፣ ያቺን እሩቅ ያለች ጨረቃ አፌን በአፏ ጎርሳ አሳየችኝ ። ከንፈሬ ከንፈሯን ፈልቅቆ ሲነካው ፣ ነፍሴ ከነፍሷ ጋር ጋብቻ የፈፀሙ ነው የሚመስለኝ ። ከንፈሯ ደግሞ ለስላሳ ነው ፤ ለዘለዓለም እንድትስመው ይገፋፋል ። መሞት ካለብኝ ልሙት ፤ ሞቴ ግን ከንፈርሽ ላይ ይሁን የሚያስብል ፣ ምሽቱ ነግቶ ፣ ወፎች እስኪንጫጩ ፣ ምድርም እስክትነቃ ድረስ ልቀቁኝ የማይል ከንፈር ። (ኧረ በህግ አምላክ ልቀቃት ...
። በስንት መከራ ከንፈራችን ተላቆ አይኖቻችን ማውራት ጀመሩ ። የከንቲባው ልጅ ከብዙ ዝምታ በዋላ "በህይወቴ አንድ የማይሰለቸኝን ነገር ልንገርህ...?" አለችኝና ቀጠለች "ካንተ ጋር #24 ሰዓት ማሳለፍ ፣ እንደውም ሰዓቱ በጣም አንሶኛል ፣ ሰዓቱም ልክ ቀናቱ #365 በሆነልኝ ። ቀናቱን ሁሉ ፣ ሳምንቱን ሙሉ ፣ ወራቱን እንዳለ ፣ ዓመታቱንም እንደዛው ካንተ ጋር በሆንኩ ። ካንተ ጋር ከሆንኩኝ ሁሉም ቀን ለኔ የፍቅር ቀናት ናቸው ። አንተኮ መውደድን የማነብብህ ደብተሬ ፣ ፍቅርን የማይብህ መስታወቴ ፣ ያለ ስጋት የምኖርብህ ሀገሬ ፣ በእስትንፋስህ የምተነፍስ ንፁህ አየሬ ነክ ። ባንተ ፍቅር እንደ ጤፍ ሺህ ቦታ ብትንትን ብልም ባንተው ፍቅር ደግሞ ይኸው እየኖርኩ ነው ። በህይወቴ ውስጥ አንተን ስላገኘሁ በጣም ደስተኛ ነኝ ። በምታደርገውና በምትለኝ ነገሮች የተለየሁ እንደሆንኩ ያክል እንዲሰማኝ ታደርጋለህ ። እናም በጣም ነው የምወድህ ፤ ሁሌም ደግሞ አደርገዋለው" ብላኝ አይኖቿን ጨፍና ከንፈሬን ድጋሜ ስትስመኝ ከውጪ በሩ ተንኳኳ ። ደንግጠን ከንፈራችን ተላቆ አይኖቻችን በሩ ላይ አረፈ ። የልብ ምታችንም ከሚንኳኳው በር በላይ ይሰማናል ። እኔ ምናልባት አቧቷ ከሆኑ ብዬ ለጥንቃቄ ወይኑንና ብርጭቆዎቹን ይዤ ወደ ቤት ውስጥ ገባሁና ኩሽና አስቀምጬ ወደ ሳሎን ተመልሼ በመስኮት የሚሆነው ነገር መከታተል ጀመርኩኝ ።
@babusem
😘የከንቲባው ልጅ😘

ክፍል 20


.
.
.

ወደ ውስጥ አንድ ሰው ገባና በሩን ዘግቶ ከህይወት ጋር ጥምጥም ብለው ተቃቀፉ ። አባቷ ናቸው አልኩኝ በልቤ ። ደንግጬ ወዴት እንደ ምሄድ ግራ ገብቶኝ ወደዚያ ወደዚህ ስል አንዴ ከግድግዳ ጋር ተላተምኩና ግንባሬን እያሻሸው ወደ ከንቲባው ልጅ ክፍል ገባሁ ። ለማየትና ለመስማት እንዲያመቸኝ የክፍሉን በር ሙሉ በሙሉ አልዘጋሁም ። መብራት ግን አጥፍቻለሁ ። አባትና ልጅ ተያይዘው ወደ ውስጥ ገቡ ። ደስ የሚለው አባቷ ላለሁበት ክፍል ጀርባቸውን ሰጥተው ነው የተቀመጡት ። ህይወት ደግሞ በኔ ፊትለፊት ሶፋው ላይ ቁጭ ብላ ከፀሀይ በላይ ፈክታ በናፍቆት ወደ አባቷ እያየች ታወራለች ። "አባቢ ደና ነህ አይደል ፡ እኔኮ ተጨንቄ ስልክህ ላይ ከጠዋት ጀምሮ ስሞክር ነበር ፤ ግን አይሰራም" አለቻቸው ። አባቷም "የኔ ህይወት አመሻሹ ላይ ነው እኮ አዲስ አበባ የገባሁት ፤ እረፍት ሳልወስድ ነው በዛው በድሬ plane ወደዚህ የመጣሁት" አሏት ። "ደክሞሀል አይደል በሙቅ ውሃ እግርህን ልጠብልክ ...?" ስትላቸው "አይ ፡ ባይሆን ሻዎር ልውሰድና ብዙ የማወራሽ ነገር አለኝ" ብሏት ተነስቶ ግንባሯን ሳሟትና እኔ ወዳለሁበት ቦታ አመሩ ። ደንግጬ ከበሩ ጀርባ ተደበኩኝ ። ካለሁበት አጠገብ በቀኝ በኩል ያለው ክፍል ሲከፈት ይሰማኛል ። ባለፈው ለመጀመሪያ ጊዜ እዚህ ቤት ስመጣ የከንቲባው ልጅ "አባቴ ሲመጣ እዚህ ነው የሚያድረው" ያለችኝ ክፍል ነበር ። ከትንሽ ደቂቃ በዋላ ተመልሶ ተዘጋና ወደኔ እየቀረበ የሚመጣ የእግር ኮቴ እየሰማው አልፎኝ ሄደና በግራዬ በኩል ያለው ክፍል ተከፍቶ ወዲያው ተዘጋ ። በሆዴ 'አባቷ ሻዎር ገቡ ማለት ነው' ብዬ ሳልጨርስ በድጋሜ ወደኔ የሚመጣ የሰው ኮቴ ሰማሁ ። በቅስፈት ያለሁበት ክፍል መብራት ሲበራብኝ ባለሁበት ደርቄ ቀረሁ ። ኡፍፍፍ ፡ የከንቲባው ልጅ ነበረች ። "እዚህ ነህ እንዴ ...?" አለችኝ በሹክሹክታ ። (አያይ ፡ ኩሽና ነኝ ...) ። ስናወራ ድምፃችን እንዳይሰማ ሰግተን Telegram ገብተን txt መላላክ ጀመርን ። 'እስከ መች ነው ግን ከአማቼ ጋር ድብብቆሽ የምጫወተው ...?' አልኳት ለጨዋታው ድምቀት ። አንብባ ከት ብላ ሳቀችና መልሳ ደግሞ ደንግጣ በግራ እጇ አፏን ከድና "እኔኮ ወንድ መስለኸኝ ነበር ላስተዋውቅህ እዚህ ድረስ ያመጣሁክ ፤ አንተ ግን እንደ ሴት ጓዳ ለጓዳ ትሽሎኮሎካለህ" ብላ መለሰችልኝ ። 'ተነስቼ ሻዎር ቤት ገብቼ እንዳልተዋወቃቸው' ስላት "ወንድ ነህ አ" አለችኝ ። ወንድነት ተሰማኝ መሰለኝ ከአልጋዋ ላይ ተነስቼ ወደ በሩ አመራሁ ። በሩን ከፍቼ ልወጣ ስሞክር ምንም ሳይመስላት ቁጭ ብላ ታየኛለች ። "ኧረ ተመለሰ ቀልድ አታውቅም እንዴ ...?" የሚል ልመና ነበር የጠበኩት ። (ግን ወፍ የለም ...) ። ወደ አልጋው ተመልሼ ሥርዓቴን ይዤ ተቀመጥኩ ። የከንቲባው ልጅ ለሴኮንዶች ስልኳ ላይ አቀርቅራ ቀና ስትል ስልኬ ላይ መልዕክት ገባ ። ማንበብ ጀመርኩኝ "አየህ ፡ የብዙ ሰዎች ችግር ይሄ ነው ገላጋይን ተስፋ አድርገው ይጣላሉ ፣ ይለምኑኛል ብለው ይዳፈራሉ ፣ ይጠሩኛል የሚል አጉል ተስፋ ይዘው ይሄዳሉ አንተም እንደዛው ነው የሆንከው የኔ ጌታ የሚል ነበር (sticker እኔ ጨምሬበት አይደለም) እንዲሁ በ txt እየተበሻሸቅን ከደቂቃዎች በዋላ የሻዎር ቤቱ በር ሲከፈት ተሰማን ወዲያውኑ አባቷ "ህይወት ፣ ህይወት" እያሉ መጣራት ጀመሩ የሲሊፐር ድምፅም "ጣ ጣ" እያለ እኛ ወዳለንበት ክፍል እየቀረበ መጣ
በብርሃን ፍጥነት እኔ ከአልጋው ላይ ተነስቼ በሩ ጀርባ ስደበቅ የከንቲባው ልጅ ደግሞ ተስፈንጥራ በሩን ከፍታ ደጃፋችን ላይ የደረሱት አባቷ ወደ ውስጥ እንዳይገቡ በሩ ላይ ቆማ "አባዬ ክፍል ተሳስተሃል ቀጣዩ እኮ ነው ያንተ" አለቻቸው በፍርሃትና በሚንቀጠቀጥ ድምፅ "እሱማ መች ጠፋኝ ከሳሎን ሳጣሽ ጊዜ ነው የጠራውሽ" አሏትና ወደ ክፍላቸው ሄዱ ህይወት በረጅሙ "ኡፍፍፍ" ብላ ተነፈሰች ፤ እኔም እንደዛው "ከዚህ ክፍል ንቅንቅ እንዳትል" የሚል ማስጠንቀቂያ በጆሮዬ እያንሾካሾከች ሰጠችኝና ወደ ሳሎን ተመልሳ ተቀመጠች ያለሁበት ክፍል በር እንደ ቅድሙ ሙሉ በሙሉ አልተዘጋም ሳሎን ውስጥ የሚደረገውን ማየትም መስማትም እችላለሁ አባቷ ከደቂቃዎች በዋላ በለሊት ልብስ ከክፍላቸው ወተው ወደ ሳሎን ተመለሱ ። ትልቅ ሰው ናቸው እድሜያቸው በግምት ወደ #40 ዓመት ይጠጋል አሁንም እንደ ቅድሙ ጀርባቸውን ሰተውኝ ተቀመጡ "እስቲ ሂጂና ወይን አምጪልኝ!" አሏትና ወይን ከነመጠጫው ይዛላቸው ተመለሰችና እየቀዳችላቸው "አባቢ ቅድም እኮ ብዙ የማወራሽ ነገር አለኝ ብለህ ነበር ። ምንድነው እሱ ?" ብላ ጠየቀች ። "እይውልሽ የኔ ህይወት" ብለው ንግግራቸውን ጀመሩ "አንደኛው ነገር ፡ እንደ ምታውቂው የከንቲባነትን ስራ የጀመርኩት የዛሬ አራት ዓመት አካባቢ ነበር እናም በየ #4 ዓመቱ ሌላ ዓዲስ ከንቲባ ይመረጣል በዚህም መሠረት የኔ የስልጣን ጊዜ ቆይታ ተገባዶ ወደ ሌላ ሰው የሚያልፍበት ሰዓት ላይ ደርሷል ስለዚህ ከቅርብ ቀን በዋላ እኔ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ አይደለሁም ማለት ነው" ሲሏት ህይወት በደስታ ዘላ ተጠመጠመችባቸው አባቷ ንግግራቸውን ቀጠሉ ፡ "የኔ ህይወት ኢትዮጵያ ውስጥ ባለስልጣን መሆን ክብደቱ ከስራው ይልቅ አንዴ ገብተውበት የስልጣን ጊዜውን ሳይጨርሱ ለመልቀቅ መሞከሩ ነው የዛሬ #4 ዓመት ያኔ ልክ አንቺላይ የግድያ ሙከራ እንዳደረጉ ስራውን ለቅቄ ይዤሽ ከሀገር ለመውጣት አስቤ ነበር ግን ስልጣኑን የተረከብኩበት ጊዜ ስለነበር ሁሉም ነገሮች በኔ እጅ ውስጥ ሆነው ስለተጀመሩና ሴኔቱ እንዳለ የኔን መልቀቅያ ወረቀት ውድቅ ስላደረገው ምንም ማድረግ አልቻልኩም ለማንኛውም አሁን እሱን ተይና ከአሁን ሰዓት ጀምሮ እኔ ያንቺና ያንቺ ብቻ ነኝ ። ሁለተኛው እና ዋነኛው ነገር ደግሞ" ብለው ቀጠሉ "የኔ ህይወት አሁንም ለኔና ላንቺ እዚህ መኖር አደጋ ሊኖረው ይችላል ከሰዎቹ ጋር ችግር ውስጥ መግባት አልፈለኩም ። ክፉ ሰው የተቀጣው ክፉ የሆነ ቀን ነው እነሱን ብበቀል ያንቺ ህይወት ያሳስበኛል ትቻቸው እዚህ ብኖር ደግሞ ምናልባት ያንቺን በህይወት መኖር ካወቁ ሊነጥቁኝ ይችላሉ ያኔ አንቺን ለመግደል ብለው አቤል ላይ የተኮሱት በወቅቱ እኔ ስልጣን ላይ ከወጣሁ በዋላ በከፍተኛ የሀላፊነት ወንበር ላይ የተቀመጡት ሰዎች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ይሄን ፍቅር የሆነ ምስኪን የድሬዳዋ ህዝብ እየበዘበዙ ነበር ። እነሱን ግማሹን ከስልጣን ላይ አንስቼ ሌላ ሰው ስተካና ለቀሩት ደግሞ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ስሰጣቸው ነበር ባንቺ ፋንታ አቤል ላይ ጉዳቱ የደረሰው ከቅጣት ሁሉ የበለጠ ቅጣት ጠላትሽን መግደል አ

​​ይደለም ፤ እሱ አብልጦ የሚወደውን እና የሚኖርለትን ነገር ማሳጣት እንጂ ለዛም ነበር እኔን ትተውኝ አንቺን ለማጥፋት የተነሳሱት" ስለዚህ ከዚህ ሀገር ወተን መሄድ ግድ ነው በቅርቡ ተያይዘን አሜሪካ ሄደን በነፃነት እንኖራለን" አሏት
.✎ @babusem
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 14


.
.
.
ብዙም አልተኛሁም ነበር ። በትካዜና በሀዘን እንደ ዳግም ምፅአት የራቀኝ ለሊት ነጋ ። የኔስ ይሁን የራሴ ችግር ነው ። የከንቲባውን ልጅ ግን ለማዝናናት ይዤ መጥቼ ቀኗን አበላሸሁ ። ጠዋት ከእንቅልፍ ሳይሆን ከአልጋው ላይ ስነሳ "ደና አደርክ የኔ ጌታ ፡ ቁርስ ቀርቧል እሺ ቶሎ ፊትህን ታጥበህ ና" አለችኝ ። ቁርሱን ከበላን በዋላ 'ትናንት እንደዛ ስለ ሆንኩብሽ በጣም ይቅርታ' ስላት "ኧረ አያሳስብም ፡ እኔ ከዛ በላይ ሆኜብህ አልነበር እንዴ ፡ ባይሆን ካሁን በዋላ እንደዛ አትሁን እሺ ፡ የሰውን እምባ ጠርገው እያሳሳቁ የምን ለራስ ማልቀስ ነው ...?" አለችኝ በአሽሙር መልክ ። ቀጥላም "ካሁን በዋላ እንደውም ከቴዲ አፍሮ ሙዚቃ #ማራኪዬ የሚለውን ሳይሆን #መማፀኔ የሚለውን መውደድ ያለብክ ይመስለኛል" አለችኝና ድምጿን ከፍ አድርጋ ዘፈኑን ታዜምልኝ ጀመር ።

"በደለኛ ሰው ይቅርታ ብሎ አንሶ ሰው ከካሰ ፡
ይኖር ወይ ልቡን ያልመለሰ ፣
ሳይገባኝ ለኔ ፡ የቱጋ እንደሆን እንኳን ማስቀየሜ
ተይ ብያት ነበር ባለኝ አቅሜ ።
መማፀኔ ፡ ማሪኝ ማለቴ ፡
ለኔስ ሳይገባኝ ነው ጥፋቴ ፣
ታድያ እንዴት ይሆን ፡ ወዳጅን ነግሮ ፡
ልብን መመለስ ወደ ድሮ" ።

ቆሜ ነበር ያጨበጨብኩላት ። ስትዘፍን ድምጿ ስያምር ። በቃ ሴቷ ቴዲ አፍሮ ብያታለሁ ። "ከቤት ስለማልወጣ ስዕልና ሙዚቃ እቤት ውስጥ እሞክራለሁ ። እስካሁን አባቴ ከሰጠኝ ስጦታዎች መካከል በጣም የምወደው ጊታር'ን ነው ። ሲከፋኝና ብቸኝነት ሲሰማኝ በጊታሬ እዘፍናለሁ ። አንተ ከመጣህ ወዲህ ብቸኝነት ስላልተሰማኝ ነው እሺ ጊታሩን አውጥቼ ያልተጫወትኩት" አለችኝ እያሾፈችብኝ ። ከዛን "ስማኝማ ፡ ዛሬ ማክሰኞም አይደል ፡ ደብረ ዘይት ላይ የመጨረሻ ቀናችን እኮ ነው ። ታውቃለህ አባዬ ባለፈው ሀሙስ ነበር ሳምንት እመለሳለሁ ብሎ የሄደው ። እና ሳምንቱ ደግሞ ከነገ ወዲያ ስለሆነ ነገ ወደ ድሬዳዋ መመለስ ይኖርብናል" አለችኝ ። በግልጽ ባትነግረኝም ለማለት የፈለገችው ነገር ገብቶኛል ። የዙሪያ ጥምጥሙ ፍቺ ፈታ እንበል የሚል መሆኑ ነው ። ከዛ በፊት ግን ልጠይቃት ብዬ የረሳሁትን ነገር የአባትዋን ስም ስታነሳ ትዝ አለኝ ። 'ስሚማ ፡ አባትሽ ግን ለምን ይሄን ሁሉ ዓመት ለብቻሽ በአንድ ቤት ውስጥ እንዳስቀመጠሽ እኮ በግልጽ አልነገርሽኝም...? ፡ ማለቴ አባትሽ በስልጣኑ ምክንያት ከሰዎች ጋር ችግር ውስጥ ገብቶ አንቺላይ ጥቃት እንዳይደርስ ከፈራኮ አንቺን በአንድ ቤት ውስጥ ከማስቀመጥ ይልቅ ወደ ውጭ ሀገር መላክ ይችል ነበር ' አልኳትና ጠየኳት ። እሷም "የመጀመርያው ፡ አባቴ ብቻውን ስላሳደገኝ ፣ ከኔ ውጪ ማንም ስለሌለውና ከኔ ተለይቶ መኖር ስለማይችል ነው ። ሁለተኛው ፡ ውጪ ቢልከኝም እዛ ማንም ስለሌለን ከፈረንጅ ነፃነት የሀገር ውስጥ እስረኛ መሆን ይሻላል ብሎ ነው ። ያው 'ከማያውቁት መላክ ፡ የሚያውቁት ሰይጣን ይሻላል' ይባልም የለ ። ሲጀምር እሱ ሂጂም ቢለኝ ከሱ ተለይቼ ውጪ ሀገር መኖር አልፈልግም" አለችኝና ሶስተኛው ብላ ልትቀጥል ስትል 'ኧረ ይበቃል ፡ ሶስተኛ ፣ አራተኛ እያልሽ ከቀጠልሽማ ሳንዝናና መሽቶ መንጋቱ ነው' አልኳትና ይዣት ተነሳን እና ከአንዱ ምግብ ቤት ገብተን ምሳ ከበላን በዋላ "ፍቅር ግን ለአንተ ምንድነው...?" አለችኝ የከንቲባው ልጅ በልጅቷ የቅድሙ መልስ እንደኔው ተገርማ ። 'እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም ብያንስ አንድ ጊዜ አፍቅረናል ። እንደውም አብዛኞቻችን የፍቅርን ትርጉም ሳናውቅ ነው ያፈቀርነው ። anyways ፍቅር ግን ለኔ ...! አንድ ወንድና ሴት ተፈላልገው የሚመሰርቱት ግኑኝነት ...? ፡ እሱ ነው ፍቅር ...? ፡ አይመስለኝም ። እስቲ ወይ የራስሽን ወይንም ደግሞ የጓደኛሽን የፍቅር ታሪክ ለትንሽ ደቂቃ አስቢው ። እያሰብሽው እንደሆነ ተስፋ አለኝ ። እርግጠኛ ሆኜ የምነግርሽ እራሳችንን ወደን እንጂ ሰውን አፍቅረን አናውቅም ። እንዴት...? ለምትዪኝ :- በመጀመሪያ ወንድ ከሆነ አንዲት ሴትን ፡ ሴት ከሆነች ደግሞ የሆነ ወንድ ፡ በሆነ አጋጣሚ ያገኛሉ ። የሆነ ነገሯ ይማርከዋል ፡ #90% መልኳ ፣ አካሄድ ፣ አለባበስ ፣ አነጋገር ፣ ወዘተ ። ይተዋወቃሉ ፡ ሊግባቡም ላይግባቡም ይችላሉ ። ጉዳዩ እሱ አይደለም ። ከጥቂት ቀናት በዋላ ፡ ካላገኘዋት ፣ እጄ ካላስገባዋት ፣ የኔ ካልሆነች ፣ ህይወቴ ካለሷ ባዶ ነው ፣ ወዘተ ማለት ይጀምራል ። እዚህ ጋር ልብ በይ እንግዲህ ። አነዚህን ነገሮች እያለ ያለው ለልጅቷ አስቦና ተጨንቆ አይደለም ፡ ለራሱ ፍላጎት እንጂ ። ስለናፈቀችው ፣ ደስ ስላለችው ፣ ስለምታምር ፣ ከሷ ጋር ከሆነ ደስተኛ እሆናለሁ ብሎ ስለሚያስብ ፣ ባጠቃላይ ልጅቷ ትሆነኛለች ብሎ እንጂ ፡ ለልጅቷ እሆናታለው ፣ ብሎ አይደለም ። አስተውይ ፡ መጀመሪያ ላይ አፈቀርኳት ብሎ ሲያወራ የሱ ህይወት ካለሷ ባዶ ሆኖ ስለተሰማው እንጂ የሷ ህይወት አሳስቦት አይደለም ። የሱ ጭንቀት እንጂ የሷ ፍላጎት አልታየውም ፤ አያውቅምም ። በቃ በዛ ሰዓት እሱ የሚፈልገው ነገር ቢኖር ልጅቷ የሱ እንድትሆን ነው ። የሱ ብቻ ። እሷ እንኳን የሌላ ሰው ሆና ማየቱ ይቅርና ሰላም እንኳን ቢሏት ካልገደልኳቸው ሊልም ይችላል ። እሷን ከራሱ ውጪ ከሌላ ሰው ጋር ለሴኮንድ እንኳን ማሰብ አይፈልግም ። እሷ አልፈልግህም ብትለው እንኳን በግድ ካልሆንሽ የሚል ጉድ ውስጥም ሊገባ ይችላል ። አስቢ ይሄን ሁሉ እያደረገ ያለው ለራሱ ሲል ነው ። ይሄንን ነው እንግዲህ ፍቅር ብለን የጠራነው ። እመኚኝ ግን ከዚህ ሰው በላይ እራስ ወዳድ ሰው በምድር ላይ የለም ። የፍቅር ትርጉም ግን ይህ አልነበረም ። ፍቅር ከራስ አልፎ ለሰዎች ሁሉ መኖርና መሞት ነው ። ቢተያዩም ባይተያዩም ፣ ብታምርም ባታምርም ፣ ለሱ ህይወት አስፈላጊ ሆነች አልሆነች ፣ እውነተኛ ልብ ካለው ያኔ የእውነት ፍቅር ከልቡ ይገባል ። በአይኑ ሳይሆን በልቡ ማየት ሲጀምር እሱ ሳይፈልገው ቤቱ ድረስ መጥቶለት ደጁን ያንኳኳል ። አፍቃሪ መሆን ከፈለገ ከልቧ ውጪ ምኗንም ሳያይ ፣ ምንም ሳታደርግለት ፣ ብትበድለው ብትክሰው ፣ ለሱ ሆነች አልሆነች ፣ ባጠቃላይ የሷ ነገር አሳስቦት እንጂ የሱ ጎዶሎነት ተሰምቶት አይውደድ ። ለጎዶሎው ብሎ ካፈቀረ አንድ ቀን እንዳልተሟላለት አስቦ ሊተዋት ይችላል ። የሷን ጎዶሎ ሊሞላ ቢሯሯጥ ግን አትራፊ ይሆናል ። ቅዱሱ መፅሐፍም "ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው" አይደል የሚለው ። ክርስቶስስ ከሰማይ ላይ ወርዶ የሰውን ስጋ የለበሰው ለራሱ ጥቅም ይመስልሻል ...? ፍቅር መጠቀም ሳይሆን መጥቀም ነው ። እውነተኛ አፍቃሪ በነገሮች ሁሉ ቅድምያ ለራሱ ሳይሆን ለሌላ ሰው ሰጥቶ የሚጠቅም እንጂ የራሱን ችግር ለማሸነፍ ብሎ በሌሎች የሚጠቀም አይደለም...
"አንተ ልጅ ግን ሰባኪ ነገር ነህ እንዴ ...?" አለችኝ ሳወራላት የነበረውን ሁሉ በተመስጦ አይን አይኔን ትኩር ብላ እያየችኝ ከሰማችኝ በዋላ ። ቀጥላም "ቆይ ግን አንተ ሴት ልጅን መተህ አታውቅም ...?" አለችኝና ብዙ ዓመት ወደዋላ እንድመለስ አረገችኝ ። 'ትዝ ይለኛል እንደ ትናንት ፡ ከ #10 ዓመት በፊት በ #2001 ዓ.ም #4ኛ ክፍል እያለሁ ነበር ። #6ኛውን period ተምረን ተደወለ ። ምሳ ሰዓት በመሆኑ ፣ እቤታችንም ለት/ቤቱ ቅርብ ስለነበረ ወደ ቤት ለመግባት ቦርሳዬን ይዤ ከ desk ላይ ተነሳሁ ። ነገር ግን አጠገቤ ትቀመጥ የነበረችው አቢጊያ የምት
😘የከንቲባው ልጅ😘

🔥ክፍል 17


.
.
.
"ሰዎች መሞት አይፈልጉም ነገር ግን ፣
መንግሥተ ሰማይ መግባት ይፈልጋሉ ።
ንሰሐ አይገቡም ግን ሁሉንም የሰፈር ዕድር ገብተዋል"።

ሲመስለኝ አሁን ሞት ለ #3ተኛ ጊዜ ነገር እየፈለገኝ ነው ። የከንቲባው ልጅ ከመፍራቷ የተነሳ ጥቅልል ብላ ደረቴ ውስጥ ሽጉጥ ብላለች ። ("ሞት ርስት ነው ፤ መፈራቱስ ለምንድነው ...?") ። የጠረጠርነው ሰውዬ ይመጣ ይሆን እያልን በጉጉት (ይቅርታ በፍርሃት...😬) እየጠበቅን ነው ። እስካሁን ግን ምንም ነገር ሳናይና ሳንሰማ ቀኑ ወደ ምሽት ተለወጠ ። ሁሉም ነገር ፀጥ ረጭ ብሏል ። እኛም ድምፃችንን ብቻ ሳይሆን ትንፋሻችንን ጭምር አጥፍተን ኩርምት ብለን ተቀምጠናል ። በድንገት ሳናስበው በራችን ሲንኳኳ ሁለታችንም ከአልጋው ላይ ተስፈንጥረን ተነሳን ። ቀስ ብዬ ወደ በሩ አመራሁና 'ማ ማ ማነው...?' አልኩኝ በተንቀጠቀጠ ድምፅ ። "እኔ ነኝ" አለ ድምፁ አዲስ ያልሆነብኝ ሰው ። 'አንተ ማነህ ፡ ስም የለህም' አልኩት ፈራ ተባ እያልኩ ። "እኔ ነኝ የናንተን የዕንግድነት ቆይታና መስተንግዶ የምከታተል" አለን በትህትና ። ሁለታችንም በሀይል ኡፍፍፍ አለንና በሩን ከፈትኩለት ። "ዛሬ ምነው ድምፃቹ ጠፋ ፡ ምሳ ላይም አልነበራቹም ፡ እራቱንም ልትዘልቁበት አስባቿል እንዴ ...?" አለን በተለመደው ትህትናና ፈገግታ ። የእጅ ሰዓቴን ሳይ #01:33 ይላል ። እራት እዚው እንዲያ መጣልን ነግሬው እጅ ነስቶ ተመለሰ ። ብዙም ሳይቆይ ምግብ ከወይን ጋር ይዞ መጣ ። የምግብ ፍላጎት ባይኖረንም ነገ መንገደኛ በመሆናችን እንደ ነገሩ አድርገን ከላይ ትንሽ ወይን ከለስንበት ። በስተ መጨረሻም የእስካሁኑን ሙሉ ወጪ አስደምረን ከፍለንና አመስግነን ከአስተናጋጁ ጋር ተለያየን ። ለነገ ጠዋት #12:00 ሰዓት Alarm ሞልተን አንሶላ ውስጥ ገባን ። "ሞት ወደ ትጉህ ነፍስ ፣ እርጅናም ደግሞ ወደ አፍቃሪ ልብ አትመጣም" በሚለው ቃል እራሳችንን አሳምነን ተኛን ። ጠዋት ነግቶ Alarm እኛን ሳይሆን እኛ አላርሙን ቀስቅሰነው ከውቢቷ ደብረ ዘይት ከተማ ወደ በረሃዋ ንግስት ድሬዳዋ ጉዞ ጀመርን ። አዲስ አበባ ፣ አዳማ ፣ አዋሽ ፣ መታሃራ እያለን ሂርና ደረስን ። ወርደን ምሳችንን ዕሮብ በመሆኑ ቆንጆ በየ አይነት በልተን ጉዞ ቀጠልን ። ከዋላችን ከተለመዱት የጭነትና የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችና ሚኒባሶች ውጪ የተለየ አይነት መኪና ስላላየን ውስጣችን ለጊዜው ሰላም ተሰምቶታል ። ሙቀቱንና የመንገዱን አሰልቺነት ተቋቁመን ፣ የደንገጎን አስፈሪ ተራራማ zigzag ቁልቁለት መንገድ ወርደን #11:00 ሰዓት አካባቢ ድሬዳዋ ገባን ። ለጥንቃቄ ብለን ቀስ ስላለች እንጂ የሸገር ድሬ መንገድ ለትክክለኛው ሾፌር ከ #9 ሰዓት አያልፍም ። Tata የሚባሉት አውቶብሶች ግን በጣም ደካማ ስለሆኑ ጠዋት #12:00 ሰዓት ከሸገር ተነስተው ምሽት #03:00 ሰዓት ድሬ የሚገቡበት ሰዓት ይበዛል ። ለጊዜው ድሬዳዋ ራስ ሆቴል አርፈን እራት እዛው በልተን ትንሽ አምሽተን ወደ ከንቲባው ልጅ ቤት በከዚራ በኩል አድርገን አቀናን ። የቀድሞ ቤቷና የአባቷ መኖርያ ቤት አካባቢ ስንደርስ መኪናውን አቆመችና ለትንሽ ደቂቃ ትኩር ብላ በቁጭት አየችው ። እምባዋ ጉንጮቿ ላይ ሳይራመዱ ታፋዋ ላይ ዱብ ዱብ ማለት ሲጀምሩ ፤ አይኗን ከቤቱ ላይ ነቀለችና እምባዋን ዋጥ አድርጋ መኪናውን አስነስታ ወደ ራሷ ፣ ከአባቷ ውጪ አንድም ሰው ወደ ማያውቀውና ዝር ወደማይልበት ቤት አመራን...
ከምሽቱ #02:00 ሰዓት አልፏል ። የከንቲባው ልጅ ቤት ደርሰን የውጪኛውን በር ከፍተን ገብተን ፣ መኪናዋንም ጊቢ ውስጥ አቁማ ወደ ውስጥ ገባን ። የሳሎንና መኝታ ክፍሏ መብራቶች በርተው ነበር የጠበቁን ። ትዝ ይለኛል ስንወጣ አጥፍተን ነበር ። ህይወት ዞር ብላ በፍርሃት ታየኝ ጀመር ። "አጥፍተን ነበር አ የሄድነው ...?" አለችኝ ። እራሴን በአዎንታ ወደላይ ወደታች ነቀነኩኝና 'አባትሽ የዚህን ቤት ቁልፍ አላቸው እንዴ ...?' አልኳት ባለፈው ሲመጡ በር ላይ ነኝ ብለው ስለደወሉላት ። "አዋ አለው ፣ ባለፈው ሲመጣ ረስቼ ነው ብሎኛል" አለችኝ ። ከእሷና ከአባቷ ውጪ ቁልፉን ማንም ከሌለው ፣ በዛላይ አባቷ እንዳሉትም ሀገር ውስጥ ከሌሉ ፣ በተጨማሪም ቢሾፍቱ እያለን ካየነው ሰውዬ ጋር ሲደማመር የሆነ ችግር እንዳለ በግልጽ ተሰማኝ ። "ይሄኔ ነው መሸሽ" አለ ያገሬ ሰው ፤ አሁን ገና ፍርሀት የሚባለው ስሜት አካሌን ወረረው ። "ሞት ላይቀር ፍርሀት ፤ አመል ላይቀር ቅጣት" ። "ፈሪ ውሃ ውስጥ ሆኖ ያልበዋል" ፤ እኛ ግን የጦርነት ቀጠና ውስጥ ሆነን ደርቀናል ። "ፈሪ ከአልጋ ላይ ወድቆ ይሞታል" ፤ እኛ ግን አልጋ ላይ የመውጣት አቅምም የለንም ። "ፈሪ የሚያባርረው ሳይኖር ይሸሻል" ፤ እኛ ግን የሚያባረን እያለ ካለንበት መንቀሳቀስ ከብዶናል ። ሞት በየሁሉም ሰው በራፍ ላይ የሚቆም ጥቁር መላክ ነው ። እኛም ቤቱን ፈትሸነው ባዶ መሆኑን ስናረጋግጥ ይህ በራፋችን ላይ የቆመው የሞት መላክ እንዳይወስደን በሩን ሁለት ጊዜ ቆለፍነው ። ተስፋና ፍርሀት ሁሌም አይነጣጠሉም ። ፍርሃት ያለ ተስፋ ፣ ተስፋም ያለ ፍርሃት አይኖርም ። ፍርሃትን የሰጠ አምላክ ፡ ተስፋንም አይነፍግም ። "ተስፋ ያልቆረጠ መነኩሴ ምናኔ ሲሄድ ሴቲቱን ይሰናበታል" አሉ አበው ። እኛም ምንም እንኳን ወደሞት እየሄደን ቢመስለን በምድር ተስፋ አልቆረጥንም ። አባቷ መጥቶ ከሆነ ብለን በሀገር ውስጥ ስልኩ ላይ ስትደውልለት "የደወሉላቸውን ደምበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም..." አለች የቴሌ ሰራተኛ ። በጣም ተጨንቀናል ። ጭንቀታችን በከንቱ ይሁን አይሁን ግን አናውቅም ። ከመተኛታችን በፊት ከጊቢ የዶርም ጓደኛዬ ደውሎልኝ ነገ ትምህርት እንደሚጀምር እና class ባልገቡት ተማሪዎች ላይ እርምጃ እንደ ሚወሰድ ነገረኝ ። ስልኩ speaker ላይ ስለነበር ያለኝን ነገር የከንቲባው ልጅም ሰምታለች ። አንድ ሶፋ ላይ ሆነን የመረቀነ የድሬ ልጅ መስለን አይናችንን አፍጥጠን እየተያየን የዕሮቡ ለሊት ለሀሙሱ ጀምበር እጁን ሰጠ ። ስንት ሰዓት እንደ ተኛን አላውቅም ። እራሳችንን እዛው ሶፋ ላይ ተቃቅፈን አገኘን ። አዲስ ነገር ካለ ብለን ቤቱንና ጊቢውን ፊትሽነው ። ሁሉንም ነገር ግን ትተነው እንደ ተኛን አገኘን ። ትንሽም ቢሆን ተረጋግተን "በቃ አንተ ወደ ጊቢ ተመለስ ፡ በኔ ምክንያት ትምህርትህን እንድታጣ አልፈልግም ። እስካሁን ድረስ ለኔ ያደረከው እራሱ ከበቂም በላይ ነው" አለችኝና ልትሸኘኝ ወደ ጊቢው ወጣን ። እኔም እቅፍ አረኳትና 'አይዞሽ እሺ ምንም አይፈጠርም ። ደግሞ ብዙም አልቆይም ፡ ፍቃድ ብቻ ጠይቄ ነው የምመልሰው እሺ' አልኳትና ስታለቅስ ላለማየት ብዬ በፍጥነት ወደ ውጪኛው በር አመራሁ ። ልክ በሩን ስከፍት "ትተኸኝ በዛው እንዳትቀርብኝ እሺ የኔ ጌታ ፣ ብቻዬን እፈራለሁ ፣ ደግሞም ማንም እንደሌለኝ ታውቃለህ አይደል...?" አለችኝ ልክ የመጀመሪያው ቀን ስንገናኝ "ትተኸኝ አትሂድ ፡ ማንም ሰው የለኝም" ባለችኝ ዜማ ። ዞር ብዬ ሳያት ፊቷ በዕምቧ እየታጠበ ነው።
😘የከንቲባው ልጅ😘

🔥ክፍል 22
.
.
.
ቶኒ በር ላይ ፈታሾቹ ከኔ ምንም ላያገኙ ፈትሸውኝ ፣ በርብረውኝና ዘቅዝቀውኝ ምንም ነገር ሲያጡ ወደ ውስጥ አስገቡኝ ። እና አሁን ያ አመዳም ጊቢ ውስጥ ነኝ ። እንዴት እንደ ሚያስጠላኝ አጠይቁኝ ። (እንግዲህ በግድ ከጠየቃችሁኝ ምን ይደረጋል...🙆) ። ገና በቶኒ በር ስገባ ጀርባዬን ያሳክከኛል ። ብታዩት Campus ሳይሆን የአዋራ ፋብሪካ ነው የሚመስለው

​​። በዛላይ በጣም ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ ከዶርም ወደ cafe ስንሄድ ከመኝታ ቤት ወደ ሳሎን የሄድን ነው የሚመስለኝ ። ዶርም ሆነን ከሴቶች ጋር ማውራት ከፈለግን እኮ መስኮት መክፈት ብቻ ነው የሚጠበቅብን ። መሀል ላይ በቆርቆሮ አጥር ቢለያዩንም ከወንዶች ዶርም ጋር face to face ስለሆኑ ጎረቤቶቻችን ናቸው ብል ማጋነን አይሆንም ። እንደውም አንዳንድ ጊዜ ቺኮቻችን ሲደብራቸው መስኮት ከፍተው ይደበሩብናል ። professional የሆኑ የ GC ወንድ ተማሪዎች ደግሞ ጭራሽ micraphone ገዝተው ለሁሉም ዶርሞች እንዲዳረስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ ። አልፎ አልፎ ግን ወደ ሴቶቻችን ዶርም ስንመለከት ከ #18 ዓመት በታች ለሆኑ የተከለከለ ነገር እናያለን ። ከሙቀቱ የተነሳ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዶርም ውስጥ ልብስ መልበስ አቁመዋል ። ለነገሩ የድሬ ሙቀት እንኳን ልብስ ቆዳም ያስገፍፋል ። ሻዎር ውስጥ ስትገባ እንኳን fan ያስፈልግሃል ። አየሩ ፣ ውሃው ፣ መሬቱ ፣ ከሰው በስተቀር ሁሉነገሩ የተመታ ከተማ ። በቶኒ በር ገብቼ ፣ ፍቅር cafe ፣ cenrtal library ፣ የሴቶች ዶርም እና senior cafe'ን አልፌ ፣ ወደ ወንዶች ዶርም ዘለኩኝ ። ጊቢው ያለወትሮው ጭር ብሏል ። ጥሎበት ደግሞ ተማሪ ከሌለበት ሲኦል ነው የሚመስለው ። (አንተ ልጅ ደግሞ አንዳንዴ ታበዛዋለህ ፡ ሲኦልን ደግሞ መች አየሃት ...?) ። የተመደብኩበት block ደርሼ ፣ የዶርሜን በር (white house F #45) ከፍቼ ገባሁ ። እንዴት እንደ ሚያስጠላ idea'ው የላቹም ። ተሳስቼ ሽንት ቤት የገባሁ ነበር የመሰለኝ ። ዶርም መሆኑን ያወኩት አልጋና ሎከር በመኖራቸው ነው ። ከሁሉም ግን ድንቅ የሚለኝ ፡ ሽንት ቤቶቹ እንዳለ ቀለም ተቀብተዋል ። የምናድርበት ዶርም ግን ለመጨረሻ ጊዜ ቀለም የተቦረሸው ለመጀመሪያ ጊዜ ይሄ ጊቢ ሲመሠረት ነው ። ግድግዳው የወፍጮ ቤት ይመስላል ፣ ፍራሾቹ ደርቀው ከድርቆሽ በላይ ጠንክረዋል ፣ ሎከሮቹ ተሰባብረው የማገዶ እንጨት መሥለዋል ፣ ኮርኒሱ ኩሽና ይመስል ጠቁሮ የጨለመ ሰማይ ሆኗል ፣ ሊሾው አፈር ለብሶ ወደ መሬትነት ተለውጧል ። በቃ ምን ልበላችሁ ...? ፡ ዶርሙ ከዶርምነት ተራ ወጥቶ ዱሪዬ ዶርም ሆኗል ። እዚህ ውስጥ እየኖርኩማ እንኳን ትምህርት ሊገባኝ ቀርቶ እንቅልፍ እራሱ የሚወስደኝ አይመስለኝም ። አማራጭ የለኝም ፤ ጠልቼ በግድ አንዴ ገብቼበታለሁ ። በጣም ደክሞኝ ስለነበር ፣ በዛላይ ጊቢው ስለዘገነነኝ ዶርሜን ዘግቼ አልጋ ላይ ፌንት ሰራሁ ። (ፌንት ግን ይሰራል ወይስ ይወደቃል ...?) ። ይሄን የመሠለ ዶርም ውስጥ ሆኜ በየት በኩል እንቅልፍ ይውሰደኝ...? ። anyways ቤት ሳይሆን ዱር እንዳደርኩ እቆጥራለሁ ። ኧረ ዱር እራሱ በስንት ጣዕሙ ። እውነት አያ ጅቦ እዚህ ቢመጣ "እኔን ፡ እኔን ፡ ምን ሆነክ ነው ጎዳና ላይ የምታድረው...? ፡ በል ተነስና ወደ ቤቴ ልውሰድክ" እንደ ሚለኝ አልጠራጠርም ።

የዶርም ልጆች class ሄደዋል መሠለኝ ሁሉም የሉም ። ሙሉ ብሎኩም ባዶ ነው ። አንዳንዴ ግን ከጦርነት በላይ ፀትታም ያስፈራል ። እንደዚህ አይነቱ ቀንማ ዳዊት ካልደገሙበት በስተቀር የሚያልፍም አይመስልም ። (እሺ ሊቀ ጠበብት ተስፋዬ ...) ። anyways የዛሬው እቅዴ እስከ ከሰዓቱ ፈተና ድረስ መተኛት ነው ። በህልሜ የማቴሪያል ትምህርት መፃፍ ካገኘሁ አጠናለሁ ። ካልሆነ ግን በፈተናው ላይ ለሚ ብዛት ሀላፊነቱን አልወስድም ። ብዙም ሳልቆይ ግን ዶርም የነበርኩኝ ልጅ ማን እዚህ ቦታ እንዳመጣኝ ሳላውቅ ሌላ ቦታ ላይ እራሴን አገኘሁ ። ለመጨረሻ ጊዜ ትዝ የሚለኝ ነገር ቢኖር 'የሰላም እንቅልፍ ጣልብኝ ፈጣሪዬ' ብዬ መተኛቴን ነው ። አሁን ግን አልጋ ሳልሆን መሬት ላይ በተነጠፈ ምንጣፍ ላይ እግሮቼን አጣምሬ ፤ በብዙ ወንዶችና ሴቶች ተከብቤ ነው ያለሁት ። ጆሮ ደግፍ የያዛቸው ይመስል ጉንጫቸው የሌለ አብጦ ፣ አይናቸው ቆንጆ ኮረዳ የሾፈ ይመስል ተጎልጉሎ ወጥቶ ፣ ጥርሳቸው ሳር የጋጡ ይመስል የላይኛው የኢትዮጵያ ባንዲራ ቀለም መስሎ ፣ ባጠቃላይ የሀገሪቱን የመብራት መቆራረጥ ችግር ይፈቱ ይመስል ባንድላይ እየጮኹና እያሽካኩ ያቺን ጠባብ ቤት ሊያፈርሷት ምንም አልቀራቸውም ። የአንዳንዶቹ ፊት ለኔ አዲስ አይደሉም ። እንደውም ወደ ቀኝ ዞር ስል በታሪክ እዚህ ቦታ ላይ አገኘዋለሁ ብዬ የማላስበውን ልጅ አይቻለሁ ። ያው እኔም እዚሁ ከሱጋ ስለሆንኩኝ አላዘንኩለትም ። እዚህ ቦታ ላይ መተፋፈር የለም ። አሜሪካ በሏት ። ጫት ፣ ሲጋራ ፣ ሺሻ ፣ ሴት ፣ ወንድ ፣ ዊድ ፣ ጋንጃ ፣ ከቦብ ማርሌይ ውጪ ምን የሌለ ነገር አለ...? ። እየቃምኩ መሆኔን እስካሁን አላመንኩም ። እያጨስኩ መሆኔን ደግሞ ላምንም አልፈልግም ። አንዲት የማላውቃት ሴት ተገላልጣ ወደኔ እየተወላገደች ስተመጣ 'አንተ ክፉ ሰይጣን ፡ ከኔ ራቅ' ብዬ #3 ጊዜ ላማትብ ስል እጄን ይዛኝ ከተቀመጥኩበት አስነሳችኝ ። ይዛኝ ወደሆነ ክፍል ወሰደችኝ ። ቀለል ብላ ደስ የምትል መኝታ ቤት ውስጥ ነን ። እኔና እሷ ብቻ ። እንዲህ ውብ ሆኗ እዚህ ቦታ ላይ መገኝቷ ሲገርመኝ ገፍትራኝ አልጋው ላይ ወደኩኝ ። ምን አስባ እንደሆነ እስቲ ልየው ብዬ ዝም አልኩኝ ። ቀስ ብላ ወደ አልጋው ላይ መውጣት ጀመረች ። ለነገሩ እኔ ላይ ነው እየወጣች ያለችው ። ምክንያቱም አልጋው ያለው ከኔ ስር ነውና ። ወደኔ ይበልጥ በ slow motion እየተጠጋች ከንፈሯን ከከንፈሬ ጋር ልታገጣጥም ስትል በሩ ተንኳኳ ። (ምናለበት እስኪ ነገ ቢያንኳኩ ...?) ። ኳ ኳ ኳ ... ። 'ማነው...?' አልኩኝ ጮክ ብዬ በምሬት ። "አንተ አዝግ የፈተና ሰዓት ደርሷል ተነስ" የሚል የዶርሜ ልጅ ድምፅ ተሰማኝ ። ለካ የዶርሜ በር እስኪንኳኳ ድረስ የነበረው ሁሉ በህልሜ ነው ። እኔ ግን 'ማነው' ያልኩት እኮ ከህልሜ ጓደኛ ጋር እያለሁ የተንኳኳ መስሎኝ ነው ። የዶርሜ ልጅም "ጠዋት እኮ ወደ class ስሄድ ከሩቅ አይቼህ ነበር ። ከዛን #2 period ተምረን ምሳ በልቼ መጣሁ ። እንዳጋጣሚ ደግሞ ቁልፌን ምግብ ቤት ስበላ አስቀምጬ ሳላነሳው ረስቼ መጣሁ ። ለዛ ነው ያንኳኳሁት" ብሎኝ ተያይዘን ወደ መፈተኛ ክፍል ጉዞ ጀመርን ።


ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................
😘የከንቲባው ልጅ😘

🔥ክፍል 18


.
.
.
በሩን አልፌ የመሄድ አቅም አልነበረኝም ። ዘጋሁትና ወደሷ ተመልሼ እቅፌ ውስጥ አስገባዋት ። ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ፤ ሁለመናዋም ይንቀጠቀጣል ። 'እሽሽሽ ፡ በቃ አታልቅሺ ፣ በየትኛውም ጊዜና ቦታ ካንቺ ጋር ነኝ ። ትቼሽ የትም አልሄድም ። ሁሉንም ችግሮችሽን ላላስወግድልሽ እችላለሁ ፤ ነገር ግን ብቻሽን እንድትጋፈጪው በፍፁም አላደርግም' አልኳትና ዕምባዋን ጠራርጌ ፡ ግንባሯን ፣ አይኗን ፣ ጉንጯንና አንገቷ ስር ስሜያት ተያይዘን ወደ ቤት ተመለስን ። ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ዘንድሮ ባወጣው ህግ መሠረት የ #3 ቀን ቀሪ ከጊቢው ያሰናብታል ። የኔ ቀሪ ደግሞ ከዚያ እያለፈ ስለሆነ ትንሽ አሳስቦኝ እንጂ መጀመሪያውኑ የትምህርት ፍቅር ኖሮኝ አይደለም ወደ ጊቢ ለመመለስ የተነሳሁት ። ይሄው አሁን ትምህርቱ ላይ ፈርጄ የከንቲባው ልጅ ቤት ቀርቻለሁ ። ትውልድ ይዳን ፤ ትምህርት በኔ ይብቃ ። ሳስበው ግን ህይወት በዚሁ ሁኔታ ከቀጠለች ወደፊት ልጄን ትምህርት ቤት ወስጄ የማስተምረው አይመስለኝም ። ለነገሩ ልጄ እንደኔ ደደብ ፣ ደነዝ እና ሰነፍ የሚሆን አይመስለኝም ። በኔ ከወጣ ግን ውሃ በላው ። Campus ባይገባ ነው የሚሻለው ። ልግባ ቢል እራሱ ማን ሲያስገባው ...? ከኔጋር እየኖረ ትምህርቴን ማቄን ምናምን የሚል ከሆነ #18 ዓመት እስኪሞላው ደረስ አልጠብቅም ። ልክ ይቺን ጥያቄ ስያነሳ በሬን ከፍቼ ካለኝ ንብረት ላይ የድርሻውን ሰጥቼው አሰናብተዋለው ። (ንብረት ግን የሚኖረኝ አይመስለኝም ... ። የኔ ነገር ፡ ለራሴም ሳልሆን የልጄን ፈተፈትኩ አይደል ። (አንተ ልጅ ግን ልጅ አለህ እንዴ ...?። ምን ላርግ ፡ ከ #3 ወር በፊት የተፈተነው Applied Maths final ፈተና ትዝ ብሎኝ እኮ ነው ። On time #02:00 ሰዓት ሻርፕ (flat ...) ላይ class ተገኘሁና አሰላለፍ አሳምሬ አስተማሪውን ጠበቅነው ። ዛሬማ ካልደፈንኩት ከዚህ ክፍል ውስጥ ንቅንቅ አልልም ብዬ ቆረጥኩ ። በስተ ሰሜን ጎበዙ የዶርሜ ልጅ ፣ በስተ ደቡብ ከዋላዬ ስለሆነ አይመቸኝም ፣ በስተ ምስራቅ ከክፍል #1ኛ ውጤት ያለው ልጅ ፣ በስተ ምዕራብ ደግሞ ከዲፓርትመንታችን ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ልጅ ተቀምጠዋል ። Morino እራሱ አሰላለፍ እንዲህ አይችልበትም ። የተከተልኩት የጨዋታ ስልትም ፡ ትንሽ ማንበብ + ብዙ መኮረጅ = #50/50 የሚለው ነው ። ኩረጃ ላይ ብዙም ልምድ የለኝም ። እንግዲህ የኔ ጉድ ዛሬ ይታያል ። (ጉድ = Good ...) ፈታኙም ፈተናውን ይዞ ከተፍ አለ ። (ምናለበት አሁን ቢቀር ይሞታል ...?) ። ፈተናውን ጠረጼዛ ላይ አስቀመጠና እንዲህ አለን "Continous ከ #50 ሁላችሁም ከ #40 በላይ ስላመጣችሁ አይያዝም ። ስለዚህ የዛሬው ፈተና የሚያዘው ከ #100% ነው ። #90 ጥያቄ ተዘጋጅቷል ፣ ለእያንዳንዱ ጥያቄ #3 pharagraph ትፅፋላችሁ ። ሁሉም ጥያቄ የወጣው ከተማራችሁት ውጪ ሲሆን ፤ ጥያቄዎቹ እንኳን ለእናንተ ለኛም አዲስ ናቸው ። የቀረው #10% ነጥብ ደግሞ ስማችሁን በቻይንኛ መፃፍ ይሆናል ። አሁን ፈተናውን እንጀምራለን ልክ ጀምሩ እንዳልኳችሁ pencil down እላቹዋለው ታቆማላችሁ ። ፈተናው ላይ #1 ኤክስ የገባበት ተማሪ ከጊቢው ይሰናበታል ። መልካም ፈተና ። ነጮች "ስለ ሰው ይበልጥ ባወክ ቁጥር ውሻህን ትወደዋለህ" ይላሉ ። እኔ ግን እላቹዋለው 'ስለ Maths ይበልጥ ባወክ ቁጥር አለመማርን ትወዳለህ' ።...

ከከንቲባው ልጅ ጋር ቲቪ ከፍተን እያየን እያለ ስልኬ ላይ Msg ገባና አውጥቼ ሳየው Cost ገብቶልኝ ነው ። Non cafe ስለሆንኩኝ እንደ ተለመደው መንግስት #450 የኢትዮጵያ Dollar ባንክ account ላይ አስገብቶልኛል ። እኔ የምለው ግን ፡ መንግስት ለካ እንዲህ ቋጣሪ ነው ። cost መግባት የነበረበት በየወሩ በ #28 ነበር ። የዚህኛው ወር ግን በ #36ኛው ቀን ነው የገባው ። ቆይ ግን #450 ብር ለ #1 ወር በዚህ ኑሮ ፡ ብር ሆና ነው የምትበላው ...? ያውም ከተማሪ ። እኛኮ ለምሳ እና እራት ብቻ #1200 ብር ነው የምንከፍለው ። እነሱ ግን የ #5 ሚሊዮን ብር እራት በልተው ፤ በ #450 ብር መፋቅያ ጥርሳቸውን ይፍቃሉ ። Bisrat tv እያየን ነው ። ፕሮግራሙም ስለ ሶሪያ ህፃናት ነው ። አንድ የ #7 ዓመት ህፃን እንዲህ እያለ ነው "በሽር አል አሳድ'ን (የሶርያ president) ምን አደረግነው ...? ዝምብለን እየኖርን ነበር ። ምንም ሳናደርገው ቤታችንን አፈራረሰብን ፣ ቤተሰቦቻችንን እንዳለ ገደላቸው ። ቆይ ግን ምን አድርገነው ነው ...?" ። ይሄንን ሲናገር ፊቱ እንደ ጎርፍ ዝናብ በዕምባ ተሞልቶ ነበር ። ሶሪያ ውስጥ የሞቱት ህፃናት ብቻ ከ #50,000 በላይ ናቸው ። አብዛኛዎቹ ሀገር ሰላም ብለው የትምህርት ገበታ ላይ የነበሩ ታዳጊዎች ናቸው ። በራሳቸው ጥፋት ሳይሆን በአባቶቻቸው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት ነገን ሳያዩ ዛሬን ሳይኖሩ በአጭር የተቀጩ ህፃናት ። ዛሬም ድረስ ጦርነቱ ቀጥሏል ፣ ሀገሪቷ ምድረ በዳ ሆናለች ፣ የሶሪያ ህፃናትና ህዝቦችም ስደት ላይ ናቸው ። አሸናፊ የሌለው የእርስ በእርስ ጦርነት መጨረሻው እንግዲህ ይህ ነው ። ከወር በፊት ሳቢያን ፡ ድሬዳዋ ብር ለማውጣት ባንክ ቤት ስሄድ መንገድ ላይ የሶሪያ ስደተኞች ተቀምጠው ሲለምኑ አይቼ ነበር ። ባልና ሚስት መሀላቸውን ልጃቸውን አስቀምጠው ፊትለፊት ደግሞ በአማርኛ ፊደል የተፃፈ "የሶሪያ ስደተኞች ነን ፡ እባካችሁን እርዱን" የሚል Copy ወረቀት ተቀምጦ ፣ በዚያ በኩል የሚያልፍ ሰው ደግሞ ከንፈሩን እየመጠጠላቸው ያለውን #1 ፣ #5 ፣ #10 ብር እየሰጣቸው ያልፍ ነበር ። እኔም ሳያቸው አንጀቴን ነበር የበሉኝ ። በተለይ ደግሞ መሀላቸው የተቀመጠው ፣ ምንም የማያውቀው ፣ #4 ዓመት እንኳን ያልሞላው ህፃን ልጅ እንዴት እንደ ሚያሳዝን ። anyways አያድርገውና ኢትዮጵያን ሳስባት እንደ ሶሪያ ካልሆንኩኝ ሞቼ እገኛለሁ ያለች ትመስላለች ። ሰላም ስልችት ብሏት ደም ደም ከሸተታች ሰነባብታለች ። ሰላም ሲሆን ጀርባዋን ይበላታል መሰለኝ ግደል ግደል ፣ ሰልፍ ውጣ ሰልፍ ውጣ ፣ ኮብል ኮብል ፣ አፍርስ አፍርስ ፣ ረብሽ ረብሽ ፣ ወዘተ ወዘተ ይላታል ። (ወዘተ ወዘተ እንኳን አይላትም ...) ። ከሶሪያ እንኳን መማር አልቻለችም ፤ የሰላም ዋጋ ምኑም አልገባትም ። ዛሬ ሁላችንም በየቤታችን ሆነን የምናየው የሶሪያ መጨረሻ የሌለው ዕልቂት ፣ መድረሻው የማይታወቅ ስደት ፣ መልስ የማያገኝ ጥያቄ ፣ ቀስ በቀስ የኛው ታሪክ ሆኖ ዓለም በየቤቱ ቁጭ ብሎ ይታዘበናል ። ልክ ዛሬ ለነዚህ ስደተኞች ከንፈር እየመጠጥን ሳንቲም እንደ ወረወርን ፤ አንድ ቀን ደግሞ ለኛም በባዕድ ሀገር ይወረወርልን ይሆናል ። ይሄ እንዳይሆን ከፈለግን ሁሉን ነገር የመንግስት ስራ ነው ማለቱን ትተን ለሰላማችን ስንል እራሳችን ፣ ቤተሰባችን ፣ ጓደኛችን ፣ ጎረቤታችን ፣ ሰፈራችን ፣ ቀበሌያችን ፣ ወረዳችን ፣ ዞናችን ፣ ክልላችን ፣ ምናምን ሳንል ለአንዲት ሀገራችን በጋራ ብንሰራ የተሻለ ብቻ ሳይሆን ተመራጭም ይሆናል ።....
​​🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 21


.
.
.
ህይወት ልታለቅስ ነው መሠል ደንግጣ ፍዝዝ ብላለች ። ዋነኛው ምኞቷ በነፃነት መኖር እንደሆነ ነግራኝ ነበር ። ታድያ ጊዜው ሲደርስ ምን አሸበራት ...? ነው ወይስ ደስታው ነው ባለችበት ደርቃ እንድትቀር ያደረጋት ...! የሷ ይቆየኝና ግን እኔም ልክ አባቷ "ተያይዘን አሜሪካ ሄደን በነፃነት እንኖራለን" ሲሏት የልብ ምቴ ፈጥኖ ፣ ፊቴም ተለዋውጦ ነበር ። ከውስጤም ልክ የሆነ አካል እንደጎደለ ተሰምቶኛል ። "ምነው የኔ ህይወት ፡ ደስ አላለሽም እንዴ ...? እኔኮ ይሄን ስነግርሽ ከምንጊዜውም በላይ የምትደሰቺ መስሎኝ ነበር" አሏት አባቷ ። ህይወትም ድምጿ እየተቆራረጠ "አያይ አባቢ ፡ ደስ ብሎኛል ፡ ግን በቃ የአቤል ደም ፍትህ ሳያገኝ እንደ ውሃ ፈሶ ቀረ ማለት ነው ...?" አለቻቸው ። አባቷም በረጅሙ ተነፈሱና "አይደለም የኔ ህይወት ፡ አንቺን ለ #4 ዓመት እዚህ በድብቅ አስቀምጬሽ ስራ ላይ ጊዜዬን ያጠፋሁትም ለዚሁ ነበር ። የአቤልን ደም ያፈሰሱትን ሰዎች ህግ ቦታ ይዤ ሄጄ እነዚህ ናቸው ገዳዮቹ ብል የሬሳ ምርመራ ብለው መቃብር ስለሚቆፍሩ ሟቹ አቤል እንጂ አንቺ እንዳልሆንሽ ለጠላቶቼ መንገር ስለ ሚሆንብኝ እሱን መንገድ አልተከተልኩም ። ሁሉም ሰው የሚያውቀው አንቺ እንደሞትሽ እንጂ ስለ አቤል ምንም የሚያውቁት ነገር የለም ። ፖሊሶቹን ጭምር ለምርመራ ሲመጡ 'ሲገድሏት የት ነበራችሁ ...? አሁን ወሬ ለቀማ ነው የመጣችሁት...?' ብያቸው ስለ ጮኹኩባቸው ፣ በዛላይ የከተማችን ከንቲባም ስለነበርኩ ሬሳውን ለማየት አልደፈሩም ። ስለዚህ የነበረኝ ብቸኛው አማራጭ ሰዎቹን በለመዱት የወንጀል ስራቸው ሲጨማለቁ በጥብቅና በቅርበት ተከታትሎ በቂ ማስረጃ ማሰባሰብ ነበር ። ሰዎቹ በዋዛ የሚያዙ ባይሆኑም በስተመጨረሻ ግን በእጄ ወድቀው ለዘላለም እስር ቤት ውስጥ እንዲማቅቁ አድርጌያቸዋለው" አሏት ። ህይወትም "ታድያ እነሱ ከታሰሩ የኛ መሸሽ ከማነው ...?" አለቻቸው ። እሳቸውም "የኔ ህይወት ፡ እነዚህ ሰዎች እስር ቤት ገቡ ማለት የተንኮል ስራቸውን አቆሙ ማለት አይደለም ። እንደውም እዛ በመግባታቸው ሰይጣንነታቸው ቢብስ እንጂ አይቀንስም ። ፍርድ ቤት ሲፈረድባቸው እንዴት ገላምጠው እንዳዩኝ አታቂም ። በዚህም በዚያም የኔ ህይወት ፤ አሁን ስለነሱ የምናስብበት ጊዜ አይደለም ። ማሰብ ያለብን አሜሪካ ስንሄድ ስለሚጠብቀን አዲሱ ህይወት ነው ። ባለፈው መጥቼ ፋይሎችሽን እንዳለ የወሰድኩትም ለዚሁ process ነበር ። አሁን ሁሉም ነገር አልቋል ። መሄድ ብቻ ነው የቀረን ። አዲስ አህጉር ፣ አዲስ ሀገር ፣ አዲስ ከተማ ፣ አዲስ ቤት ፣ አዲስ ት/ቤት ፣ አዲስ ጓደኞች ጭምር ይኖሩሻል" አሏትና ፊት ለፊታቸው የተቀመጠውን ወይን አንስተው ተነሱና አንዴ ከተጎነጩ በዋላ ግንቧሯን ሳሟትና "በጣም ደክሞኛል እሺ የኔ ህይወት ፡ ቀሪውን ነገ እናወራለን ፡ አሁን ገብቼ ልተኛ" አሏትና እኔ ወዳለሁበት አቅጣጫ መራመድ ጀመሩ ። በሩ ጀርባ ተሸሸኩኝ ። የክፍላቸውን በር ከፍተው ገብተው ሲዘጉት ተመልሼ በበሩ ወደ ሳሎን ማየት ቀጠልኩኝ ። በህይወት ፊት ላይ ምንም አይነት የደስታ ስሜት አይታይም ። ፊቷን ደመና ያዘለ ሰማይ አስመስላ ከሶፋው ላይ ተነስታ ወደኔ መጥታ ገባችና በሩን በቀስታ ቆለፈችው።
ምንም ሳትለኝ አልጋ ውስጥ ገብታ ጀርባዋን ሰጥታኝ ተኛች ። ምን ሆነሽ ነው ...? ልላት አልፈለኩም ። አባቷ የተኙት ከአጠገባችን ባለው ክፍል ውስጥ ስለሆነ ለማውራት አይመችም ። በተጨማሪም በራሷ ፍቃድ እንድትነግረኝ ነው የፈለኩት ። እኔም ያወሩትን ነገር እያንዳንዷን እንዳልሰማሁ ምንም እንዳል ተፈጠረ በማስመሰል አልጋው ውስጥ ገባሁና ጀርባዬን ሰጥቻት ተኛሁ ። አይኖቼ ግን አልተከደኑም ። ብዙም ደቂቃ ሳይቆይ ግን ህይወት በጀርባዬ በኩል ተለጥፋብኝ በታፈነ ድምፅ ማልቀስ ጀመረች ። ቀና ብዬ መብራቱን አብርቼ ዞሬ ሳያት በዕምባዋ አንሶላና ትራሱን አረስርሳለች ። እቅፍ አድርጌያት እምባዋን መጠራረግ ጀመርኩኝ ። ግን ማስቆም አልቻልኩም ። ዕምባ ከአይኖቿ ሲፈስ ፡ በእጆቼ ስጠርግ ፣ አሁንም ሲፈስ ፡ ደግሜ ሳብስ ፣ መላው ሲጠፋኝ 'እሽሽሽ በቃ ፡ በቃ ፡ ስወድሽ አታልቅሺ ፡ የዕምባሽ መፍሰስ ትክክለኛውን ምክንያት ባላውቅም ፡ ምናልባት ግን ሊያስቆመው የሚችለውን ጉዳይ ንገሪኝና መፍትሄ እንፈልግለት' አልኳት በለሆሳስ ። እየተንሰፈሰፈች ፣ ከዕምባዋ ጋር በአፍንጫዋ የሚወርደውን ውሃ መሠል ንፍጥ ወደላይ አየመለሰችና እየጠራረገች "ለምን እንደማለቅስ ከነገርኩህ ራስ ወዳድ ነሽ አትለኝም ...?" አለችኝ ። 'አልልሽም ፡ በይ ንገሪኝ' አልኳት ማቆምያ የሌለውን ዕምባዋን እየጠረኩላት ። "እንደውም እርሳው በቃ" ብላኝ እንደ ቅድሙ ጀርባዋን ሰጥታኝ ተኛች ። እኔም "ዛሬ እንጂ ነገ የት ይሄዳል ...?" ብዬ መብራቱን አጠፋሁና ለመተኛት ሞከርኩኝ ። ግን አይኔ አልከደን አለኝ ። ስልኬን አወጣሁና data አብርቼ Telegram ገባሁ ። የክፍሌ group ላይ ነገ Material ፈተና አለ ተብሎ ተለቋል ። በልቤ ችግር ላይ ሌላ ችግር አልኩና data አጥፍቼ ፣ አባቷ ቀድመውን እንዳይነሱ Alarm ሞልቼ ተኛሁ ። እንቅልፍ ባይኔ ስላልዞረ ጠዋት አላርሙን እራሴው ቀሰቀስኩትና ተነሳሁ ። ልጅቷንም ቀስ ብዬ በእጄ ትከሻዋን ነካ ነካ እያደረኩ በሹክሹክታ 'ህይወት ፡ ህይወት' እያልኳት ስጣራ ተነሳችና ወደ ጊቢ መመለስ እንዳለብኝ ከነምክንያቱ ነገርኳት ። አባቷ ቤት እንዳሉ ረስታለች መሠለኝ "ሂድ በቃ" አለችኝ በደከመ መንፈስ ። 'መሄዱማ የት ይቀራል ፡ ግን እኮ አባትሽ እቤት ናቸው እንዴት ነው የምወጣው ...?' አልኳት ። ሴት ልጅ መለኛም አይደለች ። እኔ የቤቱንና የአጥሩን በር ከፍቼ ስወጣ አባቷ እንዳይሰሙ እሷ ክፍላቸው ገብታ ሙዚቃ ድምፁን ከፍ አድርጋ እንደምትከፍት ነገረችኝ ። ከአባቷ ጋር ጓደኛም ጭምር ስለሆኑ በዛን ሰዓት የሚያስቡት እሳቸውን ለመረበሽ የፈጠረችው ነገር እንደሆነ ነው ። ያለውን ነገር በስልክ እርስ በርስ እንድናሳውቅ ተነጋግረን እሷ ጉንጬን እኔ ደግሞ አይኖቿን ሳምኩኝና ተሰነባብተን እንደ ተባባልነው ልክ እሷ ከሳሎን በጂፓስ የሙዚቃውን ድምፅ መጨረሻ ላይ አድርጋ ስትከፍት በሩን ከፍቼ ሸመጠጥኩት ። ከጊቢው ስወጣ በረጅሙ ተነፈስኩና ቁልፎቹን በበሩ ስር ወርውሬላት ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ አቀናሁ ። የሙዚቃው ድምፅ ውጪ ድረስ ይሰማ ነበር ። ቤት ውስጥ እያለሁ ሲከፈት ...

"ቀኑ መሽቶ ጨላለመ ፡ ብሎ
ተስፋ ቆርጦ ከደከመ ፣
ደስታውን ያራቀው ለታ ፡
ያኔ ነው ሰው የሚረታ" ።

እያለ ነበር ። አሁን ግን ድምፁ ቀስ በቀስ እንዲህ እያለ እየራቀኝ መቷል ...

"እኛ ከሌለን ባዶ ፡ እኛ ከሌለን ባዶ ፣
እኛ ከሌለን ባዶ ፡ አዎ
ይ................
ቀ..................
ጥ...................
ላ....................
ል....................

🌺የከንቲባው ልጅ🌺

🔥ክፍል 23


.
.
.
ሁሉም ተማሪዎች calculator ይዘው ነው የመጡት ። እኔ ግን በህልሜ የመረቀንኩት አለቀቀኝም መሰለኝ ብዕር እንኳን አልያዝኩም ። ብዕሩን እንደምንም ከመምህር አግኝቻለሁ ። calculator ቀድሞውኑ ለድምር አያስፈልገኝም ፤ አየር ላይ አጫውተዋለሁ ። ብዙ ጊዜ ተማሪ ፈተና ሲደርስ ሲጨናነቁ አያለሁ ። እኔጋር ግን እሱ የለም ። የምችለው ከሆነ እሰየው ፤ ካልሆነ ግን ሲፈልግ ገደል ይግባ ። (ፈተናው ሳይሆን አንተ ነህ ገደል የምትገባው...🙆) ። ፈተናው ተሰጠንና አየሁት ። #5 ጥያቄ ነው ። ከነሱ ውስጥ ግን እኔ ከአንደኛው ጥያቄ ውጪ አንድም info የለኝም ። እያንዳንዳቸው #4 ፣ #4 ነጥብ አላቸው ። ስለዚህ ከ #20% ውስጥ #4% ነው የማገኘው ማለት ነው ። የማውቃትን #1 ጥያቄ ሰርቼ የቀሩትን ደግሞ ከልጆች copy paste ላደርግ ብዬ ቀና ስል #2 አስተማሪዎች አንዱ ከፊት ሌላኛው ደግሞ ከዋላ ሆነው ድምበር እየጠበቁ ነው ። ጥሎብኝ ፈተና ሲከብደኝ መጨናነቅ አልፈልግም ። የቀሩትን #4 ጥያቄዎች በመሰለኝና ደሳለኝ ሞልቼ ወጣሁ ። ከሳምንታት በፊት "ምነው አንተ ልጅ እያሽቆለቆልክ እኮ ነው ፣ በጣም ከስተሃል" ባሉኝ አንደበታቸው ዛሬ ግን class ውስጥና መንገድ ላይ ያገኙኝ ልጆች እንዳለ "ምን ተገኘ ደግሞ ፡ በጣም ተስማምቶሃል" እያሉኝ ያልፉኝ ጀመር ። እንደውም የተመልካች አይን ሲበዛብኝ ሰግቼ ትፉልኝ ማለት ጀመርኩኝ ። እነሱ ግን ትፉልኝ እና ትፉብኝ መለየት ስለከበዳቸው በዋላ ላይ ማስታጠብያ ገዛሁና እሱ ውስጥ እንዲተፉልኝ አደረኩ ። ሁሉም የውፍረቴን ምክንያት ቢጠይቁኝም ፡ እኔ ግን ትንፍሽ አላልኩም ። ምክንያቱም ከዚህ በፊት ስከሳ አንድም ሰው የክሳቴን ምስጢር አልጠየቀኝምና ። ዶርም መሄድ ስላስጠላኝ ወደ Library አቀናሁ ። የተባረከው ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ንሰሐ ይገባል ፤ እንደኔ አይነቱ ደግሞ ቤተ መፅሐፍት ገብቶ ላይገባው ግራ ይጋባል ። Final ፈተና እየደረሰ በመሆኑ ሶስቱም የጊቢው Library እንደ አባይ ሞልተው ተማሪዎች ወደ ግብፅ እየፈሰሱ ይገኛሉ ። አሁን ያለሁት ከሶስቱ አንዱ በሆነውና ዘንድሮ ተመርቆ ስራ በጀመረው Central Science and technology Library ውስጥ ነው ። ይሄ ቤተ መፅሐፍት ግን በጣም ዕድለኛ ነው ። ስንቱ ተምሮና ተመርቆ ስራ ባጣበት ዘመን ላይ ነው ሳይማር ተመርቆ ስራ የጀመረው ። anyways እኔ እንኳን የገባሁት እንደ ሌሎቹ የትምህርት መፃፍ ላነብ አይደለም ። ላይብረሪው ከትምህርት መፅሐፍ ውጪ ፡ ጋዜጣ ፣ መፅሔት ፣ FB ፣ Telegram ፣ ወዘተ መጠቀምያ ቦታ አለው ። ያውም እንደ ሳሎን በሶፋ የተሽቆጠቆጠ ቦታ ። እና ብዙ ጊዜ እዚህ እየመጣሁ Telegram ስለምጠቀም ላይብረሪስቶቹ ጭምር ሸምድደውኝ እንደ ድንገት እንኳን አርፍጄ ቦታው ላይ ሰው ሊቀመጥ ሲመጣ "ሰው አለው" ማለት ጀምረዋል አሉ ። እዚህ የሚገኙ ጋዜጦች ግን አይመቹኝም ። ከነሱ ይልቅ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ሽንት ቤቶች ግድግዳ ላይ በተለያዩ የጊቢው Activist ተማሪዎች የሚፃፉት ሺህ እጥፍ ይማርካሉ ። ብዙ ጊዜ እንደውም የETV ዜና ሲናፍቀኝ ወደ ሽንት ቤት ጎራ እልና አነባለሁ ። ወደ ውስጥ ሳትዘልቅ ገና ከበሩ መግቢያ ላይ ይጀምራል ። "እንኳን ወደ ተመስገን በየነ የምግብ ማስወገጃ አዳራሽ በደህና መጣችሁ ። እናንተ ብቻ ጠንክራችሁ ብሉ እንጂ እኛ የናንተን የከበሩ ማዕድናት ለመቀበል #24 ሰዓት ዝግጁ ነን ። ለደንበኞች ቦታ ይያዛል ፣ በተጨማሪም በራሳችን ጉልበት ውሃ ወደ ሽንት ቤቱ እንደፋለታለን" ። ወደ ውስጥ ገብታችሁ ሱሪ አውልቃችሁ ቁጭ ስትሉ ደግሞ በአምስቱም አቅጣጫ (ከፊት በር ላይ ፣ ከዋላ ፣ በቀኝ ፣በግራ እና ኮርኒስ ላይ) ከሽንት ቤቱ ውጡ የማያስብሉ ምርጥ ምርጥ ቀልዶችን ያገኛሉ ። ከሁሉም ግን እኔን የምትመቸኝ "ለዚሁ ነበር እንደዛ የበላሁት ...?🙆" የምትለዋ ነች ።

ምሽት ላይ እራት ከጓደኞቼ ጋር በልተን ቶኒ ላይ ሻይ ጠጥተን #01:30 ወደ ዶርም ስንመለስ ህይወት ደውላልኝ telegram እንድገባ ነገረችኝ ። ቀኑን ሙሉ ያልደወለችልኝ አባቷ እቤት ስለዋሉ እንደሆነና በቅርቡ ደግሞ ከሀገር እንደሚወጡ ነገረችኝ ። አብዛኛው ወሬዋ ግን ናፍቆት ነክ ነበር ። እንደውም በ voice ጭምር እየዘፈነች ልካልኛለች ። Studio ሳትገባ ዝምብላ እንደ ቀልድ የምትልክልኝና እቤቷ እያለሁም የምታዜምልኝ ሙዚቃዎች ህይወት አላቸው ። እሱ ብቻ አይደለም ፤ የምትፅፍልኝ መልዕክቶች ጭምር ልቤን ያቆሙታል ። "ቀኑን ሙሉ ስላንተ ሳስብና ስፅፍልህ ነበር የዋልኩት" ብላኝ ይሄን መልዕክት ላከችልኝ ። "ከዋክብትንና የምድር አሸዋን መቁጠር ከሚሳንህ በላይ ላንተ ያለኝን ስሜት በቁጥር ማወቅ ያዳግትሀል ። በዚች ምድር ላይ ለመኖር #1ሺህ ምክንያቶች ላያስፈልጉኝ ይችላሉ ። ባይሆን ያንተ መኖር ብቻ በራሱ በቂዬ ነው ። አንተ የቀኔ ፀሀይ ነህ ፤ ብሩህ ታደርግልኛለህ ። የምሽቴም ጨረቃ ነህ ፤ ጨለማዬን ትገፍልኛለህ ። ልቤ ፣ ደምስሬ ፣ አይምሮዬ ፣ ንግግሬ ፣ ልብ ምቴ ፣ ህይወቴ ፣ ሁሉ ነገሬ ውስጥ ገብተሃል ። ሌላው ይቅር ፡ አይኔን እንኳን ስጨፍን የምትታየኝ አንተ ነህ ። ብዙ ጊዜ ስትጎጂ እና ስታለቅሺ ማየት አልፈልግም ብለኸኛል ። የኔ ጌታ እየተጎዳሁና እያለቀስኩ ነው የዋልኩት ። አውቃለሁ አጠገቤ መሆን ስላልቻልክ እንጂ እኔን ለመጉዳት እንዳልራከኝ ። ቢሆንም ግን በጣም እየፈራሁ ነው ። ህይወት ላንተ ናት ፡ ሞት ግን ለኔ ፣ ደስታ ላንተ ነው ፡ ሀዘን ግን ለኔ ፣ አብሮ መሆን ላንተ ፡ ብቸኝነት ግን ለኔ ፣ ሁሉ ነገር ላንተ ፡ አንተ ግን ለኔ ነህ ። አንተን መናፈቅ ያስደስታል ፤ ለዛም ነው ቀኑን ሙሉ የማስብህ ። ምሽት ላይ ሆኜ አንተኑ ሳስብህ ከዋክብት አዝነውልኝ ሊያፅናኑኝ ከሰማይ ላይ ይረግፋሉ ። ምናልባት ሰማይ ባዶ ሆና ካገኘሀት ብዙም አትደነቅ ። ምክንያቱም በደምብ እንዳስብህ አድርገህኛልና ። ቀኑን ሙሉ ድምፅህን ሳልሰማ ፣ አይኖችህን ሳላይ ፣ በናፍቆት አሳለፍኩኝ ። ረስተኸኝ ይሁን እያልኩ እጨነቃለሁ ። የኔን ስሜት ሳልነግርህ ከማንም በላይ ታውቀዋለህ ብዬ አስባለሁ ። አብጄ አማኑኤል ብገባ እራሱ አንተን መርሳት የሚቻለኝ አይመስለኝም ። ደግሞ ህይወት መልሳ እንደምታገናኘን እና ወደፊት አንድ ቀን አብረን እንደ ምንህን ተስፋ አደርጋለሁ ። በህይወት መንገድ ላይ መመለስ የለም ፤ ጉዞው ወደፊት ብቻ ነው ። በመንገዴ ውስጥ ብዙ ሰው ላይኖር ይችላል ። ለኔ ግን እሱ አያሳስበኝም ። ነገር ግን የኔ ጌታ ፡ ያንተ አለመኖር ያማል ። ከአለም ጋር ከተለያየን ቆየን ፤ ምክንያቱም የኔ አለም አንተ ነህ ። ፀሀይ ፊቷን አዙራብኝ ብርሃን ካጣሁ ቆይቻለው ፤ ምክንያቱም የኔ ፀሀይ አንተ ነህ ። ጨለማ ውስጥ ነኝ ፣ ምንም አይታየኝም ። ጭር ያለ ቦታ ነኘ ፤ ምንም አይሰማኝም ። እልም ያለ በረሃ ውስጥ ነኝ ፤ በውሃ ጥም ልሞት ነው ። ቀኑንና ለሊቱን መለየት ከብዶኛል ። በቶሎ ላገኝህ ብዬ ተኝቼ አሁንስ ነጋልኝ ስል ተመልሶ ይጨልማል ። እኔ አንተን ሳጣህ እንኳን ቀኑን እራሴንም እረሳለሁ ። ግን የኔ ጌታ እስካሁን ድረስ ያልረሳሁት #

1 ነገር አለ ። እሱም አንተ ነህ ። ምክንያቱም አንተን እረሳሁ ማለት በህይወት የለሁም ማለት ነው" ። ይሄን ሁሉ ብላኝ ፣ በድምጿም እየዘፈነች ልቤን ብታቆመውም የኔ መልስ ግን ዝምታ ነው ። ዝም ....ይቀጥላል